ሲዳማ 10ኛዋ ክልል
ሻፌታን 98.51 በመቶ ሕዝብ ሲመርጥ፣ 1.48 በመቶው ደግሞ ጎጆ ቤትን መርጧል
98.5 በመቶ መራጭ ክልል እንሁን በማለት መርጧል
ኢዛ (ቅዳሜ ኅዳር ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. November 23, 2019)፦ የሲዳማ የክልልነትን ጥያቄ በተመለከተ ኅዳር 10 ቀን በተደረገው ሕዝበ ውሣኔ ከ98 በመቶ በላይ የሚኾነው መራጭ የሲዳማ ዞን ክልል ይሁን የሚለውን ድምፅ መሥጠቱ ይፋ ኾነ። ይህም ሲዳማን 10ኛዋ የአገሪቱ ክልል ለመኾን የሚያስችላትን እድል መገኘቱን የሚያረጋግጥ ኾኗል።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ኅዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው ውሣኔ፤ ውጤቱ ለመራጭነት ከተመዘገቡት 2.3 ሚሊዮን መራጮች ውስጥ ከ2.23 ሚሊዮን በላይ የሚኾነው መራጭ የሲዳማን ክልልነት የመረጠ ሲሆን፣ በደቡብ ክልል ውስጥ ትቆይ የሚለው 33 ሺህ እንደኾነ ተገልጿል። (ኢዛ)



