በ16/07/2001 ዓ.ም. በጀርመን ሬዲዮ የተላለፈውና በሌሎች የግል ጋዜጠኞች አንድነት ፓርቲ 21 የአመራር አባላት ከፓርቲው አግዷል የሚለው ዘገባ ፍፁም መሠረት የሌለው ሐሰት ዜና ነው። አንድነት በዲሞክራሲያዊና በደንባዊ አሠራር በጽኑ የሚያምንና የሚተገበር ፓርቲ ሲሆን፣ የአመራር አባላት መታገድ የብሔራዊ ም/ቤት ሥልጣንና ኃላፊነት መሆኑ በመተዳደሪያው ደንብ አንቀጽ 11.1 እና 11.4 በግልጽ አስቀምጧል። በአንድነት ፓርቲ የመተዳደሪያ ደንብ በብሔራዊ ም/ቤት ሥልጣንና ተግባር ሥር አንቀጽ 11.4 እንደሚደነግገው “የብሔራዊ ም/ቤት አባላት የዲስፕሊን ጉድለት መፈፀማቸው አግባብ ባለው አካል ሲረጋገጥ ም/ቤቱ በ2/3 ድምፅ ይሽራል” ይላል። በዚህ መሠረት በመደበኛ የአሠራር ሂደትና ዲስፕሊን ጉድለት ማንም አመራር አባላት ያለብሔራዊ ም/ቤቱ ውሳኔ ሊሻር ሊታገድ አይችልም። ስለዚህ በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ከአንድነት ፓርቲ 21 ከፍተኛ አመራር ታገዱ የሚለው ትክክል ያልሆነ ሐሰተኛ ዜና መሆኑን ሁሉም እንዲገነዘበው እንፈልጋለን።

 

አንዳንድ መገናኛ ብዙኀን በተለይ የአውራምባ ታይምስ ጋዜጣ የአንድነት አመራር ከሁለት ተሰነጠቀ የሚለው ሌላው መሠረተ ቢስ ዘገባ ሲሆን፣ መልዕክቱም ሙሉ ውሸት ነው። በብሔራዊ ም/ቤት ማንም የአመራር አባል ባልታገደበት ሁኔታ የአንድነት አመራር ከሁሉት ተሰንጥቋል የሚለው ዜና ከበስተኋላው የተደበቀ ዓላማ ያለው ያስመስላል። የኢትዮ-ቻናል ጋዜጣ በተለመደው የውዥንብርና የሐሰት መረጃ ዘገባው በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ሐምሌ 5 ቀን 2001 ዓ.ም. ያልተከሰቱትን ድርጊቶች እንደተደረጉ አድርጎ መዘገቡ የጋዜጠኝነትን ሙያ ምን ያህል እንዳወረደው የሚያሳይ ማሰረጃ ነው።

 

በመሠረቱ የአንድነት ፓርቲ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ነው። የአባላትን ነፃ ሃሳብ፤ ጥያቄና ቅሬታ በመዋቅሩ ውስጥ ደንቡን ተከትሎ ያለ ምንም ገደብ እንዲስተናገድ ያደርጋል። የብዙኀንን አብላጫ ድምፅና ዲሞክራሲያዊ ውሳኔያችን የሚያከብሩትን በደንቡ መሠረት እንዲንቀሳቀሱና እንዲያስተናግዱ ማድረግ የአንድነት አመራር አባላት ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ዲሞክራሲያዊና ደንባዊ አሠራር የአንድነት ፓርቲ የህልውና መሠረት ነው። ስለሆነም በማንኛውም ጊዜ የአንድነት አመራር በአብላጫ ድምፅ የተወሰኑ ጉዳዮች እንዲተገብሩ ዲሞክራሲያዊና ደንባዊ አሠራር እንዲረጋገጥ ያደርጋል። ይህ ሁኔታ በማንም ግለሰብ ወይም አባላት እንዲቀለበስ ጨርሶ አይፈቅድም።

 

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

ሐምሌ 9 ቀን 2001 ዓ.ም.

አዲስ አበባ

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ