የኛ ነገር፤ ከኔ ማእዘን፤ ክፍል 14

ተክለሚካኤል አበበ(ቶሮንቶ-ካናዳ)

 የግንቦት ሰባት ርእሰ - አንቀጽ

 1.      ከግንቦት ሰባትና የግንቦት ሰባት አመራር አባላት የማደንቅላቸው ድንቅ ነገር ቢኖር ሌሎችን ያለመተናኮስ ባህርያቸው ነው።ሌሎች ቢተነኩሷቸውም እንኳን፤ ምንም ምላሽ ያለመስጠት አቋማቸውን አደንቅላቸዋለሁ። እስካለፈው ሁለት ሳምንት ድረስ። ባለፈው ሁለት ሳምንት ግን፤ በራሳቸው አነሳሽነት አገር ቤት ያሉትን ድርጅቶች ወደ መተንኮስ ያዘነበሉ ይመስላል። በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን። ስለዚህም ጥያቄ ተነሳብኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መውጫ ሰጥቶ መግቢያ የከለከለን አሰዳጁ ማን ነው?

ግርማ ሠይፉ ማሩ

ሀገራቸን ኢትዮጵያን ለቀው ለስደት የተዘጋጁት ዜጎችን ቁጥር መገመት አስቸጋሪ ቢሆንም በአንድ ወይም በሌላ ምክንያት መውጣት የቻሉት ግን ላለመመለስ ብዙ ምክንያቶች አሉዋቸው። ይህን የዜጎች (በተለይ የተማሩና ወጣቶች) ስደት ሀገራችንን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት እንደሆነ እና ወደፊትም ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ለማወቅ ሊቅ መሆን የሚያስፈልግ አይመሰለኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ ዓመትም ያላባራው ሰቆቃ

ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እና ልናገረው የከበደኝ ሮሮ

ነቢዩ ሲራክ

በግልም ቢሆን አዲሱን ዓመት በሠላም እና በደስታ መቀበሌ እውነት ነው! መስከረም ጠብቶ ብዙ ቀናት ሳንቆጥር ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚደርሱኝ የስደተኛ ወገን መከራ ግን ከአዲሱ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ እስከ መባቻው አላባራም። እያንዳንዱን የወገን ስደት ሰቆቃ መከራ ጨክኜ ከመናገር ለመቆጥብ ያደረግኩት ትግል ላንዲት ቀን ቢሳካም፤ ህሊናዬ ግን እረፍት አላገኘም። በተለይ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ "ብሪማን" ተብሎ በሚጠራው የጅዳው ትልቅ ማረሚያ ቤት የደረሰኝ መረጃ ያማል ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሙስናው ጉዳይ

ክፍል ሁለት

ዳዊት ከበደ ወየሳ

እውነት የማይመስሉ ግን እውነት የሆኑ የሙስና ታሪኮች - በኢትዮጵያ

አሁን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ወደ 2006 ተሻግረናል። ከአመት ወደ አመት ስንሸጋገር ደግሞ ያለፈውን አመት የሙስና ነገር በገደምዳሜ ዳሰስ አድርገን ብናልፍ ክፋት የለውም። በመሆኑም የስራ ባልደረባዬ ክንፉ አሰፋ "ክፍል አንድ" ብሎ በጀመረው የሙስናው ጉዳይ ... "ክፍል ሁለት" ብዬ እኔ ቀጠልኩበት፤ አንብቡት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ኢትዮጵያ ከ2ኛ የዓለም ጦርነት በኋላ የተፈጠረች ሀገር ናት!"

ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤልዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
የባሰ አታምጣ! ነው የሚባለው። መቼም የኤርትራ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋዜጣዊ መገለጫ በሰጡ ቁጥር ግርግር ሳይፈጥሩ፤ ጎረበት አገር በውስጠ ወይራ ሳይጎነትሉ፤ ምዕራባውያን መንግሥታት ግልጽና በማያሻማ ቋንቋ ሳይወርፉና ሳይዘነጥሉ፤ ብዙሐን ፈገግ ሳያሰኙ፤ በአንጻሩ ደግሞ የተማረውን ክፍል ሳያስለቅሱና እርር ድብን እስኪል ድረስ ሳያደርጉ አልፉ ማለት ዘበት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ወጣቱ አንበሳ ላገርህ ተነሳ...”

የአርቲስት ሻምበል በላይነህ አገራዊ ስራዎች አርአያነት

ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሳችሁ። እዲሱ አመት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ብስራት ይዞ የሚመጣ ይሁን። ያለምንም ደም መፋሰስ ይህ ዘረኛ የወያኔ ገዢ ቡድን መቃብር ገብቶ፤ ዘረኝነት፤ ጎጠኝነትና በታኝነት ከምድራችን ጠፍቶ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ተፋቅሮ ተከባብሮ፤ ሲያጠፉ የሚቀጣቸውን የሚሽራቸውን፤ ሲያለሙ የሚሾማችውን የሚሸልማቸውን መሪዎች በድምጹ መርጦ፤ የሚኖርበት፤ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከዘር ማንነቱ በፊት በኢትዮጵያ ሲምል ሲገዘት የምናይበት፤ ዜጎች ሁሉ ለሀገሬ፤..... ለወገኔ.. እያሉ ሲተጉ፤ ለጋራ እድገትና ብልጽግና ሲጓጉ....አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ እያሉ አንዳቸው ላንዳቸው ሲሞቱ የምናይበት የተአምር ዘመን ይሁንልን,....ዘረኞች ለአንዴና ለመጨረሻ የሚጠፉበት ዘመን ይሁንልን....2006. አሜን!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አውስትራሊያን ከኢትዮጵያ ጋር የማመሳሰል ሕልም

ታክሎ ተሾመ

አውስትራሊያ ቀለመ ብዙ ሀገር ናት። ከ200 በላይ ቋንቋ የሚናገሩባት በዝንቅ ማኅበረሰብ የተመሰረተች፤ በጥሬ ማዕድኗ፤ ወንድ ሴት ሳይል የሰዎች የተፈጥሮ ሰብዓዊ መብት የተከበረባት ሀገር ማን ትባላለች ብሎ ለሚጠይቅ መልሱ አውስትራሊያ ናት ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሐምሌ ጨረቃ አንዱዓለም አራጌ ዋለ (ከቃሊቲ ማጎሪያ) ክፍል ፩

አንዷለም አራጌ ዋለ Andualem Aragie Walleከጉልበተኞች ጠመንጃ የሚወጣ ጥይት ስጋን እንጂ እምነትን ሊገድል እንደማይችለው ሁሉ፣ ከቤተሰብና ወዳጅ ዘመድ ተነጥሎ ቅዝቃዜ በዋጠው ጠባብ ክፍል ውስጥ መታሰርም አካልን እንጂ ምናብን (ህልምን) ሊያስር የሚችልበት ጉልበት የለውም። ከቶስ እንደምናብ ሜዳውን፣ ተራራውን፣ ቁልቁለቱን፣ ዳገቱን፣ ሸለቆውን፣ ኮረብታውን በሰከንድ ክፍልፋዮች ከብርሃን ፈጥኖ በመምዘግዘግ ያለመዛነፍ ያሰበበት የሚደርስ ምን ኃይል አለ? ከጠባቧ ክፍል ውስጥ "ድርሻህ" ተብላ በተሰጠችኝ 90 ሴንቲ ሜትር ላይ ቀሪ ህይወቴን አሳልፍ ዘንድ በግፍ ፍርድ ብታሰርም ዕረፍት ለማያውቀው ምናቤ ገለታ ይድረሰውና ይዞኝ ይከንፋል፤ ወደ ምፈልገው አድርሶ ይመልሰኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ