በአልዩሚኒየም ፎይል ተጠቅልሎ ከአገር ሊወጣ የነበረ 132,860 ዶላር ኤርፖርት ላይ ተያዘ
በቦሌ ኤርፖርት ከአገር ሊወጣ የነበረው 132 ሺህ 860 ዶላር
ከአራት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር በላይ ነው
ኢዛ (እሁድ መስከረም ፲፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 27, 2020)፦ በአንድ የዚምባቡዌ ዜጋ ከአገር ሊወጣ የነበረ 132,860 ዶላር በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ።
ኮሚሽኑ ትናንት ባወጣው መረጃ ግለሰቡ ገንዘብ ይዞ ስለመግባቱ ሳያሳውቅ (ኪክሌር ሳያደርግ) 132 ሺህ 860 ዶላሩን ከአገር ለማውጣት ሲሞክር በሴክዩሪቲና በጉምሩክ ኦፊሰሮች ተይዟል።
ግለሰቡ በተለያዩ ዘዴዎች በማሳልፍ ስለመሞከሩ የሚገልጸው መረጃ፤ በተለይ በአልዩሚኒየም ፎይል በመጠቅለል ለማሳለፍ ሲሞክር በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል።
በትናንትናው ዕለት (ቅዳሜ መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም.) የተያዘው 132 ሺህ 860 ዶላር በአሁኑ ወቅት ባለው ሕጋዊ የምንዛሬ ዋጋ ከ4.8 (አራት ነጥብ ስምንት) ሚሊዮን ብር በላይ ነው። (ኢዛ)



