ከኤርትራ መንግሥትና ህዝብ ጋር የሚደረግ ግንኙነትና ትብብር ለምን?

አቶ አብርሃም ያየህ Abraham Yayehውይይት ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ
ክፍል ሁለት፣ ምዕራፍ ሁለት
አብርሃም ያየህ

"አቶ ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎች የህዝባዊ ግንባር ለፍትህና ለዲሞክራሲ መሪዎች በሁለቱ ሀገሮች [ኢትዮጵያና ኤርትራ] መካከል ያለው ወሰን ትርጉም የሌለው በመሆን ላይ ነው እስከማለት ደርሰው ነበር። ጥቂት የግንባሩ ከፍተኛ ካድሬዎች በመጨረሻ ኤርትራና ኢትዮጵያ በፌደሬሽን መሰረት ላይ የሚተባበሩበት [የሚተሳሰሩበት] ሁኔታ እስከሚፈጠር ድረስ የውህደትና የኮንፌደሬሽን መዋቅሮች እየተጠናከሩ መራመድ እንደሚኖራቸው ሃሳብ ሰጥተዋል"

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ውይይት ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ (፪)

አብርሃም ያየህ (ክፍል ሁለት)
ላንዳንድ ሰዎች፣ ወይንም ለበርካታ ሰዎች ማለት ይቻላል፣ ሀገር ማለት ጮማ የሚቆርጡበት፣ ጠጅ የሚጋቱበት፣ ለሽርሽር የሚሄዱበት፣ ወንዙን ተራራውን እየጠሩ በግጥምና በስድንባብ የሚመፃደቁበት፣ የሚጨፍሩበትና የሚዘሉበት፣ ወዘተ ብቻ ይመስላቸዋል። በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው ደግሞ፤ ሌላው የፖለቲካ ሱስ ያለበት ይመስል፣ ከፖለቲካ ገለልተኛ ነኝ፣ ፖለቲካ አልወድም፣ ኃይማኖተኛ ነኝ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ዋጋ የለውም ወዘተ. የሚሉ ጉዶች አሉ። አንዳንዶቹማ፣ መታገሉንና ላገር መቆርቆሩ ቀርቶ፤ ነብሳቸውን ሽጠው ከሚታገሉ ሰዎች ጋር ላለመታየት እንኳ ሲንጰረጰሩ ማየት ትውልዱ ምን ያህል እንደከሰረ የሚያመለክት ነው። ይቺን አጋጣሚ ተጠቅሜ፣ ባለፈው ዓመት እዚህ ከምኖርበት ዴንማርክ ያጋጠምኝን አብነታዊ ክስተት ላካፍል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያለም አቀፉ ወጀል ፍርድ ቤት ምስክር

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
የስሱ ብርጌድ የደቦ ፍርጠጣ ጥረት
የአፍሪካ አንድነት (እኔ ለማስረዳት የተገደድኩበት አሳፋሪው ከሮም ስምምነት ፍርጠጣ) "የደቦ የማስፈራራት ሕብረት" ከሸፈ። "አስቸኳዩ ልዩ ስብሰባ" "አ.አ. ከዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ችሎት ጋር ያለው ግንኙነት ያከትማል ብለው ያሰቡትና ሴራውን የፈተሉት ባለሥልጣናት፤ "ከተባበሩት መንግስታት የፀጥታ ካውንስል ጋር ውይይት ለማድረግ በሚል እሳቤ በኬንያው ፕሬዜዳንትና ምክትል ፕሬዜዳንት እንዲሁም በሱዳኑ ፕሬዜዳንት ላይ የተመሰረተውን ክስ በተመለከተ አፍሪካ አንድነት ልዩነት አለው፤ የሮም ስምምነት አንቀጽ 16 እነሱን ተጠያቂ ሊያደርጋቸው ኣይገባም ምህረት ያድርግላቸው አይነት ውሳኔ ይዞ መጠናቀቁ አስገርሟቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ውይይት ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ (፩)

አብርሃም ያየህ (ክፍል አንድ)

የኤርትራን ነፃነት በተመለከተ የወያነ መሪዎችና ቲፎዞዎቻቸው ሁሌም ሊያስረዱን የሚፈልጉት፣ ኤርትራ ነፃነቷን ያገኘችው በነሱ ፍላጎት ሳይሆን፤ ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በጦርነት አሸንፎ ኤርትራን ስለተቆጣጠረ ምንም ማድረግ የሚቻል ነገር ያለመኖሩን ነው። ይሁን እንጂ ይህ ትክክለኛ መግለጫ አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ

ይሄይስ አእምሮ

በሀገራችን የስም አወጣጥ ወግና ልማድ እልም ያለችዋ ጥሩራ ባሪያ "አልማዝ" ወይም "ፀሐይ"፣ በነጭናጫነቷና በምግባረ ብልሹነቷ መንደርተኛው ሁሉ የሚያውቃት ሴት ወይዘሮ "ዐመለወርቅ" ወይም "አበቅየለሽ"፣ እልም ያለው ቦቅቧቃ "ደም መላሽ" ወይም "ሺመክት"፣ ቤሣቤስቲን የሌለው የኔቢጤው መናጢ ድሃ "ሀብታሙ" ወይም "አዱኛ"፣ እንዴት ያለው ንፉግና ክፉ ሰው "ቸሩ" ወይም "ደጉ"፣ ... ተብሎ ሲጠራ እናውቃለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስንቱን አጣን!

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

እንደ ኢትዮጵያ ባለ ኋላቀር አገር አገር ውስጥ መሠልጠን ብዙ ችግር አለበት፤ እኔ ራሴ በኮምፒዩተር መጻፍ ከጀመርሁ ሠላሳ ዓመት ሊሆነኝ ነው፤ ታዲያ መብራት ጠፋና የምሠራው ባጣ የቆዩ ወረቀቶችን ሳገላብጥ አንድ እአአ በዲሴምበር 26 1965 ከዱሮ ተማሪዬ የተጻፈልኝን ደብዳቤ አገኘሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ እች ናት፤ አገሬ እች ናት!!

አሌክስ አብረሃም

እናት አገርን የሚያሳምረው ህንፃ ይመስለኝ ነበር ... አገርን የሚያሳምረው መንገድ ይመስለኝ ነበር አገርን የሚያሳምረው ዛፍና ቅጠል ይመስለኝ ነበር ... አገርን የሚያሳምረው ለካ ለአንድ አላማ የተሰለፈ በአንድነትና በአብሮነት ስሜት ፈገግታና እልሁ ፊቱ ላይ የሚንቀለቀል ህዝብ ነው!! አገሬ ቆንጆ ናት ድህነት ብስቁልና መገፋት የጋረደው ፈገግታችን እንዲህ እንደ ዛሬ ከችግራችን በላይ ፈክቶ ሲታይ አልኩ ... ኢትዮጵያ እች ናት፤ አገሬ እችናት!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይቺ ባንዲራ!

ተመስገን ደሳለኝ

"ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም፣ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም" ማን ነበር ያቀነቀነው? ... ብቻ ማንም ይሁን ማን፤ እኔም እደግመዋለሁ፡- ሀገሬን የደፈረ ይውደም!! ... እነሆ ከፉከራው ወደ አጀንዳችን እንለፍ። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን፣ በሚቀጥለው ዓመት በብራዚል በሚካሄደው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ለመሳተፍ፣ ከናይጄሪያ ጋር የደርሶ መልስ ግጥሚያ ብቻ ቀርቶታል። በነገው ዕለትም የመጀመሪያውን ጨዋታ በአዲስ አበባ ያደርጋል። በዚህ ፅሁፍ የማነሳው ሃሳብም፣ ስለጨዋታው ሳይሆን፣ ጨዋታውን የሚያደምቀው ሰንደቅ-ዓላማን (ባንዲራን) በተመለከተ ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀጣዩ የኢህአዴግ ዒላማ ‘ማህበረ ቅዱሳን’ ይሆን?

ተመስገን ደሳለኝ

የኢህአዴግ ታጋዮች የመንግስት "ጠንካራ ይዞታ" የሚባሉ ከተሞችን ሳይቀር መቆጣጠር ችለዋል፤ ወደ አዲስ አበባ የሚያደርጉት ግስጋሴም ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያምን እንቅልፍ ነስቷል። በአንዳች ተአምር ግስጋሴውን መግታት ካልቻሉ፣ በጥቂት ወራት ውስጥ ሁሉም ነገር ታሪክ እንደሚሆን በማወቃቸው፣ መላ በማፈላለጉ ላይ ተጠምደዋል። በዚህ ጊዜም ነበር (የሃሳቡ አመንጪ ተለይቶ ባይታወቅም) "ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች የአጭር ጊዜ ስልጠና ሰጥቶ፣ ከ ገሪቱ ሠራዊት ጎን ማሰለፍና የ'ወንበዴ'ውን ጦር መድረሻ ማሳጣት" የሚለው ሃሳብ እንደ መፍትሄ የተወሰደው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታማኝ እና ቴዲ ትላንት ምሽት

ክንፉ አሰፋ

ትላንት ምሽት። እለተ እሁድ፤ ኦክቶበር 6፣ 2013። ታማኝ በየነ እና ቴዲ አፍሮ በስልክ ያወራሉ። ንግግራቸው ከወትሮው የተለየ አልነበረም። እንደ ቀድሞው እየተቀላለዱ ይሳሳቃሉ። ታማኝ ከዴንቨር-ኮሎራዶ፣ ቴዲ ደግሞ ከሲድኒ- አውስትራሊያ በስራ ላይ ነበሩ። በዚህ የሶስትዮሽ የስልክ ጨዋታ ላይ እኔና ጴጥሮስ አሸናፊም ገብተናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ