ሰሞኑን፣ አንድ ግሩም መፅሐፍ እያነበብኹኝ ነው፡፡ ባለፈው አርብ ነው የወጣው፡፡ በዳንኤል ተፈራ የተፃፈና በዶ/ር ነጋሳ ጊዳዳ ሕይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን ነው፡፡ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ይዟል፡፡ አንድ ስሜቴን የኮረኮረውን ነገር ላካፍላችኹ ወድጃለኹ፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...ክንፉ አሰፋ
ጁላይ 1፣ አርብ ምሽት አትላንታ ጆርጂያ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረስኩ እንደቅድሞው ብዙ አበሻ ሲርመሰመስ አላየሁም። የአበሻው ትርምስ በ2005 አትላንታ ላይ ተመሳሳይ ፌስቲቫል በተዘጋጀ ግዜ ከነበረው እጅግ ቀዝቀዝ ብሎ ነበር። ይልቁንም ዝግጅቱ አልቆ አትላንታን ስንስነባበት አውሮፕላን ማረፍያው በአበሻ ተጨናንቆ አሜሪካ ሳይሆን፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለን ነበር የሚመስለው። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ዛሬ፣ ማክሰኞ፣ ሐምሌ ዐ5 2ዐዐ3 አዲስ አበባ ውስጥ ከሚታተመው አዲስ ወሬ ጋዜጣ ጋር አጭር ቃለምልልስ አድርጌያለኹ። የጋዜጣው ማኔጂንግ ኤዲተር፣ ዳንኤል ኃይሉ፣ ባለፈው ሰሞን ከመንገድ ላይ ታፍኖ ተደብድቧል፣ ቢሮው ተፈትሿል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ብዕር እስትንፋስ ናት፤ ብዕር ሕይወት ናት፤ ብዕር በሥጋ ወደሙ ላይ ሕይወትን ዕፍ በማለት ሥጋን ነፍስ የምትዘራ ከዕውቀት ዛፍ የምትገኝ ፍሬ ናት፤ ያቺን ፍሬ የቀመሰ ሁለ ማንነቱን አውቋልና ያለ እሷ መኖር አይቻለውም፤ እሷን ያጣ እለት በጨለማ ይከበባል፤ የጨለማ ሕይወት ለመኖር ሲል እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ድረስ ዋጋ ይከፍላል፤ ከራሱ አልፎ ድንበር ሳይገድበው፤ ቀለም ሳይለየው፤ የዘር ሃረግ ሳይጠልፈው፤ ከአድማስ እስከ አድማስ የነፃነት ጮራ ለመላው የሰው ልጅ ፍንጥቅ እንዲል ያደርጋል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)
የፊታውራሪ ተክለሃዋሪያት ተክለማርያምን የሕይወቴ ታሪክ (ኦቶግራፊ) እንደ ክሽን ልብ አንጠልጣይ ልቦለድ ድርሰት እረፍት እየነሳኝ አነበብኩት። እና ምን ተሰማኝ? የፊታውራሪ ታሪክ አኮራኝ፤ ደግሞም ውስጤን አብሰለሰለኝ፤ ከሁሉም በላይ ግን አስተማረኝ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)
እስክንድር ነጋ (አዲስ አበባ)
ሙሉውን አስነብበኝ ...
በገጽ 96 ላይ ከሰው ጋር ተስማምተው ስራ መስራት ስላልቻሉ በነጻ ቀለብ እየተሰፈረላቸው ሲኖሩ ስኮላር ሽፕ ያገኛሉ። ከዚያም ወደ ድርግ ጽ/ቤት ሄደው ቤተ ክህነት ስለተጣላኝ አይሰደኝምና እናንተው ስደዱኝ ብለው ደርጎችን ይማጸናሉ። ከዚአም ደርግ ሰውየው ለትምህርት ዲሄዱ ትቃወማላችሁ እንዴ? ብሎ ቤተ ክህነትን ይጠይቃል። ቤተ ክህነትም እንደማትቃወም ታስታውቃለች። ከዚያም የመጓጓዣ ተከፍሎላቸው፤ የመንገደኛ ወጭ የኪስ ገንዘብ ተከፍሏቸውና ደብዳቤ ተጽፎላቸው በክብር ነው የወጡት ይላል መጽሀፉ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)