የእኛ “መንግስት”

(ተመስገን ደሳለኝ)

“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም”

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ለምን አያስፈራ?

ግርማ ሠይፉ ማሩ

"የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ለምን ያስፈራል?" በሚል ርዕስ ሪፖርተር ጋዜጣ በእሑድ ነሓሴ 5 ህትሙ ረጅም ፅሁፍ አሰነበቦናል። ፀሐፊው በቦነያ ሰ. በሚል አቶ/ወሪት/ወሮ ይሁን በማይታወቅ ስም ነው ያወጡት። ይዘቱን ሳነበው የምናውቃቸው የኢህአዴግ ሹሞች በብዕር ስም ልከውት ያው የኢህአዴግ አቋም ነው ብዬ ለመውሰድ ዝግጁ ሆኜ ንባቤን ሳጠናቅቅ፤ ፀሐፉው የሕግ ባለሞያ እንዲሁም በተለያየ የመንግሥትና መንግታስዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በሙያቸው ሰርተዋል የሚለው የአዘጋጁ ማስታወሻ መልስ እንድሰጥ ጋበዘኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሽብርተኝነት አዋጁ፤ የጠሉትን መምቻ?


ተመስገን ደሳለኝ

ኢህአዴግ ባለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት በስራ ላይ ካዋላቸው አዋጆች መካከል የ‹‹ፀረ-ሽብር ህጉ››ን ያህል ያጨቃጨቀ የለም ቢባል ከእውነቱ ብዙም አልራቀም፡፡ በርግጥ ከተቃውሞ አቅራቢው አብዛኛው በደፈናው ‹‹ህጉ አያስፈልግም›› የሚል አልነበረም፡፡ ህጉ ‹‹ሽብርተኝነት››ን የገለፀበት መንገድና አንዳንድ አንቀፆቹ ለትርጉም አሻሚ በመሆናቸው ከስርዓቱ ባህሪ አኳያ ለፖለቲካ ጥቅም የሚውሉበት ዕድል መኖሩ አይቀሬ ነው የሚል ስጋት ነበር፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የነሱ ድፍረት የኛ ፍርሀት ነው

 ሉሉ ከበደ (ደራሲና ጋዜጠኛ)

ሙስሊም ወንድሞቻችን ሁለት አመት ለሚጠጋ ጊዜ እየተገደሉ ነው።  በጽናት፤ በጀግንነትና በብልሀት እናም በመስዋእትነት የመብት ትግላቸውን ቀጥለዋል። በለተ - አውዳመት ኢድ አልፈጥርም የመስዋእትነት ደማቸውን፤ …ኢትዮያን የተቆጣጠራት የትግራይ ዱር አራዊት መንጋ አፍሷል። የሞቱትን ሁሉ አላህ በጀነት ነፍሳቸውን ያኑር ከማለት በቀር ምን ይባላል ?  ለሁሉም ወገኖቻችን ለቤተሰቦቻቸው፤ ለዘመዶቻቸው አላህ ጥናቱን ይስጥ እላለሁ። በከንቱ ለፈሰሰ ደማቸውም እሱ በማያልቅበት ስልጣኑ ፍርዱን ይስጥ። ሳይውል ሳያድር።...አላህ ሁ አክባር!!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰላም ምንድነው?

ታደሰ ብሩ
1. መንደርደሪያ

የወያኔ ሰዎች ጋር የፓለቲካ ሙግት መሰል ነገር ከገጠማቸው ውይይቱን ያለ ጥርጥር የሚረቱበት ወደሚመስላቸው ወደ "ሰላም" ጉዳይ ይስቡታል። ከዚያም አገራችን ለዘመናት ሰላም የራቃት የነበረ መሆኑን ያስቷውሷችሁና "እድሜ ለኢሕአዴግ ይኸው የሰላም አየር እየተነፈስን ነው" ይሏችኋል። ንግግራቸውን የመቀጠል እድል ካገኙ መረር ብለው "ነገር ግን ፀረ-ሰላም ኃይሎች አልተኙልንም። በሰሜን፣ በምሥራቅ፣ በአገር ውስጥ፣ በዲያስፓራ ...." እያሉ የፀረ-ሰላም ኃይሎች ረዥም ዝርዝር ያቀርቡላችኋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነሀሴ 26ን በደቦ ሸኝተን፤ 2006 ዓ.ምን በተስፋ

አርኣያ ጌታቸው Araya Getachewአርኣያ ጌታቸው

የዘንደሮ ክረምት ከቀደምቶቹ በጥቂቱ ጠንከር ያለና ብዙዎችን በተለይም አዲስ አበቤዎችን እያማረረ ነው። ሌላው "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ" የሚያስብለው ደግሞ የከተማዋ መንገዶች በአብዛኛው ጥገና ላይ መሆናቸውና በዚህም ሳቢያ የበርካቶች መኖርያና የንግድ ሱቆቻቸው መፍረሳቸው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከቁጫ እስከ ኦሮሞ - ማንነትና የማንነት ፖለቲካ እንደምታና መዘዞቹ

ዩሱፍ ያሲን

የአሜሪካ ድምፅና የዶቼቬሌ አማርኛ ራዲዮ ፕሮግራሞች ላይ የቁጫ ሕዝብ የራሱን ማንነት የመወሰን ጉዳይ አስመልክቶ ለመንግሥት ጥያቄ ያቀረቡ ሰዎች መታሰራቸው ዜና በቅርቡ ተዘግቦ ሰምተናል። 40 የሚሆኑ የአካባቢ ሽማግሌዎች እነዚህ የተሳሩ ሰዎችን ለማስፈታት አዲስ አባባ ድረስ መምጣታቸውንም ተዘግቦዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አውራውን ፍለጋ…

በተመስገን ደሳለኝ
‹‹በድብልቅልቁ አምላክ››

መግቢያ
ዛሬ በስሱ ላነሳው ያሰብኩትን አ ንዳ አለቃ አፅሜ በምኒልክ ዘመን ካሳተሙት አንድያ መጽሐፋቸው ላይ ባገኘሁት ታሪክ ል ምር፤ እንዲህም ይነበባል፡- ‹‹በሸዋ መርድ አዝማች ኃይሌ፣ በሣህለ ሥላሴ አልጋ ከተቀመጡ በኋላ ከአቶ ሰይፉ ጋር ቂሙ የማይበርድ የቅድስት ኃይማኖት ጦርነት ተ መረ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተሸንፈን እንዳንቀር

ሉሉ ደበደ (ደራሲና ጋዜጠኛ)

አንባ ገነኖች ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ጊዜ እየረዘመ በሄደ ቁጥር አሰራራቸውን እየገመገሙና ራሳቸውን እያረሙ፤ ስልጣን ላይ ለመዝለቅ ያበቋቸውን ስልቶች የበለጠ ማጠናክራቸው እንዳለ ሆኖ፤ ቆይታቸው አዳዲስ ስልቶችን ለመፍጠርና ለመሞከርም እድል ይሰጣቸዋል ። ለምሳሌ መለስ ዜናዊ አባይን እንገነባለን ብሎ ድንገት እየተጯጯኽ ህዝብን ማሯሯጥ እንደ መረው አይነት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ