ልጅ ተክሌ (ኦታዋ)
ብሄርንና ሀይማኖትን መሰረት ያደረገ ክርክር አስቸጋሪ ነው። ሀይማኖት ይብሳል። በንጽጽር፡ ከሀይማኖት ደግሞ ብሄር ለክርክር ይቀላል። ለጥቂት ጽንፈኛ ኦሮሞዎች የምንወረውረው ትችት ወይንም ስላቅ፡ አያሌ ለስላሳ ኢትዮጵያዊ ኦሮሞዎችን ሊያስቀይም ይሆንብናል። በመርህ ደረጃ፡ ከማናቸውም ብሄር-ቀመስ ድርጅቶች ጋር የሚደረግ ውይይት ባያስደነግጠኝም፡ መጀመሪያ ይሄ የግንባር/ህብረት ምስረታ ጉዳይ፡ ለጥቆ ደግሞ ከኦነግና ኦብነግ ጋር የሚደረገውን ውይይት ያመጣው ግንቦት ሰባት ነውና፡ ማምጣትም ብቻ አይደለም፡ የተወሰኑ የኦነግ አባላት የሚናገሩትን ሰባራ አረፍተ ነገሮች ይዞ፡ በግነት “ኦነግ የመገንጠል ሀሳቡን ጥሏል” ብሎ ለነገር ያሰፈሰፉትን በባዶ ሜዳ አስጮኋልና፡ መጀመሪያ ግንቦት ሰባትን ትንሽ ለኮፍ አደርገዋለሁ። ከዚያ ወደ ኦነግ እወርዳለሁ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ዘመኑ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1990 ላይ ነበር ። ለደርግ የአስተዳደርና የፖለቲካ ድህነት ምስጋን ይግባውና ሐገራችን ከገንጣይና አስገንጣይ ሀይሎች ጋር ታደርግ የነበረው ትንንቅ በኛ ሽንፈት ወደማክተሙ ሲቃረብ ፤ ዋናው ምክንያት የወያኔና የሻእቢያ ጦር ከኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ጀግናና ሐያል ሆኖ ሳይሆን ፤ የኢትዮጵያ ጦርሰራዊት በገጠመው የአመራርና የአስተዳደር ቀውስ የውጊያ ሞራሉ ሊጠገን በማይችል መልኩ ስለተጎዳና ውግያውን ስለተወው ፤ በሩ ሁሉ ለጠላት ክፍት ሆኖ በመገኘቱ ነበር ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሲሳይ አጌና
“አባባ ታምራት፣አርቲስቶቻችን እና የህዳሴው ግድብ”) በሚል ርዕስ ባለፈው ባቀርብኩት ጽሁፍ ላይ ያልተቋጨ እና በይደር የተውነው ነገር መኖሩ ዕውነት ነው፤በዚያ ጽሁፍ ላይ የሰዎቹ ስም ባለመጠቀሱ ቅር ያላቸው፣ልብ ወለድም የመሰላቸው አጋጥመውኛል፤በኤሌክትሮኒክስ የመልዕክት ሳጥኔ ውስጥ::እንከሳለን ያሉም ጽፈውልኛል ፤ክሱ ሄግ ይሁን ልደታ ባይታወቅም።እርቃን ዳንስ ቤት የተገኘው ሚንስትር ማነው? ኮተቤው ጠንቋይ ቤት የተገኘውስ ? የአባባ ታምራት ደንበኛ የነበሩትስ እነማን ናቸው.? ....ከባንክ ብድር ወስዶ በዕዳ ሲፈለግ ጫካ የገባውስ ማነው ?ዛሬስ የየትኛው ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ነው የሆነው? ኢህአዴግን ስትከዳ በኢሕአዴግ ማጋጣነቷ የተጋለጠባት ማነች? የሚሉት ጥያቄዎች በርክተቢመጡም ለሁሉም ምላሽ መስጠት ባለመቻሌ አዝናለሁ፤የቢዮንሴን ጫማ ያደረገላት ሰው ማንነት የብዙዎቹን ትኩረት መሳቡ ግን ያልጠበኩት ነበር።እስክንድር ነጋ - (አዲስ አበባ)
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሰሞኑን ተወጥረው ሰነባብተዋል፡፡ የመንግሥታቸው ወጪ ከገቢው መንጥቆ ማምለጡ አዲስ ዜና አይደለም፡፡ ትንሹ ቡሽ እንደ እ.ኤ.አ. በ2ዐዐዐ ዓ.ም ከክሊንተን ስልጣን ሲረከቡ፣ የአሜሪካ መንግሥት በካዝናው ትርፍ ገንዘብ ነበረው፡፡ ገቢው ከወጪው ይበልጥ ነበር፡፡ በ2ዐ1ዐ፣ ዓመታዊ የባጀት ጉድለቱ ከ1 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ሄዷል፡፡ በየዓመቱ የተጠራቀመው ጉድለትና ብድር ተደማምሮ ዘንድሮ ከ14 ትሪሊዮን ዶላር በላይ አሻቅቧል፡፡ ይሄ ነው ብሔራዊ ዕዳ ማለት፡፡ ሸክሙ አሜሪካን እያንገዳገዳት ነው፡፡
ከንጉሤ ጋማ
በአሁኑ ወቅት በአፍሪቃ ቀንድ አገሮች በሶማሊያ፣ በኬንያ፣ በጂቡቲና በኢትዮጵያ በ60 አመት ታሪክ ዉስጥ ያልታየ በአይነቱ አስከፊ የሆነ የድርቅ አደጋ ተከስቷል። በዚህም 4.5 ሚሊዮን በሚሆኑ ወገኖቻችን ላይ የሞት አደጋ አንዣቧል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
በዚህ ሳምንት የማካፍላችኹ ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 19 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ከሚታተመው መሰናዘሪያ ጋዜጣ ጋር ያደረግኹትን ቃለምልልስ ነው፡፡ በዋናነት የሚያጠነጥነው በፀረ ሽብር ሕጉና ባስከተለው የፍርሃት ድባብ ዙሪያ ነው፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...