የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ

የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ

ሕዝበ ውሣኔው በሰላም ተጠናቅቋል

ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 23, 2019)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ላይ ኅዳር 10 የተካሔደውን ሕዝበ ውሣኔ ውጤት ዛሬ ኅዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ከሁለት ነጥብ ሦስት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ድምፅ የሠጠበት ሕዝበ ውሣኔ በሰላም የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት በየምርጫ ጣቢያዎቹ የተለጠፈ መኾኑም ታውቋል።

ሆኖም ሕዝበ ውሣኔው ሲዳማ በክልልነት ይደራጅ ውይም በደቡብ ክልልነቱ ይቀጥል በሚል የተደረገው ምርጫ የመጨረሻ ውጤት በምርጫ ቦርድ ይፋ የሚደረገው ዛሬ ይኾናል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ