በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ክርስቲያን ወገኖቻቸውን እየታደጉ ነው
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የአማርኛው ክፍል በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ክርስቲያን ወገኖቻቸውን እየታደጉ መሆኑ ዘገበ።
የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የአማርኛው ክፍል በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ክርስቲያን ወገኖቻቸውን እየታደጉ መሆኑ ዘገበ።
ፈረንሣይ 24 የተሰኘው የፈረንሣይ ቴሌቭዥን ጣቢያ በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ የኃይማኖት ተቋማት መሪዎች በጋራ በመሆን አይሲስ በሊቢያ በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን ጭፍጨፋ ማውገዛቸውን ዘገበ። የኢትዮጵያ መንግሥት የተገደሉት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ማረጋገጡን አክሎ ዘግቧል። የሟቾችን ቤተሰቦችንም ቃለምልልስ አድርጎላቸዋል።
ናይጄሪያዊቷ ጋዜጠኛ አዴኦላ ፋዩን በአፍሪካ ወቅታዊ ዜናዎች ላይ ተመስርታ በአሸሟሪነት ትታወቃለች። ነዋሪነትዋ በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሲሆን፣ በሣምንት አንዴ በሳህራ ቲቪ ”Keep It Real With Adeola” በተሰኘው ዝግጅቷ ነው የምታሸሙረው። ከዚህ ቀደም የቀድሞዋን ቀዳማዊ እመቤት አዜብ መስፍንን አስመልክታ ባቀረበቻቸው ዝግጅቶች በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ትታወቃላች። በዚህ ቪዲዮ የአፍሪካ መንግሥታትን ሙሰኝነት አስመልክታ ታሽሟጥጣለች።
ሙሉውን አስነብበኝ ..."ፍራንስ 24" የተሰኘው የቴሌቭዥን ጣቢያ ዛሬ ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2007፣ ማርች 13 ቀን 2015 ሪፖርተርስ በተኘው ዝግጅቱ ስለየሕዳሴው ግድብ የ16 ደቂቃ ጥናታዊ ሪፖርት አቅርቧል። ለመመልከት የማጫወቻ ቁልፉን ይጫኑ!
"አሻራ" በአውስትራሊያ የምትታተምና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የምታጠነጥን መጽሔት ስትሆን በዚህ እትም በተለይ በየመን ሀገር ለትራንዚት ባረፉበት ሰዓት በህወሃት መራሹ መንግስት ተጠልፈው ወደ ኢትዮጵያ የተወሰዱት የግንቦት ሰባት ዋና ጸሀፊ አንዳርጋቸው ጽጌ ዙሪያ ላይ በማጠንጠን በሀገር ቤት በእስር ላይ የወደቁትን የዞን ዘጠኝ አባላት የስራ ውጤቶችንና በጡመራቸው ያካተቱትን ስራቸውን መጽሔቷ ታስተዋውቅዎታለች። ሌሎችንም ወቅታዊና አነጋጋሪ ትኩሳቶችን የዳሰሰችውን "አሻራ" መጽሔትን ይህንን በመጫን ያንብቡ
ነገረ ኢትዮጵያ የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን በመሆን በየሳምንቱ ለንባብ የሚያቀርብ ጋዜጣ ነው። (ሙሉውን ጋዜጣ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)
መልካም ንባብ!
በአውስትራሊያ ሜልበርን በየዓመቱ የሚደረገውን የስፖርት ውድድር ምክንያት በማድረግ የምትዘጋጀው "ኢትዮ-ቶርናመንት" መጽሔት ለንባብ በቅታለች። "ኢትዮ-ቶርናመንት" ዓመታዊ መጽሔት በዚህ ዕትሟ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ግዙፍ ሚና የተጫወቱ እንግዶችን ይዛ ቀርባለች።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
በጀርመን ሀገር የሚታተመው "ጥላ" የተሰኘው መጽሔት ሰባተተኛ ዕትሙን ለንባብ አብቅቷል። መጽሔቱ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ሲሆን በሀገራችን የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ...
... ሙሉውን መጽሔት በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!