ከዚህ በኋላ ቀጣዩ ጉዟችን (ወይም መቆሚያችን) ወዴት ነው?

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

በዴሞክራሲ የአንድነት ጎዳና ላይ?

በጁን 2012 “ኢትዮጵያ፡ በሕገመንግስታዊ ዴሞክራሲ ጎዳና ላይ” የሚል ጦማር አቅርቤ ነበር። “በርካታማ ሕበረሰቦች ከጭቆና ወደ ዴሞክራሲ ሽግግርን ሲያስቡና ሲንቀሳቀሱ፤ እንቅስቃሴያቸውን የሚገቱ በርካታ ፈተናዎች” እንደገጠሟቸው በማስረጃ የተደገፉ ታሪካዊ እውነታዎችን ጠቅሼ ነበር፦

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቀባሪ ያጣው የወያኔ/ኢህአዴግ አገዛዝና ባለቤት የሌላት ኢትዮጵያ

ፊልጶስ

እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ ሀገርንና ትውልድን የሚያጠፋ እኩይ አመለካከትና ምግባር ይዞ ተነስቶና ተሳክቶለትም የሚገዛ ከኢትዮጵያ ውጭ በዓለም ላይ ያለ ሀገር የለም። የሚገዛ ህዝብም የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግ የገዛ ወገኑንና ሀገሩን በጠላትነት ፈርጆ፣ ታጥቆና ተደራጅቶ የሚወጋና የሚያፈራርስ የለም። እንደ ወያኔ/ኢህአዴግዊ አገዛዝም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊንን የማጥፋቱንና የመበታተኑን ምግባር እንዲያቆም እሽሩሩ የተባለና እየተለመነ ያለ የለም። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቦይ ስብሐት ነጋ “ይሰቀሉ፣ ሞት ይገባቸዋል!” የሚል የበቀል መንፈስ ከወዴየት ነው!?

አቶ ስብሐት ነጋ Ato Sebhat Negaፍቅር ለይኩን

አቦይ ስብሐት ባለፈው ሳምንት “ከላይፍ” ወርኻዊ መጽሔት ጋር ያደረጉትን ሰላም ሰላም የማይሸት፣ ፍቅርን የተራቆተ፣ የይቅር ባይነት መንፈስ ፈፅሞ የተለየው፣ በቀልንና ጥላቻን የሚሰብክና “ዕርቅ ለመፈጸም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሶች ስቅላት፣ ሞት ይገባቸዋል!” የሚል የሞት ፍርድ አዋጅን የሚያስተጋባ የሚመስል ቃለ-መጠይቃቸውን እያዘንኩም፣ እያፈረኩም ለማንበብ ተገድጄያለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕግ ካልሰራ ጉልበት አማራጭ ይሆናል

ይኸነው አንተሁነኝ

“ጠባብ ብሔርተኛው ድርጅት ወያኔና ጭፍን ተከታዮቹ ለህሊና ዳኝነት በተለይም ለሕግ የበላይነት ያላቸው አመለካከትና ክብር እስከ ምን ድረስ ነው? ወያኔዎች የነበረውን የዚያን ጊዜውን የሕግ ሥርዓት “ትክክል አይደለም!”፣ “የሀገራችንን ሕዝብ በእኩልነት ለማስተዳደር ብቃት የለውም”፣ በተለይ እጅግ ጠበው በመነሳት “የኛ” የሚሉትን የትግራይ ሕዝብ ይጨቁናል በማለት የኃይል አማራጭን እንደተከተሉ ሁሉ፤ አሁንስ ተመሳሳይ ምክንያቶችን በማንሳት የኃይል አማራጭን ለመከተል ለወሰነ ሕዝብ ምላሻቸው ምንድን ነው? ...”

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጅሃዳዊ እርምጃን በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩት ሲጋለጡ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ሀገርኛ በሆነ መንገድ ከውስጥ በፈለቁ ጠላቶች ጉልበት የማፈራረስና ከካርታ የማጥፋት ሂደት ሴራ የተፈለገውን ያህል ውጤት ባያመጣም ሀገሪቱን ግን የሁዋልዮሽ እየጎተተ እንደሚገኝ ይታወቃል። ስለምን ብለው እኒሁ የኢትዮጵያ ልጆች እናታቸውን ለመግደል ሀገራቸውን ለማፈራረስ ተነሱ? ፍጻሜያቸውስ ምን ሊሆን ነው? የሚለው ጥያቄ ሁሉንም ሰው የሚያሳስብና የሚገርምም ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማለዳ ወግ … የ"ጅሃዳዊ ሐረካት" ዘጋቢ ፊልም መዘዝ!

ጅሃዳዊ ሐረካት Jihadawi Harekat ለማየት የጓጓነው ዘጋቢ ፊልም

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ አረቢያ

"ጅሃዳዊ ሐረካት" ዘጋቢ ፊልም ”በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ከሃሳብ ያለፈ እቅድ አላቸው" የተባሉት ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ገመና አንጠርጥሮ ሊያሳየን መሆኑን ሞቀ ደመቅ ደመቅመቅ ያለው የኢቲቪ ማስታወቂያ ልባችን አንጠልጥሎት ከርሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፍቅርና አንድነት ያለው ህዝብ ጠላቱን ያሸንፋል

ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)

ባለፈው ሂትለርና የወያኔን መሪዎች ባነጻጸርኩበት ጽሁፍ ላይ መለስ ስብሀት በአማራው ህዝብ ላይ በሰፊው ሊያንቀሳቅሱ የሞከሩት እልቂት አንዴት በሚፈልጉት ልክ እንዳልገፋላቸው ሗላ ላይ እናወጋለን ብየ ነበር። በአለማችን ያሉ ጤናማ መንግስታት በዜጎቻቸው መካከል የመብት ልዩነትና የዘር የቀለም መለያየት፤ ግጭት እንዳይኖር ያለመታከት ይሰራሉ። ይተጋሉ። በኢትዮጵያ ያለው የዲያቢሎሶች መንግስት፤ ሰው በዘሩ ተለይቶ እንዲታወቅ፤ እንዳይስማማም እንዲበላላም ለማድረግ በትጋት ሲሰራ ሀያ ሁለት አመታትን አስቆጠረ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ መቼ ይሆን እራሱን የሚያየው?

ይኸነው አንተሁነኝ

የታየው ድንገት የሚጠፋበት፣ የተፈለገው ለመድኃኒት ያክል እንኳ የሚታጣበት፣ ከኔ ጋር ነው ተብሎ የነበረው ሳይታሰብ የሚለይበትና ስምምነት የተደረሰበት ሳይቆይ የሚፈርስበት ወቅት። ሰዓታት ወቅቶችና ዓመታት ብቻ አይደሉም ትእይንቶችም እንደ ሸማኔ መወርወሪያ እየተምዘገዘጉ ነው። ጎን ለጎን ከአቻ የስልጣንና የደረጃ ጓደኛ ጋር፤ ከላይ ወደ ታች ወይም ከታች ወደ ላይ አለቃ ከምንዝር ምንዝር ካለቃ ሳይለይ የሚቧደኑበት የሚተሻሹበት የሚጓተቱበት ዘመን። ዘመነ ጭንቅ ንትርክ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታደሰ በዛብህ የመርካቶው አይጥ (ክፍል ሁለት)

ታደሰ በዛብህ Tadesse Zolaበልጅግ ዓሊ

ክፍል ሁለት

“የተረፉት በሞቱት ይቀናሉ ...”

“Die Űberlebenden wereden die Toten beneiden ...”

ጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የሚገኘውን የመቃብር ቦታ ግቢ ውስጥ የሚገኝ አዳራሽ አለ። ዜጎቻችንን ከዚህ ዓለም በሞት በሚለዩበት ወቅት አስከሬኑን ወደ ሃገራችን መላክ የተለመደ ቢሆንም፣ አንዳንዴ እንደ ሟች ወይም እንደ ሟች ቤተሰብ ፍላጎት የቀብሩ ሥነ ስርዓት እዚሁ ፍራንክፈርት ውስጥ ይፈጸማል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ