ሀበሻ በየመን ክፍል 8 (ግሩም ተ/ሀይማኖት)

እዚህ የሰው ልጅ መሰቃያ ቦታ /አልቀረስ ካምፕ ውስጥ/ ስደተኛውም በዘር፣ በጎሳ፣ በእምነት፣ ተቧድኖ የሚባላበት ቦታ ለምን አልገባህም ተብዬ ዱረብል ሶሊሽን አታገኝም የተባልኩት ለምን ይሆን? ሞቴ የሚፈለግበት ምክንያት ይኖር ይሆን? ኤጭ ድከም ብሎኝ ነው እንዲህ ይህን ማሰቤ…እንግዲህ እኔም እንደ የመኑ ፕሬዘዳንት አሊ አብደላ ሳላህ 32 አመት የመንን ሙጥኝ ልል ነው ወይስ እንደ እሳቸው ለየመን ህዝብ ሰሰለቸው በሰላማዊ ሰልፍ ‹‹ይርሀል›› ይሂድልን ልባል ነው? ወይ ጉዴ!!! ወይ ወገን ማጣት……ብዬ ነው ክፍል ሰባት ላይ የተሰነባበትነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔን ሥርዓት ከመጣል ባሻገር (ኢብሮ)

ኢብሮ ከጀርመን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ንጉሥ ኃይለሥላሤ፣ ረሃብና ድርቅ፣ ድህነት አሁን አሁን ደግሞ ሩጫችን እዚህ በጀርመን አገር ጥሩ መታወቂያችን ናቸው። በቃ ኢትዮጵያ ለነሱ እንደዚህ ናት። የኛ መለያ! እኔ ግን እላለሁ የዲሞክራሲ ቸነፈርን አትርሱብኝ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦነግና ኢትዮጵያዊነት – ምላሽ ለዶ/ር ብርሃኑ ክፍል 3-ግርማ ካሣ

ግርማ ካሣ

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ዙሪያ ለአንባቢያ ያቀረብኳቸው ሁለት መጣጥፍት ከፍተኛ የአንባቢያን አስተያየቶችን እንደጫሩ ለማየት ችያለሁ። የድጋፍም ሆነ የተቃውሞ ኤሜሎች በብዛት የደረሱኝ ሲሆን፣ በአቡጊዳ ድህረ ገጽ ላይ የቀረቡ አሰትያየቶች ከወትሮ እጅግ የበዙ ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወድቆ በተነሳው ባንዲራ! አትቀልዱብን!!

ተመስገን ደሳለኝ

…ባለመሆንና በመሆን መካከል

ሰው አይሻገረው፣ አለ ትልቅ ገደል።

የማይሆነው ነገር፣ ምን ጊዜም አይሆንም

የሆነውም ነገር ከቶ አይለወጥም።…

‹‹የኮሌጅ ቀን ግጥሞች›› (ተገኝ የተሻወርቅ-1950ዓ.ም) ፐ-እንዴት ያለ ግጥም ነው! ከተፃፈ ከ54 አመት በኋላም ሳይበርድ ሳይነፍስበት የእኝንዘመኑን ገላጭ ነው። ፕሮፓጋንዳውን ገላጭ ነው። የፖለቲካውን ቅጥፈት ገላጭ ነው። የስርዓቱን ጉምነት ገላጭ ነው። በአጠቃላይኢህአዴግን ገላጭ ነው። አጋላጭም ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ጠላፊው” ሀሳብ ወለድ ጨዋታ

አቤ ቶኪቻው

ወዳጄ … እንዴት ሰነበቱልኝ!?

ዛሬ አንድ እንግዳ ይዤ መጥቻለሁ። እንግዳዬ ለበርካታ ግዜያት በጠላፊነት ሙያ ሀገሩን እና መንግስቱን ይበልጡንም ደግሞ እናት ድርጅቱን አገልግሏል። በስራው የሚኮራ ታታሪ ጠላፊ ነው። ቀጥሎ በራሱ አንደበት ያወጋችሁ ዘንድ እኔ እንደሚከተለው ገለል እላለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ አፍሮ ጉዳይ አልበዛም? (በግርማ ደገፋ ገዳ)

ዘላለም ገብሬ፤ በአዲስ አድማስ ላይ ለወጣው ጽሁፍ ምላሽ ይሆናል ብለህ ስለቴዲ አፍሮ የጻፍከውን አስተያየት አነበብኩት። ጊዜ ኖሮህ ያንን ሁሉ በመጻፍህ ያስመሰግነሃል። ግን ቴዲ አፍሮን አጋኖ ለማድነቅ ተብሎ ቤትና ጨርቅ አስጥል የሆኑ ዘፈንና ዘፋኞች በሙሉ በአንድ ሙቀጫ ታጉረው ባንተ ብእር መወቀጣቸው በጣም አስገርሞኛል። እነዚያን የመሰሉ ባህላዊም ይሁኑ ዘመናዊ ዘፋኞች “ከቴዲ አፍሮ የሚወዳደሩ አይደሉም” ልትለን ከዳዳህ፤ የላንቻና ኩባንያውን ፍሬን ሸራ ግዛና እዚያ’ጋ ፍሬን ያዝ አልልህም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

በቴዲ አፍሮ አዳዲስ ስራዎች ዙሪያ (ከዘላለም ገብሬ)

"ቴዲ አፍሮ ከስንት አንድ ጊዜ ብቅ የሚል ውብ ጀምበር ነው " ውብሸት ወርቅአለማሁ "የተረሱትንም አስታዋሽ ትየባ (በዘላለም ገብሬ)

በቅርቡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ እና በዘሃበሻ ድህረ ገፅ ላይ በቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ስራ ላይ  ያቀረበው ሚዛን ያልደፋ ሃተታ በጥንቃቄ አንብቤዋለሁ አዲስ አድማስ ምን ነካው? የሚልም ስሜት ተሰምቶኛል ምክንያቱም ምን አንደሆነ ባላውቅም ፀሃፊ አጥቶ ይሆናል ከሚል ድምዳሜ ላይ ለመድረስ እስከ መብቃት ድረስ በቅቻለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ በዊኪሊክስ ፋይሎች (ሊያነቡት የሚገባ)

አቢይ አፈወርቅ

(ክፍል 4)

“…የሴቶችን የትምህርት ይዞታ በተመለከተ ጥናት የሚያደርጉት ተመራማሪ በጨለንቆ ያደረጉትን የአንድ ሳምንት ቆይታ ጨርሰው ጁላይ 8 ቀን ነበር ወደ አወዳይ የተመለሱት። ሌሊቱንም በከተማዋ ከሚገኙ ሁለት የበጎ ፈቃድ መምህራን ወዳጆቻቸው ጋር ለማሳለፍ ፈቀዱ። “በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 1 ሰዓት ላይ ግን ያልተጠበቀ ነገር ተፈጸመ። 3ቱም ሰዎች ያደሩበት መኖሪያ ቤት በታጠቁ ፖሊሶች ተከበበ። ተመራማሪውና ሁለቱ የበጎ ፈቃድ መምህራን ተገደው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰዱ። ከታጣቂዎቹ ጋር የነበረ አንድ ሲቪል የለበሰ ሰውም ‘መንግስት ነኝ’ ሲል ራሱን አስተዋወቃቸው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሀበሻ በየመን - ክፍል 7 (በግሩም ተ/ኃይማኖት)

እስረኛ ጠያቂዎች መጡ። የሽምሰዲን ሚስት ለመጡት ጠያቂዎች መታመሜን እንድትነግርልኝ ለመንኳት። ነገረቻቸው። ፖሊሶቹን ለምነው ጉርሻም ሰጥተው ገብተው አዩኝ፡፡ ትግርኛ ትንሽ..ትንሽ ስለምችል የሚያወሩትን እሰማለሁ። ይሄማ አጥንቱ ነው የቀረው ነፍስ የለውም ምኑን እንደክማለን አለች አንደኛዋ። ሌላኛዋ እኛ እንሞክር ማዳንም መግደልም የእሱ ነው ባይ ናት። ውስጤ አነባ ውስጤ ብቻ ሳይሆን አይኔም አንዠቀዠቀው። ተስማምተው እንዲያሳክሙኝ ፈለኩ። ምን ያደርጋል……ብዬ ነው ክፍል 6 ላይ ያቆመኩት። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ