ግንቦት 7፥ ኦነግ እና ኢህአዴግ በ2012

ያሬድ አይቼህ

የአገራችን ፓለቲካ ውጤታማነትና ፍሬያማነት ነው ሚፈልገው። ወሬ ብቻውን እንደውጤት እንደማይቆጠር ያለፉት 20 ዓመታት ምስክር ናቸው። የሚያወሩ ሳይሆኑ፥ በተግባር ውጤት የሚያሳዩ የፓለቲካ ብድኖች ተደማጭነትና አለምአቀፋዊ ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። በጄኔራል ከማል ገልቹ ሚመራው ኦነግ የወሰደው የአቋም ለውጥ በእውነቱ አስደናቂ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

‹‹ሀገር በእጃችን…›› (ሊያነቡት የሚገባ)

ተመስገን ደሳለኝ

(እለተ እሁድ በ22/04/04 የምሁራኑ ፊት-አውራሪ (የሚያምኑበትን በማንፀባረቅ)፤ እንዲሁም የ‹‹መባል ያለበት መባል አለበት›› ፍልስፍና ተከታይ የሆኑት ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በመኢአድ ቢሮ ተገኝተው ‹‹ህጋዊ አስተዳደር እና የመብት ጥያቄ›› በሚል ርዕስ ስር አንድ ጽሁፍ አቀረቡ። ፅሁፋቸውንም ሀሳብ ወደ መሬት አውርደው ለአድማጭ በሚገባ መልክ ተነተኑ። በትንታኔአቸውም የአፄ ቴዎድሮስ ታሪክ ፀሐፊ ከነበሩት አለቃ ዘነበ እንዲህ የሚል ቃል መዋሳቸውን ነገሩን። ‹‹…ሀገር በእጃችን…።›› አፄው የዘመነ መሳፍንትን የስልጣን መተራመስ ተሻግረው ማእከላዊ መንግስትን ለመመስረት ሲጣደፉ የስልጣን ጠቅላይነታቸውን ‹‹ሀገር በእጃችን›› ሲሉ ፍካሬያዊ ትርጓሜ ሰጡት። እነሆ አለቃንም ዶ/ሩንም ደርቤ አመስግኜ ቃሉን ለዚህ ፅሁፍ ርእስ ይሆነኝ ዘንድ ተዋስኩ) ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዲሞክራሲን ያያችሁ? (ክፍል 2)

ሉሉ ከበደ

በዲሞክራሲያዊ ስርዓት የዜጎች መብት

በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ውስጥ ዜጎች ማንም የማይነጥቃቸው፤ መንግስት የማይቸራቸው የማይነሳቸው፤ የአለም አቀፍ ህግ ጥበቃና ዋስትና ያላቸው መብቶች አሏቸው። ማንኛውም ሰው የኔ የሚለውን የግሉን እምነት የመያዝ የመከተል መብት አለው። የሚያስበውን የመናገር፤ የመጻፍ፤ ሙሉ መብት አለው። ማንም ሰው ማንንም ሰው እንዲህ አስብ፤ እንዲህ እመን፤ እንዲህ ተናገር፡ እንዲህ አትናገር፤ ብሎ ሊነገረው አይችልም። ሊያዘውም ሊያስገድደውም አይችልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦነግ “የማይበጀን ይገንጠል!” አለ፤ ኢትዮጵያም ደስ አላት!

አቤ ቶኪቻው

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ቀረብ ብለው ሲከታተሉ ለቆዩ እና የ ገሪቷ ጉዳይ ግድ ይሰጠናል ለሚሉ “ዋና” የአገር ልጆች ታላቅ የምስራች ተሰምቷል። ይህውም አንጋፋው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኦነግ በይፋ የመገንጠል  ሳቡን ትቶ ከሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ጋር በመሆን “ችርቻሮ” ለሚወደው ገዢው መንግስታችን “በጅምላው ሞክረን!” ሊለው ቆርጦ መነሳቱን ማወጁ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለልጅ ልጆቻችን ስንል - የአዲስ ዘመን መልዕክት

ግርማ ካሣ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የአሥራ ሰባት ዓመት ወጣት ነው። ጥይት የጎረሰ ሽጉጥ በእጁ ይዟል። እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ፣ ንግግር አድርገው ወደ ጨረሱ አንድ የእድሜ ባለጸጋ ሰውዬ ቀስ በቀስ ይጠጋል። ሳያስቡት የያዘውን ሽጉጥ ወደ እርሳቸው ደቅኖ ይተኩሳል። ሰውየው ይወድቃሉ። አካባቢው ተረበሸ። ተናወጠ። አምቡላንስ ተጠርቶ በአፋጣኝ በስፍራው ደረሰ። የወደቁትን አባት በአምቡላንሱ የነበሩ የህክምና ባለሞያዎች አነሷቸው። የፍጥነት ጉዞ ወደ ሆስፒታል ጀመሩ። ሆስፒታል ሳይደርሱ በመንገድ ላይ የኝህ ሰው ሕይወት አለፈች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሰላይዎችዎን ይሰብስቡልን

ተመስገን ደሳለኝ

ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር፡- በተደጋጋሚ ጊዜ ቅሬታዬን እንደጻፍኩልዎ ይታወቃል። በተደጋጋሚ ጊዜም ስልጣንዎን ይለቁ ዘንድ ተማፅኝዎታለሁ። በተደጋጋሚ ጊዜም አምባገነናዊ አስተዳደርዎን ነቅፌአለሁ። በተደጋጋሚ ጊዜም የሀገሪቱን ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ጠቅልለው መያዝዎን፣ ለሀገራችን የማይበጅ ስለመሆኑ ምክንያታዊ ትችት ፅፌአለሁ። በተደጋጋሚ ጊዜም… ሙሉውን አስነብበኝ ...

‘ፍርሀቴን አቃጠልኩት’ ለየኔሰው ገብሬ የተጻፈ (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

እነሆ አርባኛው ቀንህ በካህናት ፀሎት ተነሳ። በመላው ዓለም የተበተኑ ወገኖችህም ስምህን ከፍ አድርገው አወደሱ። የጠበሰህ እሳት ከሚያሰማህ ስቃይና ሕመም ይልቅ ትግራይ በቀል ጠላቶችህ እንዲሁም ሆዳምና አድርባዮች የሚያደርሱብን በደልና ግፍ ይበልጥ እንዳሳመመህ ነገርካቸው። ከነፃነት እጦት ሞት እንደሚሻል መራር ሞት ሞተህም አሳየሃቸው። የዘርን አጥር ሰብረህ፣ የጎጥ ፖለቲካን ኮንነህ ኢትዮጵያውያን እንደ ሕዝብ ነፃነትን እንደሚሹ አስተምረህ አለፍክ። ታጋዮች በስምህ ተማምለው ተነሱ። ገጣሚዎች ስምህን ከፍ እያደረጉ ተቀኙ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ