የልጆቼ የጎህዬና የሱመያ፣ የሩቴና የኦማር “ጩኸት”

አብዩ በለው

ዓርብ ሴፕቴምበር 10 ቀን 2010 እ.ኤ.አ. ከሌሊቱ ለሰባት ሰዓት አስር ጉዳይ (12:50 AM) በኢሜል ለማገኛቸው የትየለሌ ወዳጆቼ ለ2003 ዓ.ም. የአዲስ አመት መልካም ምኞት መግለጫ የላኩላቸው መልዕክቴ የሚከተለው ነበር።

“መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላችሁ! እንኳዋን ከዘመን ዘመን በጤና አሸጋገራችሁ! እኔ ግን ከሃሌ ጋር እንዲህ ብያለሁ። ብርቱን ጥዬ አልሻገርም!”

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ አምባገነኖች ጉም ይጨብጣሉ፣ አውሎ ነፋስን ይወርሳሉ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)

የአፍሪካ አምባገነኖች የውሃ ላይ ቤተመንግስተና የውሃ ገደብ ለዘላለም ለስማቸው መጠሪያ ይሆናል ብለው ሲገነቡና ሲያስገነቡ ኖረዋል። ትተው ያለፉት በሕያውነት ጀግነውና ሲወደሱ መኖርን ነበር። ውጤቱ ግን ጉምን መጨበጥ ነፋስን መውረስ ሆኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስ፣ የጳውሎስና የቀ.ኃ.ሥ ፋውንዴሽኖች

የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ እና ፓርላማውሰሎሞን ተሰማ ጂ.

አዲስ ዘመን ጋዜጣ በጥር 9 ቀን 2005 ዓ.ም በፊት-ለፊት ገጹ ላይ የአንድን “አዋጅ መጽደቅ” ዜና አትሞ ነበር። ዜናው አዲስ አይደለም። “የአዋጁን በጆሮ” እንደሚባለው አይነት ነው። ከሁለት ቀናት በኋላ የወጣውም የአማርኛው ሪፖርተር ጋዜጣ ያንኑ ዜና ደግሞታል። ዜናውን ያነበበና የሰማ ሁሉ ወደአእምሮው የሚመጡበት ግዙፍ ጥያቄዎች አሉ። የእነዚህም ጥያቄዎች መሠረታቸው “ከፓርላማው ግልጽነት የጎደለው አሠራር” ጋር የተያያዙ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ እግር ኳስና የደረደሩት ችግሮቹ (ሰሎሞን ተሰማ ጂ.)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድንሰሎሞን ተሰማ ጂ.

የኢትዮጵያን አግር ኳስ በዋናነት የሚፈታተኑት ችግሮች ቁጥር ስፍር የላቸውም። ዋና ዋናዎቹን የስፖርቱን እንቅፋቶች ለማውሳትም ያህል እንሞክራለን። ችግሮቹን በሦስት ረድፍ ደርድሮ ማየቱ ይበጃል። የመጀመሪያውና ዋናው የፖለቲካውና የፖለቲከኞቹ ብልጣብልጥነት ስሜት ነው። ይህም ብልጣ ብልጥነት በአንደኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወቅት ተንፀባርቆ ነበር። ሁለተኛው ችግር ደግሞ፣ የፌዴሬሽኑና የተጫዋቾቹ የብሔራዊ ስሜት የማጣት ችግር ነው። በሦስተኛ ደረጃም ተጠቃሽ የሚሆነው የስፖርት ጋዜጠኞቹና የሕዝቡ ድጋፉን በተገቢው ኹኔታ አለመስጠቱ ናቸው። እነዚህ ችግሮች እርስ በርሳቸው የተያያዙ በመሆናቸው፣ ስለአንዱ ስናነሣ ስለሌላኛውም እያወሳን እንደሆነ ትገነዘባለችሁ። በመጽሔታችን ገጽና ዐምዶች ሙሉ ለሙሉ ተሸፍኖ የማያልቅም ስለሆነ (ራሱን ችሎ ጥናትና ምርምር ያስፈልገዋል)፣ ቀሪዎቹን ነጥቦች እናንተ አንባቢያኑ በጎደለ እንድትሞሉልን በትህትና እንጠይለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የህወሓት መሪዎች "የኢትዮጵያ ታሪክ እንደገና መፃፍ አለበት!" ይላሉ፣ ለምን??

ገብረመድህን አርኣያ

ህወሓት ከጥንሥሱ ጀምሮ እንደተልዕኮ እና መመሪያው ለዘመናት ከብዙ የውጭ ወረራዎች እና ያልተሳኩ የቅኝ ግዛት ጥረቶች በአባቶቻችን ጽኑ ተጋድሎ የቆየውን ኢትዮጵያዊነት ለማፍረስ፤ ህዝብን በአለም ታይቶ በማይታወቅ የቋንቋ እና የዘር ልዩነት ከፋፍሎ ለብቻው የትግራይን ሪፖብሊክ ለማቋቋም፤ ኤርትራን መገንጠል፤ ትግራይን ከአማራ ቅኝ ገዢዎች ነጻ ማውጣት፤ ኢትዮጵያ የምትባል በአጼ ምኒሊክ የተፈጠረችን አገር ከአለም ካርታ ላይ ማጥፋት፤ የሚሉ እና ሌሎች ዝርዝር ግቦችን እና አላማዎችን አንግቦ የተነሳ ድርጅት እንደነበር …

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሌለ ዲሞክራሲ ይሰጣልን?

ይኸነው አንተሁነኝ

ከታላቋ ሩሲያ መከፋፈልና ከኮሚኒዝም ርዕዮተ ዓለም መንኮታኮት በኋላ ጥቂት የማይባሉ ሀገሮች እና ለለውጥ እንታገላለን ሲሉ የነበሩ ድርጅቶች መመሪያችን ነው እያሉ ሲያመልኩት የኖሩትን የሶሻሊዝም አይዲዮሎጂ፤ የተናገሩት ሳያቅራቸው የጻፉት ሳያሳፍራቸው ባንዲት ጀንበር እርግፍ አድርገው፤ ጥቅም እስከተገኘ ድረስ በሉ የተባሉትን ለማለት ሁኑ የተባሉትን ለመሆን ተሯሯጡ። እጃችሁ ከምን እያሉ ሲያባብሏቸው የነበሩትን የትላንት ወዳጅ መከታ ሀገሮችን ረሱ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊያን ሰደተኞች በአረብ ሀገር… (ግሩም ተ/ሀይማኖት)

በየመን ስደተኛው ላይ ግፉ ቀጥሏል

ብልቱን የተቆረጠ፣ አይኑ የጠፋ፣ጆሮው የተቆረጠ፣ እግር እጃቸው የተሰበረ ልጆች ሀረጥ IOM ካምፕ ውስጥ ያለ ህክምና ይሰቃያሉ

ዕለት ከዕለት በየመን ኢትዮጵያዊያን ስደተኛ ላይ የሚሰራው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትና ግፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ወደ ሀገሬ የገቡት በየመን በኩል ነው እና ወደ ሀገራቸው ሳይሆን ወደ የመን ነው የምመልሰው ብሏል። ማለት ብቻም አይደለ አፍሶ እያመጣ የመን መሬት ቀይ ባህር ዳርቻ እየጣላቸው ነው። ከሳዑዲ ተመላሾቹን ገንዘብ ይዘዋል። ባይዙ እንኳን እዛ ካለ ጓደኛ ወዳጅ ዘመድ ያስልካሉ ብለው እያፈኑ ማሰቃየቱን በግሩፕ የተደራጁት የመናዊያን ገፍተውበታል። ከሳዑዲ ተመላሾቹ ለማምለጥ ሲሮጡ በጥይት ከመምታት ጀምሮ በመኪና ሁሉ እየገጩ በመግደል መጫዎቻ አድርገዋቸዋል። ይህን ስራ በትብብር አብረዋቸው የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ያነጋገርኳቸው ልጆች ነግረውኛል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስ ራዕይ በ”አዲስ ታይምስ” መጽሔት ተተገበረ!!!

ተመስገን ደሳለኝ / Temesgen Dessalegneተመስገን ደሳለኝ

ምንም ጥርጥር የለውም መለስ ዜናዊ ፍፁም አምባገነን ነበር። ምንም ጥርጥር የለውም ከአንድ ክፍለ ጦር በላይ የተለየ ሀሳብን እና ነፃ ሚዲያን ይፈራል። ምንም ጥርጥር የለውም ወራሾቹም ሀሳቡን በነፃነት የሚገልፅን ከመለስ በባሰ መልኩ ይፈራሉ። ይህ ፍራቻቸው ወደ ጭፍን አምባገነንነት ስለቀየራቸው መላ ሀገሪቷን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየገፏት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነፃ የወጣው የኦሮሞ ነፃ አውጪ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ

ቀስ በቀስ ደረጃ በደረጃ የሰከነ የሃሳብ እድገት፣ ብስለትና መረዳት ከዘመናት ለውጥ ጋር መሻሻልን መፍጠሩ እውነት ነው። ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማኖር፣ ይልቁንም ደግሞ በነፃነት ለመኖር ከወራሪዎች ጋር በተደረገ ትግል ሁሉ ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ ተንቀሳቅሰዋል። ለዚህ ታሪክ ሥሪት የኦሮሞ ልጆች ያልከፈሉት መስዋዕትነት አልነበረም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታደሰ በዛብህ የመርካቶው አይጥ

Tadesse Sőhl ታደሰ በዛብህበልጅግ ዓሊ

ታደሰ በዛብህ በተወለደ በአስራ አንድ ዓመቱ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር - መስከረም 26/1981 ራሱን በማጥፋት ከዚህ ዓለም ተለየ።

ስለ ታደሰ በዛብህ ለመጻፍ ካሰብኩ ብዙ ጊዜ ነው። ቀን ሞልቶልኝ ተሳክቶልኝ አልጻፍኩትም። ሰሞኑን ሁለት ገጠመኞቼ ታደሰን እንደገና እንዳስበው አደረጉኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ