“ሆያ ሆዬ… ያች ድንክ አልጋ… ሆ… አመለኛ” (ሊያነቡት የሚገባ)

ተመስገን ደሳለኝ - አዲስ አበባ

በልጅነት ዕድሜያችን ከሚወደዱ እና ከሚናፋቁ ወራቶች ነሐሴ ዋነኛው ነው። በተለይ ለብላቴናዎች። ለወሩ ተወዳጅነት ምክንያት የሆነው ደግሞ በ‹‹ሆያ ሆዬ›› ጭፈራ የሚከበረው የ‹‹ቡሄ›› ባህል በዚህ ወር መሆኑ ነው። ስለዚህም ከወሩ የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ‹‹ጅራፍ›› እየገመዱ በሚያስጮኹ ማቲዎች መንደሮች ይታመሳሉ። በዚህ አይነት መልኩ እየተዝናኑ ይቆዩና ዕለቱ ሲደርስ ተቧድነው ‹‹ሆያ ሆዬ›› ዕያሉ በየቤቱ ይዞራሉ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢሳት ፤ ታማኝና ሲድኒ

እሁድ ኦገስት 12 ቀን 2012 ዓ.ም.                                 

 (ከኢትዮጵያ ዛሬ ባልደረባ - አውስትራሊያ [ሲድኒ])

ዙሪያ ገባዬን ቃኘሁት። አዳራሹ ጢም ብሏል። በወጉ የምቀርባቸው ፣ በዓይን የምለያቸው ፣ ከቶም የማላውቃቸው. . . በርካታ ሰዎች ከበውኛል ። ሴቶቻችን ከወንዶቻችንም በዝተው ይታያሉ። ታዳጊ ወጣቶች ደግሞ ፎቁ ላይ ተኮልኩለዋል። ሁሉም አቆብቁቦ የሚጠብቀው ውዱን የመብት ተሟጋች፣ አርቲስት ታማኝ በየነን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አብዮታዊ ዴሞክራሲ ልጆቿን እየበላች ነውን!?

አቤ ቶኪቻው
ይህ ጨዋታ ለዚህ ሳምንት ፍትህ ጋዜጣ የተላከ ነበር። ነገር ግን ፍትህ አሁንም በሀገሪቱ እንድትኖር ሰዎቻችን አልፈቀዱም። በፍርድ ቤት የታዘዘው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት “መጀመሪያ ሌላ ቦታ አሳትሙና በሚቀጥለው ሳምንት እኔ አትምላችኋለው” ብሎ መልስ ሰጠ ሲባል ሰማሁኝ። ይሄ በጣም አስቂኝ ነው…! ሌላ ማተሚያ ቤት እኮ የለም። አንድ ቦሌ ማተሚያ ቤት ነበረ እርሱም ደንበኛችን ስላልሆናችሁ አናትምላችሁም ብሏል። ወደየት እየተገፋን እንደሆነ እግዜር ይወቀው!
እስቲ ለማንኛውም ወጋችን ይጀምር… ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ መለስ የማን ናቸው? (ዳዊት ዋስይሁን)

ዳዊት ዋስይሁን

አቶ መለስ ከዚህ በፊት የራሳቸው እንዳልሆኑ በምርጫ 2010 ወቅት ነግረውናል። እንዲህ አሉን ”ድርጅቴ ቀጥል ካለኝ አሉ ”ታዲያ ይህ ድርጅት የትኛው ነው ብትሉኝ? ያልገባቸው ኢሕአድግ ይላሉ መች ሆነና እሳቸውማ የዚህ ድርጅት ሊሆኑ አይችሉም፣ በመጀመሪያ ኢሕአዲግ የሚባል ድርጅት የለም እሳቸውም ያውቁታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የውጭ ጉዳይ ዜናዎች

በሙሉነህ ዮሃንስና የውጭ ጉዳይ ምንጮች የተጠናከረ (ጁላይ 31 2012)

  • አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስን ሲያስታምም ከርሞ ከብራስልስ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሰ ነው!
  • አምባሳደር ሙሉጌታ አለምሰገድ ባጣዳፊ ቤተሰቡን ወደ ጣሊያን አሸሸ!
  • አሜሪካን ሃገር በአምባሳደርነት ማእረግ ያሉ አራት ዲፕሎማቶች ከአበበ ገላው ጋር በተያያዘ ጠቅልለው እንዲመለሱ ታዘዙ!
  • መጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብና የባለስልጣናት ቤተሰቦች ወደ ኬንያ እየተሸጋገሩ ነው!

አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ

ህወሃት በጫካ እያለ ጀምሮ የድርጅቱን ገንዘብ ውጭ ሃገር በማንቀሳቀስ የሚታወቀውና በአሁኑ ወቅት በምክትል ሚኒስትርንት ስም ውጭ ጉዳይን የሚያዘው ብርሃነ ገብረክርስቶስ መለስ ዜናዊ ከታመመ ጀምሮ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ሄድ ኦፊስ) አካባቢ ጠፍቶ መክረሙን በቦታው ያሉ ሰራተኞች አረጋግጠዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ