ከአንድነቶች ሦስት ወር ዘመቻዎች የተማርናቸው

ግርማ ሞገስ

የህወሓት/ኢህአዴግ ጠንካራ ጎኑ እስከ ጥርሳቸው ድረስ የታጠቁት ፖሊስ፣ ደህንነት፣ ምድር ጦር፣ አየር ኃይል፣ አየር ወለድ፣ ካድሬ እና ቅጥረኛ ወርበሎችን ያካትታል። የሚያውቀው የፖለቲካ ትግል ዘዴ በጫካ መገዳደልን እንጂ በከተሞች ሠላማዊ ትግሎች ማድረግ አይደለም። ስለዚህ ሠላማዊ ትግል ህወሓት/ኢህአዴግን በማያውቀው የትግል ሜዳ፣ የትግል ዘዴ እና በደካማ ጎኑ እንዲታገል እንደሚያስገድደው እና የህዝብ ድጋፍ የሚያሳጡ ስህተቶች እንደሚያሠራው የአንድነቶች የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት ዘመቻ ወለል አድርጎ አስተምሮናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንዳርጋቸው ጽጌ፡- ከኢሳያስ ጉያ፤ ነፃነት ወይስ ባርነት?

ቦጋለ ካሣዬ 

"... ግንቦት-7 ሲመሰረት፤ ብዙ ሀገር ወዳድ ዜጋ 500 ዶላር ወይም ኢሮ እያዋጣ ተቀላቅሎት ነበር። ይሁን እንጂ እነአንዳርጋቸው ብራቸውን ከሰበሰቡ በኋላ፤ በመጀመሪያ ከአንድነት ኃይሎች ጋር ለመስራት ፍላጎታቸውን ማሳየት ጀመሩ። ቀስ ብለው ደግሞ ከቅንጅት መንፈስ በመንሽራተት፤ የኦነግንና ኦብነግን ማሽኮርመም ጀመሩ። የአንድነቱ ኃይል አጉረመረመ። እነአንዳርጋቸው ግን ብዙም አልተጨነቁም። ኢሳታቸው ስላለ የፕሮፓጋንዳ የበላይነት አላቸውና፤ የጎሣ ፖለቲካቸውን በታሪካዊ በደል ፈጻሚ (አማራ) እና ሰለባ (ሌለው ጎሣ) እያመካኙ፤ አሁን ኤርትራ ሽባ ሆኖ የቀረውን ከማል ገልቹን፤ እንደ የአንድነት ታጋይ በማግዘፍ ጄኔራል ከማል ገልቹ! ጄኔራል ከማል ገልቹ! እያሉ አናፉብን። ..."

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ውይይት ከግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ

አብርሃም ያየህ

ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

የግንቦት 7 ዋና ፀሐፊና የድርጅቱ ያመራር አባል የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ከቅርብ ቀናት በፊት ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ጋር ባደረጉት ሰፊ ቃለመጠይቅ አማካኝነት በሰነዘሯቸው የተለያዩ አብይ ሃሳቦችና፣ ከቃለ-መጠይቁ ውጭ ነገር ግን ተያያዥ የሆኑ ሌሎች ጉዳዮች፣ መሰረት በማድረግ ለመወያየት ወስኛለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ አበባ ሆይ ድምጽሽን አሰሚ!

አማኑኤል ዘሰላም

በደሴ፣ ጎንደር፣ ባህር ዳር፣ ፍቼ፣ አዳማ/ናዝሬት፣ ሮቢ/ባሌ፣ መቀሌ፣ ወላይታ ሶዳ፣ ጂንካ፣ አርባ ምንጭ ... ሰላማዊ ሰልፎችና ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል። በአዋሳ፣ ድሬደዋ፣ ወሊሶ፣ አሶሳና ጋምቤላ፣ እቅዱ ውስጥ የነበሩም ቢሆንም በገንዘብ አቅም ምክንያት ለጊዜው ሰልፎች ሊካሄዱ አልቻሉም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አወይ ሶሪያ - የኢትዮጵያ ጠላት

Ethiopia ኢትዮጵያSyria ሶሪያሰሎሞን ተሰማ ጂ.
የሶሪያ ጉዳይ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ መጥቷል። በስልጣን ላይ ያለው ጎሳ "የአላዊት ጎሳ" ይባላል። አላዊቶችና በደዊኖች በሽፍትነትና በባህር ላይ ውንብድና ስማቸው የገነኑ ናቸው። በደዊኖች፣ ሶሪያን ለዘመናት ያህል ሲፈልጧትና ሲቆርጧት ኖረዋል። እንደነሱ ዘረኛ፣ እንደበደዊኖች ጠባብ፣ አክራሪና ቁመኛ ታይቶም-ተሰምቶም አይታወቅም። አላዊቶችም ቢሆኑ "አልሸሹም ዞር አሉ" ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ክፍል ሁለት/2

Girma Moges ግርማ ሞገስግርማ ሞገስ 

በክፍል አንድ እንዳነበብነው የዝንጀሮዎቹ አምባገነን ጌታ ተርቦ ከመሞቱ በፊት የሚቀልቡት የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ነበሩት። የፖለቲካ ኃይል ምንጮቹ መድረቅ ተርቦ እንዲሞት አድርገውታል። እንደ ዝንጀሮዎቹ አምባገነን ጌታ መንግሥትም የፖለቲካ ኃይል ምንጮች አሉት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ በባሕርይው ጅብና ውሻ ነው

ይነጋል በላቸው

"አውሬ አውሬነቱን አይረሳም" አለ ልበል ተወልደ (ተቦርነ) ስለአንበሣው ቀላቢውን መግደል ሲያወራ አሁን? አዎ፣ ብሏል። እውነት ነው፤ አውሬ አውሬነቱን አይረሳም። ወያኔም ወያኔነቱን አይረሳም - እባብ የትምና መቼም ቢሆን እባብነቱንና የወጣበትን ጉድጓድ እንደማይረሣ ሁሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዝንጀሮዎቹ ጌታ ሞተ - ለምን እና እንዴት?

Girma Moges ግርማ ሞገስየፖለቲካ ኃይል ምንጮች (ክፍል አንድ/2)

ግርማ ሞገስ

የዝንጀሮዎቹ ጌታ አጭር ታሪክ የተወሰደው ቻይናዊው ሊዩ ጂ/ Liu-Ji (1311-1375) ከጻፈው የሞራል ማስተማሪያ መጽሐፍ ነው። ይኽ አጭር ታሪክ የአምባገነን ገዢዎች የፖለቲካ ኃይል ከየት እንደሚፈስላቸው (ምንጩ ምን እንደሆነ) እና እንዴት ምንጩን በመቆጣጠር የአምባገነኖችን አቅም መቆጣጠር አልፎም ምንጩን በማድረቅ አምባገነኖችን ማስራብ እንደሚቻል በምሳሌ አድርጎ ግልጽ ያደርጋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መስከረም ሲጠባ አደይ ሲፈነዳ ...

Yedenekachew Kebede ይድነቃቸው ከበደይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ)

የዘመን መለወጫ ክብረ በዓል በየትኛውም ሀገር እንደ አገሩ ወግና ልማድ በድቅመት የሚከበር በዓል ነው፤ በእኛ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ደግሞ ልማድና ወጋቻን እጅግ ከመጠንከሩ የተነሳ ለአዲስ ዓመት ወይም ለዘመን መለወጫ ክብረ በዓል ዝግጅታችንም ሆነ አከባበራችን እጅግ በጣም ጠንካራና ደስ የሚል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከለውጡ በኋላስ?

(ተመስገን ደሳለኝ)

ኢህአዴግ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ (በውስጥም በውጪም ተግዳሮቶች) መገፋቱን በሚያመላክቱ የፖለቲካ አንዳዎች ላይ የሚያጠነጥን አንድ ፅሁፍ (‹የአብዮቱ የምፅዓት ቀን ምልክቶች›› በሚል ርዕስ) አቅርቤ እንደነበር ይታወሳል፤ ይዘቱም በመጪዎቹ ወራት ወይም ዓመት ስርዓቱ ‹ምርጫ› አሊያም ‹ህዝባዊ› እምቢተኝነት ከሚያመጣው ‹ማዕበል› (እንደበረከት ስምዖን አገላለፅ ‹ናዳን በሚገታ ሩጫ›) የማምለጥ ዕድሉ የጠበበ መሆኑን የሚያመላክት ነው፤ ይሁንና አንድ አብዮት ታላቅ (ውጤታማ) ሊባል የሚችለው አምባገነን ስርዓትን በመቀየሩ ብቻ ስላልሆነ (ሥር-ነቀል ለውጥ የሚፈጥር አብዮት ዋጋ የሚኖረው የዲሞክራሲ ተቋማትን መሰረት መጣል ሲችል ነውና) በቀጣይ መፃኢ ዕድሉ ላይ መነጋገሩ አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ