ይድረስ ለክቡር ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

 

በዘውገፋንታ (ሲያትል)

በዚህሐምሌወር (2005 /) የጻፉትን እንደተለመደው በጉጉት ማንበብ ጀምሬ በመንሰፍሰፍ ጨርሻለሁ። መልዕክቶችዎ ብዙ ዘመን የሸፈናቸውን ትዝታዎች እንዳስታውስና ብዙ ትውስቶችን እንዳሰላስል አድርጎኛል። ብዙ ሆድ የሚያባቡ ሃሳቦች ነበሩ። የአብዘኽኘው ሰው ስሜት እንዴት እንደሆነ ባላውቅም፣ ሁላችንም ያለንበት ጀልባ አንድ፣ ያለንበት ባሕር አንድ፣ ጉዞአችንና አቅጣቻችን እንዲሁ አንድ ነው ብየ ስለማምን ያንዱ ስሜት የጋራ ነው ብዬ ገምቻለሁ።(ሙሉውን ጽሁፍ በፒ.ዲ.ኤፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ)

ከኦሮሞ ፖለቲካ ወደ ጁዋር ፖለቲካ

መስፍን ነጋሽ

ወንድሜ ጁዋር መሀመድ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በኦሮሞ ፖለቲካ እና አሁን ደግሞ ስለኦሮሞ-ኢስላም ያቀረባቸው ንግግሮች ኮርኳሪ ሆነዋል። ኮርኳሪነታቸው የሚመነጨው ግን ሐሳቦች አዲስ ስለሆኑ አይደለም፤ በአቀራረባቸውም ቢሆን ያልተለመዱ አይደሉም። "የአግራሞቱ" ወይም የንዴቱ ምንጭ ጃዋር የገነባው ወወይም እየገነባው የመሰለን የፖለቲካ ማንነትና በቅርብ ያንጸባረቃቸው አቋሞቹ እጅግ የሚቃረኑ ስለሚመስሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሚወለዱበት፣ የሚሞቱለትና የሚሞቱበት መሬት (ሊያነቡት የሚገባ)

/መሰፍን/ማርያም

የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ -ሌላ- እንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዲሲዎችን ለቀቅ!

ከተፈሪ በላይ (የዲሲ ነዋሪ)

ይህን መጣጥፍ እንዳዘጋጅ የገፋፋኝ ጋዜጠኛ አቶ ክንፉ አሰፋ በኢትዮ ሚድያ በኢትዮጵያ ዛሬና EMF ድረ ገጽ ላይ ዲሲን ለቀቅን አስመልክቶ “ዲሲ 2013” በሞል ርእስ የጻፈውን ጽሁፍ ነው። ከጽሁፉ መግነቢያ ላይ ተገለጸወን ሃተታ ማለትም ፈረንጆች በአገራችን ኢትዮጵያ በቆዩ ቁጥር የሚጽፉት ያጣሉ የሚልወን አባባል ባልቀበለውም ወግ ለማጣፈጫ እንደገባ ቅመም ልቁጠረውና ልለፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዲሲ 2013

ክንፉ አሰፋ

ስለ ኢትዮጵያውያን ብዙ የሚያውቁ ፈረንጆች ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ጠንቀቆ ማወቅ በጣም አስቸጋሪ እና ከባድ እንደሆነ ይናገራሉ። "ስለ ሕዝቡ ለመጻፍ የሚፈልግ አንድ ሰው ኢትዮጵያ በገባ ማዕግስት አንድ መጽሃፍ ሊጽፍ ይችላል፤ ይህ ሰው ሳምንት ሲቆይ አንድ መጣጥፍ ይጽፋል፣ ወር ሲቆይ ግን የሚጽፈው ይጠፋበታል።" ይላሉ። ይህ አባባል በከፊል ትክክል ይመስለኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስደት ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን

ታክሎ ተሾመ

በየዓመቱ ከግንቦት 6 እስከ 20 ቀን 2013 እ.ኤ.አ. ድረስ የስደተኞች ቀን ታስቦ እንደሚውል ይታወቃል። ስለሆነም የዚህች አጭር ጽሁፍ ዓላማ በሱዳን የስደተኞች ኑሮ ምን ይመስል እንደነበር አንዳንድ የኑሮ ትዝታዎችን ተመልሰን እንድናስታውስ ይረዳ ዘንድ ለመዳሰስ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ