ትግላችንን እንመርምር

አንዱዓለም ተፈራ

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ፤ “ትግላችን ወደፊት የሚሄደውና ለድል የሚበቃው፤ ሀገራዊ ራዕይ ይዘን፤ በአንድነት ስንሰለፍና ለአንድ ግብ ስንታገል ብቻ ነው!” በማለት አስፈላጊውን ውይይት ለማበረታታት ጽሑፎችን አቅርቤ ነበር። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ፤ አሁን ያለንበትን በመመርመር፤ ወደፊት ለመሄድ፤ አሁንም ወሳኝ የሆነው፤ በአንድነት መነሳታችን መሆኑን አሰምርበታለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምንወድሽ ሀገራችን ደግመሽ አልቅሽ!

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም:- ነጻነት ለሀገሬ)

የኢትዮጵያውያን/ት ህይወት ያሳስበናል!

እ.ኤ.አ. በ2005 ልክ የዛሬ 10 ዓመት በያዝነው ወር ገደማ አሁን በህይወት የሌለው እና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አድራጊ ፈጣሪ አምባገነን መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ በዚያን ዓመት ተካሂዶ የነበረውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ሁከት የደህንነት እና የጦር ኃይሉን በእራሱ ቁጥጥር ስር በማዋል በሰላማዊ እና ባልታጠቁ ንጹሀን ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እልቂት እና መከራን ያዘለ ዘመቻ አካሂዷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አደራጅተው ገደሉን፤ ተደራጅተን ብንገድልስ?

አብርሃም ዘታዬ
ፌዴራል ፖሊስ በሊቢያ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያኖች አስመልክቶ ለኀዘን የወጡትን ሲደበድብ

በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ ከደረሰብን ኀዘን ሳናገግም በሜዲትራንያን ባህር የሰጠሙ ወገኖቻችንን መርዶ ተረዳን። በአገር ቤት ከድሮም ጀምሮ በተናጥልም በጅምላም መጨፍጨፋችን አላቆመም። ባለቅኔው "ሞትና የላሊበላ ህንጻ ሁልጊዜ አዲስ ነው" ብሎ እንደተቀኘው ስለአዲሱ አሟሟታችን እንጉርጉሮ እናውጣለት ከተባለ በሰፈር ተደራጅተን እየሞትን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በመጨረሻም በግብጽ ነጻ ወጡ፣ እኛ ግን መንግሥት አለን እንዴ?

ክንፉ አሰፋ
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከሊብያ የተመለሱትን ኢትዮጵያውያኖች ሲቀበሉ

የፌስቡክ አርበኛው ቴድሮስ አድሃኖም ቦሌ ሄደው ከሊቢያ ነጻ የወጡ ዜጎችን ሲቀበሉ አየን። እፊታቸው ላይ የማፈር ሳይሆን የጀግንነት ስሜት ይነበባል። አቀባበላቸውም 90 ደቂቃ በኢንቴቤ የሚለውን ታሪክ ይመስላል። ኡጋንዳ ላይ የታገቱ ዜጎችዋን ለማስለቀቅ እስራኤል ያደረገችው ገድል። ቴድሮስ አድሃኖምም በኩራት እና በድል አድራጊነት ስሜት ነው ስደተኞቹን የተቀበሉት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አሜሪካ አይሲስን ለምን ፈጠረችው?

ክንፉ አሰፋ

Obama Stop ISIS

ግብጽ የሃያ አንድ ክርስቲያን ዜጎችዋን በአይሲስ መታረድ ዜና እንደሰማች ዝም ብላ አልተቀመጠችም ነበር። ብሔራዊ የኀዘን ቀንም አላወጀችም። እንዲህ ነበር የሆነው። ከመቅጽበት ተዋጊ አውሮፕላኖችዋን አስነስታ ወደ ሊቢያ ላከቻቸው። የአይሲስ አራጆች የተከማቹበትን ደርና የተሰኘ ስፍራ እያከታተለች በቦምብ ቀጠቀጠችው። ብዙ አራጆች በድብደባው አለቁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምሥጋና ለሾባት ፋውንዴሽን

ወልደማርያም ዘገዬ (አዲስ አበባ)

“Shoebat Foundation” የሚባል ክርስቲያኖች በአክራሪ ሙስሊሞች የሚደርስባቸውን ጥቃት እየተከታተለ የሚያጋልጥና ለመታደግም አቅሙ በፈቀደ የሚታገል ድርጅት አለ። የተቋቋመው ቀድሞ ሙስሊም በነበረና እምነቱን ወደ ክርስትና ኃይማኖት በለወጠ ሰው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የልቅሶና የዋይታ ድምፅ በደቡብ አፍሪካ፣ በየመን፣ በሊቢያ ምድር ተሰማ

Ethiopias tear. እናት ኢትዮጵያም ስለ ልጆቿ አለቀሰች የሉምናእናት ኢትዮጵያም ስለልጆቿ አለቀሰች የሉምና!!

ዲ/ን ተረፈ ወርቁ

”... ዓይኔ በእንባ ደከመ፣ አንጀቴም ታወከ። ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ አንጀቴ በምድር ላይ ተዘረገፈ። አቤቱ የሆነብንን አስብ፣ ተመልከት ስድባችንንም እይ ...።” ሰቆ. ፪፣፲፩ ፤ ፭፣፩።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጨለማው ሣምንት

ክንፉ አሰፋ

Eyassu Yukunualem and Balecha Belete, ISIS massacred them in Libya. የአይሲስ ሰለባዎቹ እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ

ወጣት እየሩሳሌም አስፋው እንደወትሮው ቴሌቭዥን ከፍታ እየተመለከተች ነው። ብርቱካንማ ቱታ የለበሱና፣ እጆቻቸው የፍጢኝ የታሰሩ ወጣቶች በአሸባሪዎች ታጅበው ሲጓዙ ያሳያል ቴሌቭዥኑ። ለእርድ ከተሰለፉት ወገኖች ፊት ለፊት ላይ ያለው የእየሩሳሌም ወንድም ነበር። ሌላኛው ወንድሟም ከበስተኋላ ተሰልፏል። እያሱ ይኩኑዓምላክ እና ባልቻ በለጠ፤ ሁለቱም በዚያች ቅጽበት ክቡር ነብሳቸውን በግፈኞች ተነጠቁ። ከሁሉም የከፋ የሚያደርገው ደግሞ ወዳጅ ዘመዶች የነዚህን ወገኖች አስከሬን አግኝተው ለመቅበር እድል እንኳን ባለማግኘታቸው ነው። የሁሉንም ልብ የሚሰብር ክስተት!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር

Senakriem Mekonnen. ሰናክሬም መኮንንክንፉ አሰፋ

"አሜሪካ ይዞን ከሄደ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ውስጥ ጥሎን ጠፋ ... ፖሊስ ሁለት ግዜ ይዞን ነበር ... በርሃብ ተቀጣን፣ ርሃብ ጸንቶበት ሆስፒታል የገባም ልጅ አለ። ... በየሬስቶራንቱ እየዞርን ለምነናል።" ይላል አንድ የ11 ዓመት ሕጻን ሳይንቲስት። ሂውስተን ቴክሳስ ያሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ሄደው ነው አስሩ ሕጻናት ዲሲ ላይ የሚሰቃዩት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መማር እንችላለን ወይ?

አንዱዓለም ተፈራ

Revolution. መማር እንችላለን ወይ?

ከ፲፱፻፷፮ ዓመተ ምህረቱ የየካቲት ሕዝባዊ መነሳሳት ጀምሮ፤ ለመብት፣ ለነፃነትና በሰላም ሠርቶ ለመኖር ያለው ትግል፤ ሳያርፍ በተከታታይ አሁንም እየተካሄደ ነው። በነዚህ ባለፉት ፵ ዓመታት፤ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፤ በትግሉ ከሕዝብ ጎን ተሰልፈው ሕይወታቸውን ሠጥተዋል። ቆራጥ የሕዝብ ጠበቃዎች ወጥተዋል፤ ሕይወታቸውን ላመኑበት ዓላማ በቆራጥነት በመሥጠት በጀግንነት ተቆጥረዋል። ትውልድ አልፎ ትውልድ ተተክቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ