ምስጢሩ - ፯
ክፍል ሰባት
ወለላዬ ከስዊድን
የጤንነት ምስጢር
ማንም ሕመምተኛ የወሰደው ኪኒን
ያድነኛል ብሎ ከቻለ ለማመን
ስላስተላለፈ ለአዕምሮው መልዕክት
በርግጥም ይችላል ጥሩ ፈውስ ማግኘት
በሰውነትህ ውስጥ ሕመም የሚኖረው
በሽታውን ትኩረት ስትሰጠው ብቻ ነው
የጤና መዛባት ስሜት ከተሰማህ
ሕመሙን አታስፋ ለሰዎች ተናግረህ
ሰዎች ስለሕመም ሲያወሩ ማዳመጥ
መንገዱን መክፈት ነው እንዲባባስ ይበልጥ
ሕመማቸው ጸንቶ ቢወተውቱ እንኳን
በመልካም ነገሮች ለውጠህ ወሬውን
ባነጋገር ብቃት ትችላለህ ማዳን
የአዕምሮ ፈጠራን የአርጅቻለሁ እምነት
ከራስህ መንጭቀህ ይገባሃል ማውጣት
ወጣት ነኝ አሁንም ብለህ በማተኮር
ደስታን ጤናን ይዘኽ ትችላለህ መኖር
ስለዚህ አረጀሁ ብለህ በመጨነቅ
ሕመም እያወራህ ዕድሜህን ከመስረቅ
ራስህ ራስህን በዚህ ዘዴ ጠብቅ
መልዕክትና አስተያየት ካለዎ፣ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ማስታወሻ ለአንባብያን/ት፦ "The Secret" በሚል ርዕስ አውስትራሊያዊቷ ሮዳ ቢየርን ጽፋው፣ ጋሻው አባተ "ምስጢሩ" በማለት ወደ አማርኛ የመለሰውን መጽሐፍ ገጣሚ ወለላዬ የእያንዳንዱን ምዕራፍ ጭብጥ በግጥም እያስነበበን ይገኛል። ይኽ በመጽሐፉ ካሉት አስር ምዕራፎች ውስጥ ሰባተኛው ነው። መጽሐፍን አንብቦ እጥር ምጥን ባሉ ስንኞች በግጥም ማስቀመጥ በኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ያልተለመደ ሥራ ነው። ምናልባትም ወለላዬ የመጀመሪያው ነው የሚል እምነት አለን።
የኢትዮጵያ ዛሬ ዝግጅት ክፍል