ኢትዮጵያ የፖሊስ መንግሥት ያንሰራፋባት ሀገር

Prof. Al Mariam ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፦ ነጻነት ለሀገሬ)
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገመንግሥት በሕግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ዜጎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን መብቶች ያጎናጽፋል። "በሕግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ሰው በሕግ አግባብ መብቱ ተጠብቆ ይያዛል። ማንኛውም ሰው በሀሰት ለመረጃ ጠቀሜታ ተብሎ በማስገደድ እንዲያምን ወይም የተባለውን እንዲቀበል አይገደድም። ማንኛውም በማስገደድ የተገኘ መረጃ ተቀባይነት አይኖረውም።" ይላል አንቀጽ 19(2)(5)። እውነታው ሲታይ ግን ይህ የይስሙላ ሙበት የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያህል የለውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሁለት ኢትዮጵያውያን ሁለት አንቀጽ ወግ እና እኔ

ዳዊት ከበደ እና ተስፋሁን ጫመዳ Dawit Kebede and Tesfahun Chemedaአቤ ቶኪቻው

ዳዊት ከበደ እና ተስፋሁን ጫመዳ

ተስፋሁን ጫመዳ የተባለ አንድ ወጣት ኢትዮጵያዊ ነበር። የገዢው ግንባር ኢህአዴግ ነገረ ሥራ አልመችህ ቢለው በተለያየ አጋጣሚ "ተው!" ማለት ጀመረ። ኢህአዴግዬ ግን ተው ባይ አይወድምና በክፉ ዓይኑ ተመለከተው። ይሄኔ ተስፋሁን የሚመጣበትን ጦስ ሸሽቶ መጪው ጊዜ መልካም እንደሚሆን ተስፋ አድርጎ 'እስኪያልፍ ያለፋል' ብሎ ሀገሩን ትቶ ተሰደደ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ንጉሠ ነገሥት አብርሃም ያዬህ ሆይ! መፍትሔው ይሄው ነው በቃ?

ይሄይስ አእምሮ

"የአፄ አብርሃም ያዬህን ጽሑፍ አንብበን ስንጨረስ ነገር ማብላላታችንን ትተን ዝም ብለን መጋደም አልቻልንም። ዘመናችን ብዙ የሚሠራበት ሣይሆን ብዙ የሚወራበትና የሚጻፍበት መሆኑን እናውቃለንና አግራሞታችን ወሰን አልነበረውም። ጥሎብን "ሌላ ሥራ የላቸውም ወይ?" እስክንባል ድረስ በዬቀኑ ብዙ እናነ(ብ)ባለን፤ ስለዚህም ሲሆን በምታዘበው ሁሉ እናነባለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሁሉም ይናገር ሁሉም ይደመጥ!! (ከአንተነህ መርዕድ እምሩ)

በድሮ አጠራሩ ሻንቅላ በአሁኑ የጉሙዝ ብሄረሰብ የተማርሁት ትልቅ ነገር አለ።በትልቆች ጉዳይ ምን ጥልቅ አደረገህእየተባልሁ በሚያሸማቅቅ ባህል አድጌ በጉሙዝ ህብረተሰብ ህፃናት ታላላቆቹ ጋር ያለምንም ተፅዕኖ ሲወያዩ መመልከት አስደንግጦኝ ነበር። በጨዋታ መሃልግሰምእንግሻባኒያ” (እኔንም በተራዬ አድምጡኝ) ካለ አንድ ሰው ልጅንም ቢሆን ፀጥ ብሎ ማዳመጥና ማስጨረስ የተለመደ ክቡር ባህላቸው ነው።

(ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

 

 

 

 

አደባባዩ ምን ያህል ይርቃል?

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ - ከአዲስ አባባ

እነሆ ይቺ ገር ኢትዮጵያ ናትና የመብት (የለውጥ) ጥያቄዎች፣ እንደ አህጉር ተጋሪዎቿ ሁሉ መልስ የሚያገኙት ከአደባባይ ጩኸት ብቻ ይሆን ዘንድ ባህል ሆኖአል፡፡ ትውልድ ተሻጋሪ ታሪኳም የሚነግርህ በየወቅቱ ከተፈራረቁ ገዥዎቿ አንዳቸውም እንኳ ለህዝብ ፍላጎትና ውሳኔ ተገዝተው አለማወቃቸውን ነው፤ ጠመንጃ አሊያም ተፈጥሮ ወደ ግብአተ መሬት ካልሸኛቸው በቀር

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአፍሪካ ውስጥ በቅዠት የሚባንኑት እነማን ይሆኑ?

Prof. Al Mariam ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
ታላላቅ የአፍሪካ መሪዎች ህልም አላቸው፤ ቀሪዎቹ በቅዠት የተሞሉ ናቸው።

በቅርቡ የአፍሪካ መሪዎች ቢያንስ በአፍሪካ ህብረት ስልጣን ያላቸውና የእነርሱ ጋሻ ጃግሬዎች ስለህግ ልዕልና፣ ስለዘር ማደን (ማሳደድ) የማያቋርጡ አስደንጋጭ የቅዠት ሪፖርቶች በገፍ እያቀረቡ ነው። ቅዠታቸውም የፍትህ ጎራዴ ስያሳድዳቸው በላብ ተጠምቀው ከእንቅልፍ ይነቃሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሌባ ተይዞ ዱላ ይጠየቃል? በሆላንድ

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም Prof. Mesfin Woldemariamፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በአሥራ አምስተኛው ምዕተ-ዓመት ግድም ሆላንድ የታወቀ የባሕር ኃይል ሆኖ ከደቡብ አፍሪካ እስከደቡብ አሜሪካ፣ የኔዘርላንድ የቆዳ ስፋት 41 526 ኪ.ሜ. ካሬ ወይም የትግራይ ግማሽ ነው፤ የሕዝቡም ቁጥር አሥራ ስድስት ሚልዮን ተኩል አይሞላም። የትግራይን ግማሽ በሚሆን መሬት ላይ የትግራይን ሦስት እጥፍ ግድም የሚያህሉ ሰዎች ይኖሩበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትርፍ ሰዓት ትግል

ወ/ሮ አዜብ መስፍን Azeb Mesfinኢዮብ ይስኃቅ

ከዕለታት አንድ ቀን ባልተለመደ ድፍረት የሙስና ኮሚሽን ሰይፉን ትላልቅ የወያኔ ባለሥልጣናት ላይ አሳረፈ። እንደመድኃኒት ብልቃጥ እዚህም እዚያም ተወሽቆ የነበረ ብርና ንብረት እያስቆጠረ ወንጀለኞቹን ዋስ እየከለከለ ወደ ወህኒ ወረወረ። ሚኒስትሮች ከቦታቸው ተፈናቀሉ፤ የሙስና እናት የሚለውን ሜዳሊያ ያጠለቀችው ወ/ሮ አዜብ ከኤፈርት ተባረረች። ያዲሳባ ከንቲባነትም ሱሚ ነው ተባለች። ከሁለት ብቻ ሳይሆን ከብዙ ያጣች ሆነች። ህዝቡ እልል ለማለት ቢፈልግም ወያኔን ስላላመነ መጨረሻውን ለማየት መጠባበቅ ያዘ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ