የመጨረሻው ሱባኤ
ሙሉነህዮሃንስ (ከሲያትልዋሽንግተን)
የፍልሰታ ልደታ ቀን 2005 ዓ.ም. ተጻፈ
ክፍል አንድ፡- ንግርት፣ የመጨረሻው መጀመሪያ ሱባኤና የመንግስት ትንቅንቅ
በታላላቅ የበቁ የቤተ-ክርስቲያን አባቶች ዘንድ ዘመን የተቆጠረለት የኢትዮጵያን መጻኢ እድል የሚተነብይ ጥንታዊ ንግርት አለ። ኢትዮጵያ እግዚአብሔርን በካዱ ጨቋኝ መንግስታት ለአርባ አመታት ወድቃ እንደምትገዛ በታላላቆቹ የኢትዮጵያ ገዳማት አባቶች በለሆሳስ ሲነገር ከርሟል። ይህ ዘመን የሚቆጠረው ጃንሆይ ከተፈናቀሉበት ዘመን ምሮ ነው። ይህም ሲሰላ መነሻው 1966 ዓ.ም. መሆኑ ነው። አዎን አርባ አመት ከዛ ላይ ስትጨምሩ የዘመን ባቡር በፍጥነት የፊታችን መስከረም 2006 ዓ.ም. ላይ ያደርሰናል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ግርማ ሞገስ


