የዳያስፖራው ፖለቲካ ቆሽሿል - ተሃድሶ ይስፈልጋ

አማኑኤል ዘሰላም

“ESAT is tasked to produce accurate and balanced news and information” ይላል የኢሳት ኤዲቶሪያል ፖሊሲ። ኢሳትን የሚያዳምጠው ሰው ጥቂት እንደማይሆን አስባለሁ። እስቲ በኢሳት የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን እንመዝናቸው። ምን ያህል ሚዛናዊ፣ በእውነት ላይ የተመሰረተ፣ የሁሉን ወገኖች አስተያየት ያንጸባረቀ ዜናና ትንታኔ ይቀርባል? ምን ያህል በአገራችን ኢትዮጵያ መቀራረብ፣ ፍቅር፣ አንድነት እንዲሰፍን ይረዳል?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኳስና ፖለቲካ

የኢትዮጵያዊነት ልዩ ውበትና አንድነት እስከ ፖለቲካዊ፣ ኃይማኖታዊ፣ የመብት ጥያቄዎችና ተቃውሞዎች የተንጸባረቁበት 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ

Sports had the power "to change the world ... to inspire ... to unite people." - Nelson Mandela

ፍቅር ለይኩን

የ998ቱ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት የተካሄደው የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ በዓለም አቀፉ የፖለቲካ መድረክ ስፖርት ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለአንድነት … ወዘተ ያለው አዎንታዊ ፋይዳ በግልፅ የታየበት መድረክ ሆኖ ነበር ያለፈው። በአንድ ቡድን ተደልድለው የተገናኙት በጥንታዊ ስልጣኔዋኗ እስከ አስር ሺህ ዘመን በሚመዘዝ ግዙፍ ታሪኳ፣ ታላቅ የሆነ ብሔራዊ ኩራትና ስሜት ያላት ጥንታዊቷ ፋርስ የዛሬዋ ኢራን ብሔራዊ ቡድን፣ ከአሜሪካ አቻዋ ጋር በተፋጠጡበት መድረክ፣ የትናንትነዋ ኃያል ኢራንና የዘመናችን ልዕለ ኃያል አገር አሜሪካን ያገናኘ ልዩ አጋጣሚ ሆኖ ነበር ያለፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ህወሐት ለሁለት ተሰነጠቀ፤ ወረቀት ለአባለት ተበተነ

እየሩሳሌም አርአያ

ዛሬ በመቀሌ ለአባላትና አልፎም ለህዝቡ በተበተነ የትግርኛ ፅሁፍ እነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሐዬ፣ ፀጋዬ በርሔ ከነባለቤታቸው እንዲሁም ሌሎች ከድርጅቱ እንዲባረሩ በተበተነው መግለጫ ተጠቁሞዋል። በመግለጫው፥ ከጀርባ አሉ የተባሉትና « የዚህ መኅንዲስ» ተብለው የተፈረጁት ስብሃት ነጋ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ከተባሉት መካከል በዋነኛነት ተፈርጀዋል። እነ ቴውድሮስ ሃጎስ፣አዜብ መስፍንና በረከት እጃቸው እንዳለበት የተነገረለት ይኸው መግለጫ ተከታዩን ይመስላል፤

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎችና አባ ዝምታዎች ትንሣኤ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

በአቦሸማኔዎች ምድር የጉማሬዎች (አባ ዝምታዎች) ዓለም

በአዲስ ዓት መግቢያ ጦማሬ ላይ 2013ን “የኢትዮጵያ የአቦሸማኔ ዓመት”(የወጣቶቹ) ብዬው ነበር። በዚህ ዓመትም የኢትዮጵያን ወጣቶች ለማስተማር፤ ባሉበት ለመድረስ፤ ለማሳሰብም ቃል ገብቼ ነበር። የኢትዮጵያም የምሁራን አምባ ይህንኑ ለማድረግ ጥረት እንዲያደርጉ ተማጽኜ ነበር (በተለይም በከፍተኛው ጣርያ ላይ ያለነውን ምሁራን)። በተመሳሳይ ወጣቱን እንዲደርሱት አሳስቤም ነበር። ከዚህ ባለፈም ተማጽኖዬ ከሰፊው የጉማሬ ትውልድ ጋር (መንገዱ የጠፋው ትውልድ) እራሱን በማግኘት መስመሩን አስተካክሎ ጉዞውን እንዲያሳምርና ወጣቱን እንዲረዳ ምኞቴን አስታውቄ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አማናዊ ‘ሕዳሴ’ ይሉሃል ይኼ ነው!!

ኤፍሬም እሸቴ

ከዚህ በፊት አንዲት ተውሼ ለራሴ ያሻሻልኳትን ግጥም ነግሬያችሁ ነበር። የግጥሟ ባለቤት የአብዬ መንግሥቱ ለማ አባት የኔታ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ ናቸው። መጽሐፋቸው በድጋሚ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስለታተመ ምራቁን የዋጠ፣ ታሪክ የሚወድ፣ ማንነቱን የሚፈልግ ማንም ኢትዮጵያዊ ሊያነበው የሚገባ “ባዮግራፊ” ነው። አገር ቤት የሚሄድ የአሜሪካ ነዋሪ ባገኘኹ ቁጥር “ይኼንን መጽሐፍ ሳትገዛ/ዢ እንዳትመጣ/ጪ” እላለኹ። አንዴ ያነበበው መድገሙ እንደማይቀር እርግጠኛ ነኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሒትለርና አይሁድ፤ መለስ፤ ስብሀትና አማራ

ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)

ውድ አንባቢያን “ዘራፊ ሚሊየነሮች” ለሚለው ጽሁፍ ካደረሳችሁኝ መልሶች አጠር ያለውን አንዱን እንመልከትና ወደሚቀጥለው ጉዳይ እናመራለን። ወዳጄ ስለነዚህ እርጉም ሰዎች የጻፍከዉን ከማህደሬ አዉጥቼ ዛሬ አነበብኩት። እግዜር ይስጥህ። ምን እላለሁ። አፍዝ አደንግዝ እንደተደረገብን ሁሉ ዝም ብሎ ማየት ሁኗል ።ጉርሻ በሚሸጥበት አገር ሰዉ በቁንጣን አለቀ ሲሉን ለማመን ይዳዳናል። ምን አይነት እርጉም ወራዳ ትዉልድ እንደሆንን ነዉ የሚያሳየዉ። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቤተክርስቲያናችንን እናድን!! መስጊዳችንንም!!

ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ

ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ፣ ለእጅግ ረጅም ዘመናት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይና ውስጥ ስላለው የሰላም መደፍረስና ጠንቁ መፍትሔ ይሆናል ብለው የሚያምኑበትን ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ልከዋል። ዕቅዱ አንድ ሲኖዶስ ብቻ እንዲኾን፣ ሲኖዶስ ፓትሪያርኩን እንዲመርጥ፣ ገዥዎቹ ሕገ መንግሥታቸውን እንዲያከብሩ የሚሉትን ያካትታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለኢንተርኔት ድረ-ገጽ ኃላፊዎች

ከብዕር ስም ጀርባ

ብስራት ኢብሳ (ሆላንድ)

ድሮ የምደግፈው የነአበበ ጉርሙ የመቻል እግር ኳስ ቡድን ከጠፋ ከዓመታት በኋላ በትላንቱ ምሽት ለመጀመርያ ጊዜ የተከታተልኩትን፣ በደቡብ አፍሪካ፣ ብሔራዊ ቡድናችን ባሳዛኝ ሁኔታ በቡርኪና ፋሶ ተሸንፎ ጨዋታው ሲያልቅ፣ ተደብሬ የቴሌቭዥኑን መስመር ከኢሮ-ስፖርት ወደ ደች የዜና መስመር ቀይሬ ከባለቤቴ ጋር የዓለም ዜና ማዳመጥ ጀመርን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዳዊት ከበደ እየበራ ነው እየጠፋ!?

አቤ ቶኪቻው

የቀድሞው አለቃዬ እና የአሁን ወዳጄ ዳዊት ከበደ ሰሞኑን አወዛጋቢ ሆኖ ሰንብቷል። ለምን አወዛገበ? ምን አወዛገበ? እንዴት አወዛገበ? ማንን አወዛገበ…? ወዘተ የሚሉትን ሁሉንም ዘርዝሬ መዝለቄን እንጃ ግን እስቲ ትንሽ ነካ ነካ ላድረግማ፤ ባለፈው ጊዜ ዳዊት ከበደ ስለ ኢትዮ ሚዲያው አበርሃ የፃፈውን ወቀሳ በአውራምባ ታይምስ ድረ ገፅ ላይ አንብቤ ነበር። በኢትዮ ሚዲያ ላይ ስለ ዳዊት ከበደ የወጣውን ፅሁፍ አላየሁትም። የዳዊትን ምላሽ ግን አልወደድኩትም። ይህንን ለዳዊትም ነግሬዋለሁ። ሳስበው ዳዊት ያንን ፅሁፍ ሲፅፍ ክፉኛ ተበሳጭቶ እንደሆነ እገምታለሁ። ምን መገመት ብቻ በደንብ አውቂያለሁ እንጂ …

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ የመን ላላችሁት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች

ሀበሻ በየመን ክፍል 10

ሀገር መግባት ለሚፈልጉ መርዳት ከቻላችሁ…

በግሩም ተ/ሀይማኖት

መጠ ሰው ወገን ወገኑን ሲባላ ወገን ወገኑን ሲረዳ ያያል፡፡ በሁለቱም መንገድ ተሰለፉም አሉ፡፡ አንዱን ይበላሉ አንዱን ይረዳሉ፡፡ ከሁሉ ከሁሉ ግን ወገን ወገኑን ማረዱ፣ ለማጥፋት መቸኮሉ የሚያሳዝን ነው፡፡ በተለይ ለኢትዮጵያዊያን ይሰራል የተባለው ስሙን ኤምባሲ ያደረገው የሆድ አደር ጥርቅም ግሩፕ ወገኑን ሲገፋ እና ሲደፋ ማየት አስጠሊታ ነገር ነው፡፡ ይህን ያልኩበት ምክንያት አለኝ፡፡ ይድረስ ስል ‹‹አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት..›› የሚሉትን አባባል ረስቼው አይደለም፡፡ ወይም ህሊናችሁን በሆዳችሁ እንደ ቀየራችሁት ዘንግቼም አይደለም፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ