የግንቦት ፖለቲካ

ተስፋዬ ገብረአብ

በዚህ በወርሃ ግንቦት ከጥቂት በላይ ጆሮ የሚጎትቱ ዜናዎች መስማታችን አልቀረም። የኦሮሚያ አመፅ በገጠር ከተሞች መቀጠሉ፣ የቦሌ አለማቀፍ አይሮፕላን ጣቢያን ስም ለመቀየር መታሰቡ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የስራ ፍለጋ ማመልከቻ ማስገባቱ፣ የህወሃት የፀጥታው መስሪያ ቤት ባልደረቦች በውስጥ ሽኩቻ መናጣቸው፣በርካታ የስርአቱ ደጋፊዎችና ቤተሰቦቻቸው ባለመረጋጋት ስሜት የሽሽት ጉዞ መጀመራቸው፣ የኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅቶች ተባብረው የኢትዮጵያን መንበረ ስልጣን እንዲረከቡ ግፊት በመደረግ ላይ መሆኑ እና ሌሎችም በወርሃ ግንቦት ከተሰሙ አበይት ዜናዎች መካከል ናቸው። አንዳንዶቹን ርእሰ ጉዳዮች በጨረፍታም ቢሆን ፈታ አድርጎ ማየቱ አስፈላጊ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔ ውድቀት የአደባባይ ምሥጢር መሆኑን የሚያመላክት አጋጣሚ

ማስተዋል በለጠ (ከአዲስ አበባ)

የወያኔ ውድቀት የአደባባይ ምሥጢር መሆኑን የሚያመላክት አጋጣሚ

ከደቂቃዎች በፊት ከአንዱ የመሥሪያ ቤቴ ቅርንጫፍ ወደ ዋናው መ/ቤት ስመጣ እንዲህ ሆነ። መኪናዋ ውስጥ በተላላኪነት የምትሠራ አንዲት ወጣት፣ ሹፌራችንና እኔ ብቻ ነን የነበርነው። የዛሬው ቀን የከተማችን ወሬ የሆነውን የማትሪክ ፈተና መሰረቅ አነሳሁና የተለጎመውን የሦስታችንንም አንደበት በጋራ የሀገር ጉዳይ ከፈትኩት። በዚህን ዓይነት ሁኔታ እኔ ብዙውን ጊዜ ነገር እለኩስና ዋና ሥራየ ማዳመጥ፣ ማዳነቅና ማውጣጣት ነው። ቀዳሚው ሥራየ ግን የማዋራቸው ሰዎች በኔ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ጥረት ማድረግ ነው፤ ሰው ከተጠራጠረህ የልቡን አይናገርም። ዝም ሊል ወይም ሊዋሽህና ሊያታልልህም ይችላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በእርስ በርስ ጦርነት ድል ሃያ አምስት ዓመት ፉከራ

ይገረም አለሙ

Ginbot 20, 25th anv. ግንቦት 20፣ 25ኛ ዓመት

በእርስ በርስ ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሚሞተው የአንድ ሀገር ልጅ ነው። አባትና ልጅ፤ ወንድምና ወንድም ከዛና ከዚህ ተሰልፈው የሚገዳደሉበት አጋጣሚም ይኖራል። ይህም በ17 ዓመቱ የርስ በርስ ጦርነት በግልጽ ታይቷል። ወያኔዎች ለድል የበቁት የኢትዮጵያን ሠራዊት ብቻ ሳይሆን ደርግን ተቃውመው ብረት ያነሱ፤ ነገር ግን ከዋሉ ካደሩ ለህወሓት ህልውና አስጊ ይሆናሉ ያሉዋቸውን ድርጅቶች ጭምር (ለምሳሌም ኢህአፓ፣ ኢዲዩ፣ …) ተዋግተው፤ ከዚህም አልፎ በህወሓትም ውስጥ የተለየ አስተሳሰብ ያራመዱ ወይንም ለሥልጣን ያሰጋሉ የተባሉትን እያሰቃዩና እየገደሉ በመሆኑ፤ መገዳደሉ በአንድ ሀገር ልጆች መካከል ከመሆን አልፎ በቤተሰብ መካከል ጭምር እንደነበር አሌ አይባልም። ለዚህ ደግሞ ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ በኢህአፓነቱ በወያኔ እንደተገደለ የሚነገረውን የአቶ በረከት ስምኦን ወንድም መጥቀስ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እንባዬን ጨርሼ፣ ደም እንደ እንባ አነባሁ

ሄኖክ የሺጥላ

ስደት

ወዳጄ እና ጓደኛዬ በቅርቡ በሱዳን አሳብሮ፣ በሊቢያ በረሃ አቋርጦ፣ በባህር አሳልጦ ጣሊያን፣ ከጣሊያን ደሞ ጀርመን እንደደረሰ አጫወተኝ። እርግጥ የተጓዘው መንገድ፣ ያየው መከራ፣ የቀመሰው ችግር እንዲህ በሁለት መስመር በሱዳን አድርጎ በሊቢያ አቋርጦ ጣሊያን ደረሰ ብሎ እንደማለት ቀላል አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግንቦት 20 እንዲህ መቀለጃ ሆና ትቅር?

ግንቦት 20 እንዲህ መቀለጃ ሆና ትቅር?ታዛቢ (ከአዲስ አበባ)

ሥራየ መምህርነት ነው። በአንድ የመንግሥት የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ውስጥ አስተምራለሁ። ሰሞኑን ታዲያ የግንቦት 20 የኢትዮጵያ የነፃነት ቀን እንደመሆኑ የበዓሉን መቃረብ አስታክኬ በየምገባባቸው በርካታ ክፍሎች ትምህርቱን ከመጀመሬ በፊት “እንኳን አደረሳችሁ” እላለሁ። ይሀንን የምለው ኢህአዲግ መራሹ ዴሞክራሲያዊው መንግሥታችን ጨቋኙን የደርግ መንግሥት ደምስሶ ህዝባዊ መሠረት የተላበሰና በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የቆመ የዴሞክራሲ ሥርዓት በመትከሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መቶ ሚሊዮን ህዝብ ያላት የሰው ድሃ ሀገር ኢትዮጵያ

Ethiopiaይገረም ዓለሙ

በ1982 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ አይደለም የት ላይ እንዳለች አንኳን መናገር በማይቻልበት ወቅት፤ ከአንድ ባልንጀራየ ጋር እየሄድን፤ እኔ ከማላውቀው የእርሱ ጓደኛ ጋር መንገድ አገናኘን። እናም ሠላምታ ተለዋውጠው፤ ታዲያስ እንዴት ነህ፣ እንዴት ናችሁ ሲለው፤ ምን እባክህ ሰውም አለን ሰውም የለንም ሲል መለሰለት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦዴጎች ምን ነካቸው?

ግርማ ካሳ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኦዴግ). Oromo Democratic Front (ODF)

አንዳንድ በተለይም በውጭ ያሉ የኦሮሞ ብሔረተኞች፣ የአክራሪውን እና የብዙ ወገኖች ደም በእጁ ያለበትን የኦነግን ባንዲራ እያውለበለቡ፣ የጭቁን ኦሮሞ ወገኖቻችንን ተቃውሞ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እና እንቅስቃሴውን ሃይጃክ በማድረግ፣ የኦሮሚያ ሪፑብሊክን ለመመስረት ያላቸውን ሕልም ለመተግበር ደፋ ቀና እያሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፍቅርና ክብር ለዚህ ነጻነትና ክብር ላበቁን ጀግኖች አርበኞቻችን!

በፍቅር ለይኩን*

Ethiopian patriots. ጀግኖች አርበኞቻችን

"... When he saw a poster, Mussolini Invades Ethiopia, he was immediately seized by a violent emotion. At the moment, he writes, it was almost as if the whole of London had suddenly declared war on me personally. For the next few minutes I could do nothing but glare at each impassive faces, wondering if these people could realize that wickedness of colonialism, and praying that the day might come when I could play my part in bringing about the downfall of such a system. … I was ready to go through hell itself, if need be, in order to achieve my object."

ዕውቁ ፓን አፍሪካኒስትና የ"ጋና የነጻነት አባት" በሚል ቅጽል የሚጠራው ዶ/ር ክዋሜ ንኩርማ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ በሚያደርገው ጉዞው በለንደን ከተማ ባደረገው አጭር ጊዜ ቆይታ ያስተዋለው፣ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ምልክት፣ የጥቁር ሕዝብ ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ቅርስና ማንነት መገለጫ፣ የነጻነት የተስፋ ምድር- ከነዓን ተደርጋ የምትቆጠረው ኢትዮጵያ በፋሽስት ኢጣሊያ በግፍ የመወረር አስደንጋጭ ዜና፣ መርዶ በውስጡ ያሳደረበትን ስሜትና ቁጭት "ጋና" በሚል ርዕስ በጻፈው የሕይወት ታሪኩ መጽሐፍ ያሰፈረውን በጥቂቱ የቀነጨብኩት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምሥራች! ትግርኛና አማርኛም በላቲን ፊደል ሊጻፉ ነው

ይሄይስ አእምሮ

Tigrinya. ትግርኛ

መምህር ልዑለቃል አካሉ የተባሉ ኢትዮጵያዊ በቅርቡ በኦሮምኛ ቋንቋ የላቲን ፊደል አጠቃቀም ዙሪያ የጻፉትን መጣጥፍ ቆየት ብዬም ቢሆን ዛሬ አነበብኩት፤ ግሩም ነው። እሳቸው የሚሉት “ለኦሮምኛው ከላቲን ይልቅ የግዕዙ ፊደል አይቀርብም ወይ?” ነው። ይሄን ያህል ለምን ሩቅ ተሄደ ነው ጥያቄያቸው። ላቲኑን ለመጠቀም ለምን ያን ያህል ሩቅ መንገድ መጓዝ እንዳስፈለገም መልሱ በመጣጥፉ ውስጥ አለ - ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች በወያኔ በመታገዝ ሀገሪቱን ለመበታተን ከሸረቡት ሤራ አንዱ መሆኑ በስፋት ተጠቅሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከኢትዮጵያውያን ቋንቋዎች አንዱ የሆነው ኦሮምኛ ቋንቋ መጻፍ ያለበት በግዕዝ ፊደል ወይስ በላቲን ፊደል?

ከኢትዮጵያዊ ማንነት አንጻር ለውይይት መነሻ እንዲሆን የቀረበ ጽሁፍ

መምህር ልዑለቃል አካሉ (ሲያትል፣ ዋሽንግተን)

መግቢያ

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፈ ቅዳሴዋን ወደ ኦሮምኛ ቋንቋ ተርጕማ አሳትማለች። መሆን ያለበትና መደረግም የነበረበት ነው። በምርቃቱ መርሐ ግብርም የቀድሞውን ፕሬዝደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ ብዙ እንግዶች ተገኝተው እንደ ነበር ታውቋል። ይሁን እንጂ ከግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በቀር የላቲንን ፊደል በቅዳሴው ላይ መጠቀሟ ትክክል አለመሆኑን ያስታወሰ እና ለወደፊትም ቤተ ክርስቲያን እንድታስብበት የጠየቀ የለም ተብሎአል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ