በ19 ዓመቴ ወልጄው፣ ጠፍቶ፣ ሞቷል ያልኩትን ልጄን አገኘሁት

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ Dr. Fikre Tolossa ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ (ዶ/ር)

ውድ አንባብያን ሆይ! የምሥራች! የምሥራች ስላችሁም በሀገራችን ባህል አጸፋውን "ምስር ብላ!" በሉኝ። ልቤን ወደ ሰማይ እያዘለለ፣ እግሮቼን ጮቤ የሚያስመታ ነገር ሰሞኑን ገጥሞኛልና። እሱውም ከአያሌ ከዘመናት በፊት ዕድሜዬ 19 ሳለ የወለድኩት ልጄ፣ ያውም የበኹር ልጄ፣ ጠፍቶብኝ "በቃ! ሞቷል፣ ተከቷል!" ብዬ እርሜን አውጥቼ እያዘንኩ እኖር ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሐምሌ ጨረቃ - አንዷለም አራጌ ዋለ (ከቃሊቲ ማጎሪያ)

አንዷለም አራጌ ዋለ Andualem Aragie Walleክፍል ሁለት

በሀገሬ ሰማይ ስር በሚደረገው የተቃውሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ከኢዴፓ እስከ አንድነት ፓርቲ ድረስ በመሳተፍ ለአስራ ሦስት ዓመታት ያህል የምችለውን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ። ይህ ኹነትም የፓርቲዎችን ጓዳ ፈትሼ ግንዛቤ እንዳገኝ ስላመቻቸልኝ፣ በቀጣይ ህዝባችን የፖለቲካና ሰብአዊ መብቶቹ ተከብረው ነፃነቱን እንዳያገኝ እንቅፋት ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ የማስባቸውን ነጥቦች እንደሚከተለው ለማቅረብ እወዳለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አጭር ማስታወሻ የሰማያዊ ፖርቲ የተቃውሞ ሠልፍ

ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ)ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ ፓርቲ የሕግ ጉዳይ ኃላፊ)

ነኀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፤ ይሁን እንጂ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት እንደሰፈር ጉልበታኛ ድንኳን ሰባሪ ዘው ብሎ በኃይማኖት ሰበብ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ በሕግ አግባብ ሣይሆን በጉልበት ሠልፍ መሰል ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፖለቲካ ሳይንስ ነው ወይ? ፖለቲካ ምሁራዊነት ያስፈልገዋል ወይ?

ፈቃዱ በቀለ

መግቢያ
በዚህ አርዕስት ላይ ለመጻፍ ከአሰብኩ ረዥም ጊዜ ሆነኝ። እንደሚታወቀው አንድ ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ቀላል አይደለም። የመንፈስ ርጋታን የሚጠይቅ ብቻ ሳይሆን፣ ለአንባቢ የሚቀርበው ጽሁፍ ከርስ በርስ ቅራኔዎች የተላቀቀና አሳማኝ እንዲሆን አድርጎ ለመጻፍና ለማስነበብ ረዥም ጊዜን ይፈጃል። ብዙ ዕውቀትንና ምርምርን ይጠይቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መለስ 'አንጃ' አይወድም

አብርሃ ደስታ Abreha Destaአብርሃ ደስታ ከመቐለ

የህወሓት ደጋፊዎች የአቶ አርከበ ሚና መቀነስ በአቶ አባይ ምክንያት እንደሆነ ያስባሉ። እንደኔ ግን አርከበ የተገለለው በአባይ ወልዱ ሳይሆን በመለስ ነው። መለስ ሥልጣን በጣም ከመውደዱ የተነሳ ሥልጣኑን የሚፎካከሩና አደጋ የሚደቅኑ አቅም ያላቸው የህወሓት ሰዎች ሲያርቅና ሲያጠፋ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሙስናው ጉዳይ

ክንፉ አሰፋ
በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች "ጸዳ" ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለሥልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ቡፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ፤ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ። ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሔር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአብዮቱ የምፅአት ቀን ምልክቶች!

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ Journalist Temesgen Desalegnተመስገን ደሳለኝ
"በአፍሪካ ትልቁ አምባገነን" የሚል ተቀፅላ የተሰጣቸው የሊቢያው ኮሎኔል መሀመድ ጋዳፊ እና የግብፁ ሆስኒ ሙባረክ በህዝባዊው እምቢተኝነት ከሥልጣን መነሳታቸው በመሰል አገዛዞች ስር ያደሩ ሕዝቦችን ለለውጥ ማነቃቃቱ የሚጠበቅ ነው። በተለይም ከራሳቸው መንግሥት ተኳርፈው አስተማማኝ የዲሞክራሲ ተቋማትን በገነቡ የምዕራብ ሀገራት በብዛት የሚኖሩ ዜጎች ላሏት ኢትዮጵያ ንቅናቄው የፈጠረው ተመሳሳይ መነሳሳት ቀላል ባለመሆኑ ኢህአዴግን ሊወጣው ከማይችለው ቅርቃር ውስጥ ከቶታል። የዚህ ተጠየቅም ቀድሞ እንዲህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ ድርጅቱ 'እሳት ማጥፊያ' ያደርጋቸው የነበሩ አጀንዳዎቹ ያለፈባቸው (Expired) መሆናቸውን ማሳየት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከመንግሥት የቤቶች ግንባታ ጀርባ ያለው ትክክለኛ ዓላማ ሲጋለጥ

ግርማ ሠይፉ ማሩ
ሰሞኑን ከፀረ-አሸባሪነት ሕግ በማስቀጠል የአዲስ አበባን ከተማ ነዋሪን በተለይ ሲያምስ ከርሞ አሁንም በማመስ ላይ ያለው የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ነው። በአዲስ አባባ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዳለ አሌ የሚባል አይደለም። ይህ ችግር እዚህ እንዲደርስ ደግሞ ዋናው ተዋናይ መንግሥት እንደሆነ መዘንጋት የለበትም። ምክንያቱም ለቤት መስሪያ የሚሆነውን ቦታ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ለዜጎች እንዳይደርስ በማድረጉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከአህያ ጋር ብጣሪ በልታ ከፈረስ ጋር ገብስ ትበላለች

"ከአድባይነት እርግማን ይሰውረን!"

ታክሎ ተሾመ

የኃይማኖት መሪው ቡድሐ የሚሰጠን አንድ እንቆቅልሽ የሚከተለውን ይመስላል። አንድ ነጋዴ ሩቅ ሄዶ ሲመለስ፤ ቤቱ በሽፍቶች ተዘርፎና ተቃጥሎ ይደርሳል። ከቤቱ ከተረፈው ረመጥ - መካከል አንድ ተቃጥሎ የከሰለ የሰው ገላ ያያል። "ይሄ ትንሹ ልጄ መሆን አለበት" አለ። በዚህ ምክንያት ምርር ብሎ አለቀሰ። ደረቱን መታ። ፀጉሩንም ነጨ። ገላውን እንደገና የማቃጠል፤ የሐዘን ሥነ-ስርዓት እንዲካሄድም አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኛ ነገር፡ ከኔ ማዕዘን፡ ክፍል 13


ተክለሚካኤል አበበ - ቶሮንቶ (ካናዳ)

በብርሀኑ ተበሳጨሁ፤ በሰማያዊ ተጽናናሁ፡ በአንድነት ደግሞ ተስፋ አደረግሁ

 

1-      ይህ ጽሁፍ ዓላማው አድናቆት፡ ትችትና ግብዣ ነው።የአንድነት ምሽትበቶሮንቶ ግብዣ። ከአድናቆትና ከግብዣው በፊት ስለፖለቲካ መሪዎችና ስለፖለቲካ ተንታኞች አትቶ፤ የብርሀኑ ነጋን (ዲባቶ) አቀራረብ ይተቻል።የሰማያዊ ፓርቲን ርምጃ ያደንቃል። የአንድነት ዘመቻን ስለማገዝ ያሳስባል። እንደው ተገጣጥሞ ነው እንጂ፤ አንዱን ለማሞገስ ሌላው መኮሰስምመከሰስም የለበትም።ግን አንዳንዴ ደግሞ፤ በጊዜ ያልተተቸ፤ ይለመዳል። አጉል ልማድ ይሆናል። ሁሉንም ለያይቶ ለመጻፍ ደግሞ፤ ጊዜ የለም። ስለዚህ ባንድ ወንጭፍ ሶስትወፍ ነው ለመማረክ የምጥረው። ከሀተታ ልጀምር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ