ግንቦት ሰባት፤ ብርሀኑ፤ አንዳርጋቸው፤ የኤርትራ ነገር?

ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ ካናዳ)

የኛ ነገር፡ ክፍል 16፤ ከኔ ማእዘን፤

እንደ መግቢያ

1. ይህ ጽሁፍ ሲታሽ፤ ሲሰቃይ እዚህ የደረሰ የቁጭት ጽሁፍ ነው። ወዲህም ግንቦት ሰባት የምወደውበሱ ግን ደስ ያላለኝ ፓርቲ ስለሆነና፤ ዲባቶ ብርሀኑ ነጋ ለኢሳት ዝግጅት ወደቶሮንቶ ስለሚዘልቅ፤ ያንዳንዶቻችንን ቁጭትና ጭንቀት ለመገለጽ የተሰናዳ ጽኁፍ ነው። ቀደም ያሉት የራስን የሆነን አካል የተቸሁባቸው ጽሁፎቼ ባንዳንድ ወዳጆቼ ዘንድ ቅሬታ ፈጥረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ ወዴት? በየታሪካዊ መጋጠሚያው አዲስ መልስ የሚሻ የተደጋገመ ጥያቄ

ዩሱፍ ያሲን

በየታሪክ መጋጠሚያው የሚወጥር ጥያቄ

በተለያዩ የሀገራችን ወሳኝ የታሪክ ምዕራፎች ኢትዮጵያ ለመፃኢ እድሏ ዕጣ ፈንታ ወሳኝ በሆነ መስቀለኛ የታሪክ መጋጣሚያ ላይ ትገኛለች ሲባል ደጋግመን ሰምተናል። በርካታ ጊዜያት መንታ መንገድ ላይ ናት ተብሎ ሲነገር እንሰማለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በታሪክ ውስጥ የሚሰሩ ስትራቴጂያዊ ስህተቶች- ጥሩ አጋጣሚን ያለመጠቀም ችግር

(አምስተርዳም ጉባዔ ላይ ለጥናት የቀረበ ጽሑፍ)

ፈቃዱ በቀለ

የታሪክ ግዴታ ሆኖ የሰው ልጅ እንደማኅበረሰብ ከተደራጀና፣ ሥልጣንና ሀብት በጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ስር መውደቅ ከጀመረ ወዲህ የአንድ ህዝብ ዕድልና የወደፊት ጉዞው፣ ታሪክ የመስራትና ያለመስራት ችሎታው በመጀመሪያ ደረጃ ሊወሰን የሚችለው ሥልጣንን በቁጥጥራቸው ውስጥ ባስቀመጡ ጥቂት ሰዎች አማካይነት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ የኳስ ሜዳ ልጅ ነው

ሄኖክ የሽጥላ (ገጣሚ)

ከምን ልጀምር? እንደው ይጨንቃል፤ ደሞ ዝም ቢሉት ያንቃል። አሁን ይሄን የምጥፈው ለማስተማር ነው ለማካረር? በልጅነቴ አንድ አብሮ አደጌ በጣም የሚወዳቸው እናቱና አባቱ እየተጋጩ ቢያስቸግሩት፣ ሄኒ አሁን አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ማንን ትጠላለህ? ብሎ የጠየቀኝ ትዝ አለኝ። ማንን ልጥላ? ለማን አግዤስ ማንን ላውግዝ? ማንንስ ልውቀስ? ማንንስ ልጥቀስ? ሲደብር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ

የተከበሩ ግርማ ሠይፉ ማሩ, Girma Seifuይህንን የማፊያ ቡድን በማፍረስ ታሪክ ይስሩ!

ግርማ ሠይፉ ማሩ

በ2005 ዓ.ም. የምክር ቤት ዘመን መጨረሻ ላይ የደህንነት መስሪያ ቤቱን በሚኒስትር ደረጃ ለማዋቀር የሚረዳ አንድ አዋጅ ለምክር ቤት ቀርቦ ፀድቆዋል። ይህ አዋጅ ሲፀድቅ ከነቅሬታዬ ያለኝን ድጋፍ መስጠቴ ይታወቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ጊዜ መስተዋቱ!” ተስፋዬ ገ/አብ ማነው?

(ከወልደሚካኤል መሸሻ)

ውድ አንባቢያን ይህን ጽሑፍ ጀምሬ ያጠናቀቅሁት ወደ እ . ኤ. አ በ2012 መጀመሪያ ነው። ለምን እስከአሁን አቆየኸው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ ነው ታዲያ። ተገቢ ጥያቄ ነው። የተለያዩ አቅጣጫዎችን የማየትና የማሰላሰል ሁኔታ በአንድ በኩል፣ በሌላ ደግሞ በአነሰኛ መጽሐፍ መልክ ባሳትመውስ የሚል አሳብ እየተደቀነብኝ መጥቶ ነው። ሁለቱም ተራ በተራ ተፈታተኑኝ። የትኛውን እንደምመርጥ ማውጣት ማውረዱን ቀጠልሁ። ጽሑፍን እንድያዩትና አሳባቸውን እንዲሰጡኝ ለጥቂት ወዳጆቼ ላክሁ። አንዳንዶቹ ቶሎ ጽሑፉ እንዲወጣ የሚገፋፋ አሳብ ሰጡኝ። አንዳንዶች ከማስጠበቅ ውጭ ላያልፉ ሆኑ። በዚህ ላይ እያለሁ ለጽሑፉ መሠረት የሆነው የእምዬ ጠላት በመርዘኛ ብዕሩ ብቅ ማለቱን ሰማሁ። ወዳጆቹ ከወዲህ ወዲያ እያሉ መሆኑንም አዳመጥሁ። እርሱም የእምዬ ልጆችን የማባላቱን ሥራ ማጠናቀቁን ከወብሳይቱ ተመለከትሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲሱ የኢህአዴግ አሰላለፍ

ተመስገን ደሳለኝ

ኢህአዴግ ከቀድሞ ሊቀ-መንበሩ አቶ መለስ ዜናዊ ህልፈት በኋላ በተከሰተበት ውስጣዊ ልዩነት በተለዋዋጭ የኃይል ሚዛን ሥር ለማደር በመገደዱ የስልጣኑን መዘውር የሚያሽከረክረውን አካል ለመለየት አዳጋች ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይህ ሽኩቻ መፍትሄ ማግኘቱን የሚያመላክቱ ሁናቴዎች መፈጠራቸውን የውስጥ አወቅ መረጃዎች ጠቁመዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለህወሓት ፀረ-ኢትዮጵያ አካሄድ የተሸፈኑ ምስጢሮች

የህወሓትን ፀረ-ኢትዮጵያ አካሄድና ዓላማ በመቃወም የሕይወት ማስዋዕትነት የከፈሉ አመራር ነበሩ ወይ? ከነበሩስ እነማን ናቸው?

ገብረመድህን አርኣያ ከአስውትራሊያ

ገሰሰው አየለ፣ አግአዚ ገሰሰ፣ ሙሴ መሃሪ ተክሌ፣ አጽብሃ ዳኛው እና ዶ/ር አታክልት ቀጸላ Gessesew Ayele, Agazi Gessese, Musse Mahri Tekle, Atsbeha Dagnachew and Dr. Atakilt Ketswela

ከዚህ ቀጥለን የምንመለከተው ትኩረት ያልተሰጠውን ተሸፍኖ የነበረውን እና የህወሓት መሪዎች፣ በሕይወት ያሉትም የሞቱትም፣ ከወያኔ የተባረሩ አመራርም ጉዳዩ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ተዳፍኖ እንዲቀር ከባድ ጥረት እያደረጉበት ያለውን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ