ሁለት ፕሮፌሰሮች፡- ፍቅሬ ቶሎሳና ጌታቸው ኃይሌ

Prof. Getachew and Fikreፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በአንድ ሰኮንድ ውስጥ ስንት ነገሮች ስንት ሁኔታዎች ይታያሉ?፣ ስንት ድርጊቶች፣ ስንት ሥራዎች ይፈጸማሉ? ስንት ሰዎች ይሞታሉ? ስንት ሰዎች ይወለዳሉ? ... አንድ ሰኮንድ ባዘለው ጊዜ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች አሉ፤ በአንድ ደቂቃ ውስጥ ባለው ጊዜ ውስጥ ቢያንስ የስድሳ ሰኮንዶችን ያህል ጥያቄዎች ይፈለፈላሉ፤ በአንድ ሰዓት ውስጥ 60*60= 3600 እነዚህ ደግሞ በ24 ሰዓት ሲባዙ 86 400 ይሆናሉ፤ የሚሆኑትንና የሚደረጉትን ነገሮች ሁሉ መዝግቦ፣ የሚነገሩትን ነገሮች ሁሉ አጣርቶ ይዞ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፍ አለ ወይ? የትናንትናውን ሃያ አራት ሰዓት በዘርዝር ማስታወስ የሚችል አለ ወይ? ጊዜውና መሣሪያው ያላችሁ የሳምንቱን፣ የወሩን፣ የዓመቱን ሰኮንዶችና ያቀፉትንና ያዘሉትን ጉዳዮች አጣርታችሁ ለማወቅና "ተረቱንና ታሪኩን" ለመለየት ሞክሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለፀረ-ኢትዮጵያውያን ኃይሎች ሁሉ

ኢትዮጵያዊነት እንደ ኢያሪኮ ግምብ በጩሀት የሚፈርስ ሳይሆን በፅኑ አለት ላይ የተመሰረተ ታላቅና ሕያው ማንነት ነው!!

ፍቅር ለይኩን

ጽሑፌን በአንድ ገጠመኜን በማስቀደም ልጀምር። ነገሩ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበርንበት ጊዜ ነው። በ1990ዎቹ መጨረሻ ገደማ በአዲስ አበባ ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች በ6 ኪሎ በዋናው ግቢ አንድ ትልቅ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገው ነበር። የዚህ ለግማሽ ቀን የዘለቀ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ዋና ጥያቄ ደግሞ፣ "የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ ፊንፊኔ/አዲስ አበባ እንጂ አዳማ አይደለችም!" የሚል ነበር። ይህን ጥያቄያቸውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ሐላፊዎችና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ሰምተው ምላሽ እንዲሰጧቸው የጠየቁት ተማሪዎች ከግማሽ ቀን ቆይታ በኋላ የዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ፕሬዝዳንት ወደ ሰልፈኞቹ ተማሪዎች ታጅበው መጡ። ፕሬዝዳንቱም ጥያቄያቸው ምን እንደሆነ በአገሪቱ/በፌዴራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ በሆነው በአማርኛ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የሆኑትን ተማሪዎች በርጋታ ምን እንደሚፈልጉ ጠየቋቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያና አሜሪካ

ሙሉነህ እዩኤል

ኢትዮጵያና አሜሪካ ምን አገናኛቸው ትሉኝ ይሆናል። ነገሩ እንዲህ ነው፦ ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራም የሰባት አገሮች ዜጎች ወደ አሜሪካን አገር እንዳይገቡ እግድ ጥለው ነበር። ፕሬዝደንቱን ለዚህ ያነሳሳቸው እግዱ ከተጣለባቸው አገሮች የሚመጡ ዜጎች ለአሜሪካን ደህንነት የሚያሰጉ ሆነው ስላገኟቸው እንደሆነ ይናገራሉ፤ ብዙዎች ይህን ስጋት ባለመጋራት እገዳውን ቢቃወሙም። እገዳው ውሎ ሳያድር የዋሽንግተን ክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የተከበሩ ጀምስ ሮበርት በሰባቱ አገሮች ዜጎች ላይ የተጣለው የጉዞ እግድ በዋሽንግተን ክልል ብቻ ሳይሆን በአሜሪካን በሙሉ እንዳይተገበር የሚል ብይን ይሰጣሉ። የእግድ እግድ መሆኑ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጎሣ ፖለቲካና የኢሳት ፈተና

ESATአንተነህ መርዕድ

ከደርግ መውደቅ ማግስት የሕዝብን ብሶትና የዕለት ተዕለት ውሎውን የሚዳስሱ በርካታ ጋዜጦችና መጽሔቶችን ከዳር ዳር ባይዳረሱም በአዲስ አበባና በትልልቅ ከተሞች ሕዝቡ እየገዛና ከእጅ እጅ እየተቀባበለ በማንበብ ይከታተል ነበር። ወያኔዎች ገበናቸው እየተጋለጠ መግዛት እንደማይችሉ ሲገነዘቡ፤ ጋዜጠኞችን በማሰር፣ በማሰደድ፣ ብሎም በመግደል (አሰፋ ማሩና ተስፋዬ ታደሰን ሳንረሳ)፣ አዟሪዎችንም በመቀጥቀጥ የነፃ ሚድያን ህልውና እንዲያከትም አድርገዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታሪክን ምርኮኛ የማድረግ ዘመቻ

Prof. Haile Lareboዶ/ር ነብዩ ጋቢሳ

ከሰሞኑ የፖለቲካችን የስበት ማእከል ታሪክ እና የታሪክ ባለሙያዎች ሆነዋል። ዶ/ር ኃይሌ ላሬቦ የተባሉ የታሪክ ምሁር ከኢሳት ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ በሶሻል ሚዲያው ከፍተኛ አዋራ ማስነሳቱ ሳያንስ፣ የተዳፈኑ የመሰሉ ጉዳዮችንም በመቀስቀስ ላይ ይገኛል። በመጀመሪያ የዶክተሩን ቃለምልልስ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በጽሞና ለመከታተል ሞክሬአለሁ። በዚህም ተጠያቂውን ዶ/ር ኃይለማርያም ላሬቦ ከሙያም ሆነ ስነምግባር አንጻር የበቃ ችሎታቸውን ለመታዘብ ችያለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሚሰማው ጉድ ኢትዮጵያውያን እግዚኦ እንበል!

ነፃነት ዘለቀ

Prof. Haile Larebo

በስንቱ አፍረን እንደምንዘልቀው አሁንስ ግራ ገባኝ። ይሄኮ ከነፍስ ግድያ አይተናነስም።

ዐረቦች እንዲህ ይቀልዱብናል አሉ - ከተጨባጩ እውነት ስንነሳም በጣም ልክ ናቸው። እየጎመዘዘንና እየመረረንም ቢሆን ልንቀበለው ይገባል። የብዙዎቻችን ወቅታዊ ምግባር ገሃድ እያወጣብን የሚገኝን መጥፎ አድራጎት በማይበልጥ የታሪክ ድርሣንና በከንቱ ውዳሤ ልናድበሰብሰው ብንሞክር “ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ” እንደሚባለው ከመሆን አይዘልም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕ/ር ኃይሌ ላሬቦ እና "የቁቤው ትውልድ" ፖለቲካ

ክንፉ አሰፋ

Prof. Haile Larebo on ESAT

ለሰሞኑ ግርግር መንስኤ የሆኑት ፕ/ር ኃይሌ የተጠቀሟቸው ሁለት ቃላት ናቸው ተብሏል። "ጋላ" እና "እረኛ" የሚሉ ቃላት። በኢትዮጵያ የታሪክ መዛግብት ውስጥ እነዚህ ቃላት "ሰፍረዋል" ወይንስ "አልሰፈሩም" የሚለውን ጉዳይ ለግዜው እንተወው። ፕሮፌሰር ኃይሌ ላሬቦ በቃለ-መጠይቁ እነዚህን ቃላት መጠቀማቸው "ስህተት ነው" ወይንም "ስህተት አይደለም" ወደሚለው ትንታኔም አልገባም። እነዚህን ጥያቄዎች ለታሪክ ለተመራማሪዎቹ ልተውላቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጻዕረ ሞትና መስፍን ወልደማርያም

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

Mesfin Woldemariam

አንደኛ፣ ገና በልጅነቴ አሥር ዓመት ግድም ሲሆነኝ አንድ በድቀድቂት ከእንጦጦ ወደታች የሚወርድ ኢጣልያዊና እኔ ተጋጠምን፤ እሱ በዚያ በጥቁር ድንጋይ ኮረት በረበረበበት መንገድ ላይ ሲጓዝ ወደእንጦጦ የሚወጣ ወታደሮችን የጫነ ከባድ መኪና ቆሞ ነበር። በዚያ መኪና ላይ አንድ ዝንጀሮ ነበር፤ የኔ አትኩሮት በዚህ ዝንጀሮ ላይ ነበር። እንደሚመስለኝ ዝንጀሮውን እያየሁ ስሮጥ ከድቅድቂቱ ጋር ተገናኘን፤ እኔ ከስር በተረበረበው የጥቁር ድንጋይ ኮረት ላይ፣ ድቅድቂቱ ደግሞ የእኔን ራስ ጨፍልቆ! ምኒልክ ሐኪም ቤት ከስንት ቀኖች በኋላ የካቶሊክ መነኮሳት አስታማሚዎች ከነመለዮአቸው አልጋዬ አጠገብ ቆመው በትልቅ የበሽተኞች ድንኳን ውስጥ በአንዱ መደዳ ውስጥ ተኝቼ ነቃሁ፤ መድኃኔዓለም ማንን ልኮ የእኔን ጭንቅላት ከድንጋዩና ከድቅድቂቱ መክቶ እንዳዳነኝ አላውቅም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የነዶን ኪሾቶች አገር

ምሕረቱ ዘገዬ

Don Quixote

በወጣትነቴ ካነበብኳቸው ጥቂት መጻሕፍት አንዱ የሰርቫንቴስ ዶን ኪሾት ነው። ይህ ገጸ ባሕርይ - ዶን ኪሾት - በጣም አስቂኝ ነው። ምናቡ የሚፈጥርለትን የጠባብ ዓለም ሕይወት ለመኖር በደራሲው ምናብ የተፈጠረ የሌለውን እንዳለው፣ ያልሆነውን እንደሆነ በመቁጠር ከንፋስና ከበጎች ጋር ሳይቀር “የጦፈ ጦርነት” ውስጥ የሚገባ ገልቱ ሰው ነው። ከነባራዊው ዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተን ስናየው በምናብ ምሪት ለመኖር ማሰብ ትልቅ ዕብደት ነው። የልቦለዱ ግን ቀላል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ደቡብ ሱዳን ለኢትዮጵያ የጉርብትና ፈተና?

ጸጋ ንጉሴ

Hailemariam Desalegn and Salva Kiir Mayardit

ባሳለፍነው ሳምንት ከዚህ ቀደም እጅና ጓንት ሆነው ይታዩ የነበሩት ጎረቤታሞቹ ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ፍጥጫ ውስጥ ገብተው ሰንብተዋል።

የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳትን ሳልቫ ኪር በትጥቅ ትግል የተሰማሩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ቢሮዋቸውን በጁባ እንዲከፍቱ ፍላጎት አሳይተዋል የሚለው ዘገባ ከወጣ በኋላ፤ በሁለቱ አገራት መካከል ከፍተኛ የሆነ የዲፕሎማሲ ውጥረት ተፈጥሮ ነው ሳምንቱ የተገባደደው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ