ስደት የፍርሃት ውጤት ነው

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

Bewketu Seyoum and Yared Tibebu በእውቀቱ ሥዩም እና ያሬድ ጥበቡ

ከሁለት ቀኖች በፊት ስለበእውቀቱ ሥዩም አድናቆታቸውን በፌስቡክ ላይ የገለጹ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ለበእውቀቱ ያላቸውን አድናቆት እኔም እጋራቸዋለሁ፤ ነገር ግን የእነዚህ ሰዎች አድናቆት በእውቀቱ ራሱንና ማንነቱን እንዲከዳ ይቃጣቸዋል። አንዱን አውቀዋለሁ፤ ከፖሊቲካና ከትጥቅ ትግል ወደስደት ”ነጻነት” የተሸጋገረ ያሬድ ጥበቡ የሚል የሚያኮራ ስም ይዞ የስደት መምህር የሆነ ነው፤ ሁለተኛው ሚስተር ቴዲ ገብርኤል ይባላል። እነዚህ ሁለት ስደተኞች በእውቀቱ ሥዩምን በጣም ስለሚወድዱትና ስለሚያከብሩት በአሜሪካ ስደተኛ ሆኖ እንዲቀርላቸው ይፈልጋሉ፤ በዚህ ብቻ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ስሜት መገመት በጣም የሚያሳዝን ነው፤ ወደዝርዝር አልገባም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ህወሓት እንዴት ሰነበተ?

ተስፋዬ ገብረአብ

የህወሓትን የጓዳ ወግ ማወቅ አስቸጋሪ የነበረበት ዘመን እንደዋዛ አልፎአል። ዛሬ ቀዳዳቸው በዝቶ፤ ቴክኖሎጂውም አግዞ የፈፀሙት ብቻ ሳይሆን ያሰቡትም በቀላሉ ይገኛል። ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነው። መረጃ ከሌለ ምንም ነገር የለም። ለችግሮች መፍትሄም አይገኝም። ወያኔ ዛሬ በአስር ሺዎች ኦሮሞዎችን በገፍ የሚያስረው ስለ ቄሮ በቂ መረጃ ስለሌለው መሆኑ ይታወቃል። ተቃዋሚ የፖለቲካ ተንታኞች ወይም የማህበራዊ ድረገፅ ፀሐፊዎች አንዳንድ ጊዜ አስቂኝ ስህተት ይሰራሉ። ማለትም ሳያውቁ ለወያኔ የሚጠቅም መረጃና ምክር ይፅፋሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዐይናችን ተከፍቷል ህሊናችን ነቅቷል

Students killed by federal police. የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተገደሉ፣ ተደበደቡአንተነህ መርዕድ

የመጀመሪያው የኬንያ ፕሬዝደንትና የነፃነት ታጋይ ጆሞ ኬንያታ ብዙ ጊዜ የሚጠቀስላቸው፣ ስለቅኝ ገዥዎች የተናገሩት እውነት ይህን ይመስል ነበር። “ሚሲዮኖች ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መጽሐፍ ቅዱስ፤ እኛ ደግሞ መሬት ነበረን። ዐይናችንን ጨፍነን እንዴት እንደምንጸልይ አስተማሩን። ዐይናችንን ስንገልጠው ግን እነሱ መሬታችንን እኛ መጽሐፍ ቅዱሱን ታቅፈናል” አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ሒደት ነው”

ሩት አማኑኤል

ተደጋግሞ የሚነገር አንድ ጉዳይ አለ። ዴሞክራሲ ሒደት ነው፤ መልካም አስተዳደር በሒደት የሚመጣ ነገር ነው፤ የዴሞክራሲ ተቋማትን መገንባት ሒደት ነው ወዘተ. ይባላል። ለጽሑፌ መነሻ የሆነኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለችጋር

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

• ችጋር ምንድን ነው? ሰፊ ቦታንና ብዙ ሕዝብን የሚሸፍን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ እንስሳት (ሰውንም ጨምሮ) ዕለት በዕለት የራሳቸውን አካል እስኪያልቅ ድረስ "እየበሉ" በመጨረሻም የሚሞቱበት ሁኔታ ነው፤ ረሀብ አካል ሲዳከም አካልን ለመገንባት የሚደረግ ጥሪ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንጀት የሚበሉ ጠቅላይ ሚኒስትር!

PM Hailemariam Desalegn. ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝሩት አማኑኤል

ሕዝብ አዋቂ ነው። የፖለቲካ ሶሲዮሎጂስቷ ቴዳ ስኮፖል በሚያሳምን ሁኔታ እንደገለጸችውና በአገራችን በተግባር እንደሚታየው ሕዝብ ዝም ቢልም አፈናን ተቀብሏል ማለት አይደለም። በአፈና ውስጥ ያለ ሕዝብ ዝም ሲል እንድም ብናገርም ለውጥ አላመጣም ማለቱ ነው፤ አንድም ማኩረፉንና መከፋቱን መግለጹ ነው፤ አንድም የተመቻቸ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ አድብቶ መጠበቁ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከመጠምጠም መማር ይቅደም

Prof. Mesfin Woldemariam ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በፌስቡክ የምንሰባሰበው ለመወያየት፣ አንዱ ከሌላው እንዲማር፣ መረጃዎችን በነጻነት እንድንለዋወጥ፣ ይህንን ሁሉ በማድረግ ራሳችንን ለማሻሻል፣ የእኛ መሻሻል እየተራባና እየተባዛ የአገርና የሕዝብ መሻሻል እንዲሆን፣ ከተቻለንም ከአገራችንና ከሕዝባችን አልፈን የምንታይ የዓለም አካል እንድንሆን መስሎኝ ነበር፤ ሳየው በዚያ መንገድ ላይ ያለንና ፌስቡክን ለበጎ ዓላማ እየተጠቀምንበት ያለን አይመስለኝም፤ ስለዚህ ወይ መታረም፣ አለዚያም በፌስቢክ ጊዜ ማጥፋቱን መተው ምርጫ ሊሆንብን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ እና የዓለም ባንክ ቅጥፈቶች፣ እርባናቢስ ውሸቶች እና የሀሰት የቁጥር ቁማር ጨዋታዎች፣

Ethiopia and the World Bank of Lies, Damned Lies and Statislies, by Prof. Almariamፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

ጆን ሚልተን ገነትን ማጣት/Paradise Lost በሚለው መጽሀፋቸው “የቱም ዓይነት ቅጥፈት ቢሆን ዘለቄታዊነት የለውም የሰማይ ቁጣንም ይስባል።” በማለት ጽፈዋል። በእርግጥ ሚልተን ሊጨበጥ ሊዳሰስ ስለማይችለው ባዶ ምናብ ስለሚፈጥረው ስለሰይጣን እና ስለዕኩይ ምግባሩ ነበር የጻፉት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም?

Prof. Getatchew Haile ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ

መግቢያ፤

መጀመሪያ ለመግቢያ ያህል፥ “ዘመድ” የሚለውን ቃል እንዴትና ለምን እንደተጠቀምኩበት ላስረዳ። “ዘመድ” ማለት “ወገን” ማለት ነው። በእንግሊዝኛ “kin, family, tribe” ማለት ነው። በየሊቃቸው የሚመሩ የተለያዩ የመላእክት ሠራዊት “ዘመድ” ወይም “ነገድ” ነው የሚባሉት”--ዘመደ መላእክት፣ ነገደ መላእክት። ሌሎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው መጠሪያዎች “ቤት” (ቤተ አምሐራ)፣ “ጎሳ” (የጉጂ ጎሳ)፣ “ዘር” ናቸው። ዛሬ ደግሞ “ብሔረ ሰብ” የሚለው መጠሪያ ነግሧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንተም ደመቀ መኮንን!

አንተነህ መርዕድ

ይድረስ ለማውቅህና ለማታውቀኝ የኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

የኢትዮጵያ ህዝብ እስከአሁን መሪዎቹን መርጦ አያውቅም። ሁሉም በጉልበት ትክሻው ላይ ተፈራርቀው ወጥተውበታል፤ እየተካኩም አሁን ላለበት ከዓለም የመጨረሻነትና የርሃብ ተምሳሌትነት አድርሰውታል፤ አድርሳችሁታል። ያለፈ ታሪክ እየቆፈርን ማን ምን ሠራ እያሉ ለመዘባነን በአሁኑ ወቅት ህሊና ላለው አንገብጋቢ ጥያቄ አይመስለኝም። በእጃችን ላይ ያለውን ዐይኑን አፍጥጦ የመጣውንና የብዙ ሺዎችን ህይወት ለመቅጠፍ “ሀ’’ ብሎ የጀመረውን ርሃብ ለመግታት ደመኛ ጠላቶችም ቢሆኑ የሚተባበሩበት ወቅት ነውና። ከየትም ወገን ይምጣ ርሃብን ለፖለቲካ ፍጆታ የመጠቀምን ያህል ጭካኔ ከቶ የለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ