የትኛው ጨዋታ ከባድ ይሆናል? የቡርኪናፋሶ ወይስ የናይጄሪያ

አደራ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፖለቲካውን በዚህ ሰሞን ገታ ያድርግልን!!!!!!

ኤፍሬም እሸቴ

ዛሬ ሐሙስ ረዥም ቀን እንደሚሆንብን እገምታለኹ። መች ነግቶ የኢትዮጵያንና የቡርኪናፋሶን ጨዋታ ባየን የሚለው የብዝዎቻችን ሐሳብ ነው። ብሔራዊ ቡድናችን ከዛምቢያ ጋር ባሳየው “ደረጃውን የጠበቀ እግር ኳስ” (World Class football") ምክንያት የዓለምን ዓይን ስቧል። ስለዚህ የሚጠበቅበትም እንደዚያው ደረጃው ከፍ ብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ልማታዊው ኪስ አውላቂ

ክንፉ አሰፋ

የ‘ህዳሴው ቦንድ’ ግዢ ግርግር ሞቅ ብሎ በነበረበት ሰሞን ይነገር የነበረ አንድ ቀልድ አለ። የ‘ማረሚያ’ ቤት ፖሊሶች እና ታጋዮች 500 ብር በሰረቀ ሌባ ላይ ውይይት ያደርጋሉ። ተከሳሹ ብሩን ያላግባብ ይስረቅ እንጂ በገንዘቡ የህዳሴውን ቦንድ መግዛቱ ነው ጉዳዩን ለውይይት የዳረገው። ይህ ሌባ መታሰር የለበትም የሚሉት ታጋዮች፣ ለፖሊሶቹ ያቀረቡት መከራከሪያ ነጥብ “ልማታዊ ሃሳብ” ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኃላፊነታቸውን የዘነጉት ግድ የለሽ ምሁራን

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)

በቅርቡ ናኦም ቺሞስኪ: የኤም አይ ቲ (M.I.T.) ዩኒቨርሲቲ የስነ ቋንቋ ፕሮፌሰርና የአሜሪካ ቀደምት ምሁር፤ ለአልጀዚራ ስለአሜሪካ የቀለም ሰዎችና ምሁራን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ላይ ምሁሮቹ ኃላፊነት ጉድለትና ግድ የለሽነት አንደሚያሳዩ መግለጫ ሰጥተው ነበር። ላለፉት 4 አሰርት ዓመታት የ84 ዓመቱ ቺሞስኪ ተጋፍጠው፤ ኃይለኛና ጉልበተኞች ነን የሚሉትንም በሃቅ አለንጋ ሲሸነቁጣቸው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ“ዝም በል ዳያስጶራ” አዋጅ ከቤተ መንግሥት እስከ ቤተ እምነት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን

ኤፍሬም እሸቴ

በዚህ ሰሞን መቼም ከእግር ኳስ ውጪ ማውራት በሕማማት ስለ ቁርጥና ጥብስ እንደማውራት ሳይቆጠር አይቀርም። እኔም ብሆን ስለ እግር ኳሱ ማውራቱን መች ጠልቼው። በርግጥ ይኼ ሁሉ ወፈ ሰማይ የስፖርት ተንታኝ በየኤፍ.ኤሙ ሲተችበት በሚውለው የተጫዋቾቻችን ብቃት፣ ጥራት፣ የኳስ ጥበብ፣ የሽልማት ዓይነት፤ የተጋጣሚዎቻችን ሁኔታ፣ የተጫዋቾቻቸው ዝና፣ ማን ከየትና ከየትኛው ክለብ እንደመጣ፣ አሰላለፋቸው እና ከኢትዮጵያ ጋር ሲገጥሙ ሊኖራቸው ስለሚችለው አያያዝ ለመተንተን ሙያውም መረጃውም የለኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማፈራረስ ማተራመስ ማሸበር- የወያኔ ታላቁ ራዕይ

ይኸነው አንተሁነኝ

“መካብ ሲያቅት ማፍረስ ሥራ ይሆናል” - ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ወያኔ ላለፉት 21 ዓመታት የሀገራችንን ታሪክ ለማፈራረስና ለመቀየር የቻለውን ሁሉ ሞክሯል። የሕዝባችንን የአልደፈርም ባይነት ወኔ ለመስለብና ለማኮላሸት ያልቆፈረው ጉድጋድ አልነበረም። ሃይማኖታዊ ስርአታችንንና ወጋችንን ለመናድ ብዙ መንገድ በመጓዝ ደክሟል። አብሮ በመቻቻል የመኖር ወጥ ባህላችንን ለመጨፈላለቅና ለማጥፋት ሞክሯል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማፍረስ አባዜ (ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም)

“መካብ ሲያቅት ማፍረስ ሥራ ይሆናል”

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

በአለፉት ሃያ አንድ ዓመታት፣ በተለይም ከ1997 ዓ.ም. ወዲህ፣ የወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ልዩ መታወቂያው ያደረገው እያፈረሱ መገንባትን ነው፤ ማፍረስ ቀላል ሥራ ነው፤ ጭንቅላትም፣ ማሰብም አይጠይቅም፤ ልብም፣ ስሜትም አይጠይቅም፤ የሚጠይቀው የዝሆን አካልና ጉልበት ብቻ ነው፤ አንድ ቤተሰብ ስንት ዓመት በዚያ ቤት ውስጥ ኖረ? ጎረቤቶች ምን ዓይነት ትስስር አላቸው? በማኅበር፣ በእድር፣ በዝምድና በቤተ ክርስቲያን ወይም በቤተ መስጊድ፣ በመቃብር፣ በሥራ፣ በአጠቃላይ የእያንዳንዱ ሰው ኑሮ ከልደት ጀምሮ የተፈተለበትና የተደራበት ውስብስብ የኅብረተሰብ አካል መኖሪያ ነው፤ ይህንን አካል ለማፍረስ ትንሽ ጭንቅላትና ግዙፍ ጡንቻ ያለው አይቸግረውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጥፋት ራዕይ፤ የክህደት ሌጋሲ

ፍአ

ራዕይም ይባል ሌጋሲ፤ ህልምም ይባል ምኞት አንድ ነገር እውነት ነው። ሰውየው፤ ከተጀመረ ጀምሮ በሰላም ኑሮ እንቅልፍ አግኝቶ ስለማያውቅ ህልም አለመ፤ ራዕይም ነበረው፤ አስቦና መዝኖ ሠራ ለማለት አይቻልም። ከፊቱ ነገ አልነበረችም። ሊባል የሚቻለው፤ የነበረው የጥፋት፤ የማፍረስ፤ የመበተን፤ የክህደት ቅዠት ብቻ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመዳኛ ወቅትና፤ የዕረቀ ሰላም ጊዜ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

የሪፖርተር ድረገፅ ሲዘግብ

“በጎሳ ላይ የተመሰረተ ግጭት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል በመጸዳጃ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍትና በመኝታ ቤት ግድግዳ ላይ፤የተጻፉ አስፀያፊ ክብረነክ ጸሁፎች ከስድስት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ለከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ተጠቂ ዳርጓቸዋል። በርካታዎችንም ለእስር አብቅቷል። ለላለፉት አሰርት ዓመታት፤በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል ግጭቶችን ሲያስነሱ ከርመዋል። ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሀገር ጩኸት እና የታሳሪ ልጆች… አውደ-ዓመት

(በተመስገን ደሳለኝ)

አጀንዳ- ፩

ለምን ይጮኸል?

መልሱ፣ ለምን አይጮኸም ይሆን? …በጠመንጃ አስገዳጅነት፣ ለማይጨበጥ፣ ለማይታይ ‹‹ራዕይ›› ሀገርን፣ ዘመንን፣ ትውልድን፣ እምነትን… ‹‹ገብር›› ሲባል ማን ነው የማይጮኸው? ... የመንግስት ሰራተኛው ይጮኸል፣ የግል ተቀጣሪው ይጮኸል፣ ቀጣሪው ይጮኸል፣ ስራ እጡ ይጮኸል፣ ነጋዴው ይጮኸል፣ ሸማቹ ይጮኸል፣ ሰራዊቱ ይጮኸል፣ ሙስሊሙ ይጮኸል፣ ክርስቲያኑ ይጮኸል፣ ጠንቋዩ ይጮኸል፣ እምነት የሌለው ይጮኸል፣ የተደራጀው ይጮኸል፣ ያልተደራጀው ይጮኸል፣ የጠገበው ይጮኸል፣ የራበው ይጮኸል፣ ፍትህ ያጣው ይጮኸል፣ እስረኛው ይጮኸል፣ እስረኛ ጠባቂው ይጮኸል፣ ታሪክ ይጮኸል….ሰሚ አልባ ጩኸት! እሪ በከንቱ!! ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ለመለስ አለቀስኩ፣ ለምን? ቢሉኝ ..."

Ato Meles Zenawiኤሎን ሳምሶን

ፓውል ኩልሆ "The Alchemist" በሚለው መጽሐፉ እንዲህ ጻፈ፦

ናርሲስ ተወዳዳሪ የሌለው ቆንጆ ወጣት ነበር አሉ፤ ከውበቱ ጋር ፍቅር ስለያዘው በየዕለቱ ወደ አንድ ሐይቅ እየሄደ መልኩን በውሀው ነጸብራቅ ሲያይ ይውላል። አንድ ቀን አጎንብሶ ሲመለከት አንሸራተተውና ሐይቁ ውስጥ ገብቶ ሞተ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ