ከትግራይ ብልጽግና ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ

"ከሁለት ቀናት በፊት በመቐለ ከተማ የተከሰተው ለአንድ ወጣት ክቡር ሕይወት ህልፈትና ለሁለት ወጣቶች የመቁሰል አደጋ በክልሉ ውስጥ የሰላምና ዲሞክራሲ እጦት ማሳያ ነው" የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ

ከሁሉ አስቀድመን በመቐለ ከተማ በጠራራ ፀሐይ ክልሉን እየገዛ ባለው ፓርቲ በታጠቁ ኃይሎች በጥይት ተደብድቦ በተገደለው ትግራዋይ ወጣት የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እየገለጽን፤ ለቤተሰቦቹ ለወዳጆቹና ለአብሮ አደግ ጓደኞቹ እንዲሁም ለሰላም ወዳድ የትግራይ ሕዝብ መፅናናትን እንመኛለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሽግግር መንግሥት ጥያቄ ቋሚ የትግል አጀንዳችን ሆኗል! (አብሮነት)

አብሮነት

ከአብሮነት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት (#አብሮነት) የተሰጠ መግለጫ

አብሮነት ለኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት (#አብሮነት) ከግንቦት ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ በአገራችን የተከሰተው “የለውጥ ሒደት” መሰረታዊ የአገሪቱን የፖለቲካ ችግሮች ለመፍታት በሚያስችል አግባብ ያልተካሄደና የከሸፈ መሆኑን በመገንዘብ አገሪቱን ወደ አንድ አዲስና ጤናማ የሽግግር ሒደት የሚያስገባ አማራጭ ሐሳብ በረቂቅ ደረጃ አዘጋጅቶ ለሕዝብ ውይይት ማቅረቡ ይታወቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አብን በሽግግር መንግሥትና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያወጣው መግለጫ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ያወጣው መግለጫ

ለመላው የአማራ ሕዝብ፣
ለድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች፣
ለመላው ኢትዮጵያውያን!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሚያዝያ 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የአገራችንን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ምጣኔ ኃብታዊ አውዶችን በጥልቀት በመገምገም፤ የአማራ ሕዝብን ወቅታዊ አቋምና ዘላቂ ጥቅሞችን፤ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ኃይሎች ፍላጎቶችን እና የቀረቡ አማራጮችን በፅሞና በመመርመር፤ በዚህም መሠረት፦

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ምርጫ 2012ና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የሰጡት መግለጫ

PM Abiy Ahmed

ክቡራንና ክቡራት ኢትዮጵያውያን፤

በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ጎልተው ከወጡ የሕዝብ ፍላጎቶች አንዱ ሕዝብ የሚሳተፍበትና የሚሰማበት የአስተዳደር ሂደት፣ በሌላ አነጋገር ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የመገንባት ፍላጎት ነው። ይህ ፍላጎት ከዘመን ወደ ዘመን እያደገ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ዛሬ ላይ ደርሷል። በዚህ ባለንበት ዘመንና ትውልድ ይህ ፍላጎት እውን ሆኖ ዲሞክራሲያዊ አገር እንድንገነባ ትልቅ ፋይዳ የሚኖረው አንዱ ኩነት ቀጣዩ ጠቅላላ አገራዊ ምርጫ መሆኑ ግልጽ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከኢዜማ የተሰጠ የአቋም መግለጫ (ሚያዝያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም.)

ኢዜማ

የምንሰጠው ሕጋዊና ፖለቲካዊ አማራጭ ከወቅታዊው የኮሮና ወረርሽኝ የሚታደገን፣ አገረ-መንግሥቱን የሚያስቀጥልና ወደ ተረጋጋ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የምናደርገውን ሽግግር የሚያግዝ ሊሆን ይገባል!

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሰጠ የአቋም መግለጫ

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከባድ ጉዳት እያደረሰ እንደሆነ ይታወቃል። ወረርሽኙ በሰዎች ጤና እና ደህንነት ላይ ካደረሰው እና እያደረሰ ካለው ጉዳት ባልተናነሰ የዓለምን እና የአገሮችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ መስተጋብሮች እና ሥርዓትን ከባድ አደጋ ውስጥ ከቷል። ወረርሽኙ በአገራችን ኢትዮጵያ እስከካሁን ያስከተለው ጉዳት ከሌሎች አገሮች ጋር ሲነጻጸር አስከፊ የሚባል ባይሆንም የደቀነው አደጋ ግን ከፍተኛ መሆኑ እርግጥ ነው። በሌሎች አገር ከታየው ተሞክሮ አንፃር ወረርሽኙ ድንገት በከፍተኛ ቁጥር ዜጎችን ሊያጠቃ እና የጤና ሥርዓት ቀውስ ውስጥ ሊከተን የሚችልበት አደጋ አሁንም አለ። የጎረቤት አገሮች (ሱዳን፣ ጅቡቲና ሶማሊያ) የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በፍጥነት መዛመት የጀመረበትና በተለይ ከጅቡቲ ጋር ካለን የቀረበ የኢኮኖሚ ትስስር አንፃር በምስራቁ የአገራችን ክፍል ላይ የደቀነው ስጋት ከፍተኛ እንደሆነ ግልጽ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ሕግን ያላግባብ በመተርጎም የብልጽግናን ሕገወጥ የሥልጣን ዕድሜ የማራዘም እንቅስቃሴ ፍጹም ተቀባይነት" ሕወሓት

TPLF (Tigray People's Liberation Front)

ከሕወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የሕወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከሚያዝያ 23-25/2012 ዓ.ም በክልላችንና በአገራችን እንዲሁም በንኡስ ቀጣናው የተከሰቱ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በስፋት በመመርመር የውሳኔ ሐሳቦችን አሳልፏል። ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በክልላችን እየተከናወኑ ያሉ የሰላምና የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የክልላችንና የሕዝባችን ድህንነት የመታደግ ሥራዎችን እንዲሁም የኮረናን ወረርሽኝ ለመመከት የተሰሩ ሥራዎች በሚመለከት በዝርዝር የተወያየበት ሲሆን፣ እስካሁን የታዩ ጥንካሬዎችን ጠብቆ ለማቆየትና የታዩ ጉድለቶችን ለማረም የተሰሩ ስራዎችን በመመርመር ውሳኔዎችን አሳልፏል። በክልላችን ያሉ ወይም የሚኖሩ ፈተናዎች ለመመከት አሁንም ወሳኙ ውስጣዊ ጥንካሬያችን መሆኑን በድጋሚ በማረጋገጥ በዚህ ረገድ የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ስምምነት ላይ ተደርሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአዲስ ማኅበራዊ ውል የምንደራደርበትና የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥትን የማሻሻያው ጊዜ አሁን ነው!

National Movement of Amhara (NAMA)

ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ የቀረበ ታሪካዊ አገራዊ ጥሪ!

• ለኢፌዴሪ ጠ/ሚ/ር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
• ለኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ
• ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
• ለኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት
• ለመላው የአማራ ሕዝብ
• ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች
• ለተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች
• ለዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ሚዲያዎች
• በአዲስ አበባ ለሚገኙ ለኢትዮጵያ ወዳጅ አገራት ኢምባሲዎች፣ ሚሲዮኖችና ዓለም አቀፍ ተቋማት
ክቡራትና ክቡራን፣

በመላው ዓለም የተከሰተውን የሳምባ ቆልፍ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ተከትሎ በኢትዮጵያም አገራዊ የጤናና የማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግር መሆኑን በመገንዘብ በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ይካሄዳል ተብሎ ታስቦ የነበረው 6ኛ ዙር አገራዊ ምርጫ በተያዘለት ጊዜ ማካሄድ እንደማይችልና ምርጫውም ላልተወሰነ ጊዜ እንደተራዘመ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ይህንን ተከትሎ በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት በዚህ አመት መጨረሻ የስልጣን ዘመኑ የሚጠናቀቅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ምን ሊደረግ እንደሚችል በሁላችንም ዘንድ የመወያያ አጀንዳ ሆኖ ሰንብቷል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!