ፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለጄኔራሎቹ ማዕረግ ሲሠጡ

ፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለጄኔራሎቹ ማዕረግ ሲሠጡ

ሹመቱን የሠጡት ፕ/ት ሣህለወርቅ ዘውዴ ናቸው

ኢዛ (እሁድ ጥር ፲ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 19, 2020)፦ በጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አቅራቢነት ለ65 መኮንኖች የተለያዩ የጄኔራልነት የማዕረግ ሹመቶች ተሠጡ።

ከእነዚህ ተሿሚዎች ስድስቱ የሌተናል ጄኔራል፣ 19ኙ ሜጀር ጄኔራልና 40ዎቹ ደግሞ የብርጋዲየር ጄኔራልነት ማዕረግ ተሠጥቷቸዋል።

ትናንት ጥር 9 ቀን 2012 ዓ.ም. የተሠጠውን ሹመት በዶ/ር ዐቢይ አቅራቢነት በፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ሹመቱ የተሠጠ ሲሆን፤ በዚህ የሹመት አሠጣጥ ፕሮግራም ላይ የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳና ሌሎች ከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊቱ መኮንኖች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተገኝተዋል።

በዕለቱ ከሜ/ጄኔራል ወደ ሌ/ጄኔራል ማዕረግ የተሾሙት የሚከተሉት ናቸው፤

ሜ/ጄኔራል ፍስሃ ኪዳኑ ፈንታ፣
ሜ/ጄኔራል ጌታቸው ጉዲና፣
ሜ/ጄኔራል ድሪባ መኮንን፣
ሜ/ጄኔራል ይመር መኮንን፣
ሜ/ጄኔራል ደስታ አብቼ፣
ሜ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮ መኾናቸው ታውቋል።

ከብ/ጄኔራል ወደ ሜ/ጄኔራል ማዕረግ ከፍ ያሉትና የተሾሙ አሥራ ዘጠኝ ሲሆኑ ዝርዝራቸው የሚከተለው ነው፤

ብ/ጄኔራል ገ/መድኅን ፍቃደን ኃይሉ፣
ብ/ጄኔራል ኩመራ ነገሪ ገመዳ፣
ብ/ጄኔራል ከድር አራርሳ ይመር፣
ብ/ጄኔራል አሰፋ ቸኮለ እንዳለው፣
ብ/ጄኔራል ደሳለኝ ተሾመ አብተው፣
ብ/ጄኔራል እንዳልካቸው ወ/ኪዳን ደጋ፣
ብ/ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ለሙ፣
ብ/ጄኔራል ሀብታሙ ጥላሁን ሄስቤቶ፣
ብ/ጄኔራል ታደሰ መኩሪያ ዘሪሁን፣
ብ/ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ኛጳ፣
ብ/ጄኔራል ክንዱ ገዙ ተገኝ፣
ብ/ጄኔራል ይርዳው ገ/መድኅን ገ/ፃድቅ፣
ብ/ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በዳዳ፣
ብ/ጄኔራል ሙዘይ መኮንን ተወልደ፣
ብ/ጄኔራል ነጋሲ ትኩዕ ለውጠ፣
ብ/ጄኔራል ተሾመ ገመቹ አደሬ፣
ብ/ጄኔራል ዘውዱ ኪሮስ ገ/ኪዳን፣
ብ/ጄኔራል ጥሩዬ አሰፌ አበራ፣
ብ/ጄኔራል አሕመድ ሀምዛ እንደኾኑ ታውቋል።

ከኮሎኔል ወደ ብ/ጄኔራል ማዕረግ የተሾሙ አርባዎቹ መኮንኖች፤

ኮሎኔል አሊጋዝ ገብሬ በርሄ፣
ኮሎኔል ጎይቶም ፋሩስ በላይ፣
ኮሎኔል አብረሃ መውጫ በየነ፣
ኮሎኔል ፍትዊ ፀሐዬ ገ/እግዚአብሔር፣
ኮሎኔል ይልማ ከበደ ገ/መስቀል፣
ኮሎኔል ጠቅለው ክብረት ይመር፣
ኮሎኔል አብዱሰላም ኢብራሂም ሙሳ፣
ኮሎኔል ዘውዱ ሰጥአርጌ ደነቀ፣
ኮሎኔል መሸሻ አረዳ ሂርጶ፣
ኮሎኔል ሻምበል ፈረደ ውቤ፣
ኮሎኔል ኩማ ሚደቅሳ ሰንበታ፣
ኮሎኔል ሙስጠፋ መሐመድ አብዲ፣
ኮሎኔል አበበ ተካ ወ/ሩፋዮል፣
ኮሎኔል ሚልኬሳ ረጋሳ ኢተፋ፣
ኮሎኔል ግዛው ኡማ አብዲ፣
ኮሎኔል አብድሮ ከድር በናታ፣
ኮሎኔል መለስ መንግሥቴ ንረይ፣
ኮሎኔል መለስ ይግዛው መድፉ፣
ኮሎኔል ያሲን መሐመድ ሲሳይ፣
ኮሎኔል አብደላ መሐመድ ተገኝ፣
ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ዓለሙ፣
ኮሎኔል ይታያል ገላው ቢተው፣
ኮሎኔል ሙሉጌታ አምባቸው ጎሹ፣
ኮሎኔል ተስፋዬ ረጋሳ አመንቴ፣
ኮሎኔል ነገሪ ቶሊና ጉደር፣
ኮሎኔል ጡምሲዶ ፈታሞ ዱባለ፣
ኮሎኔል ፍስሃ ገ/ሥላሴ እኑን፣
ኮሎኔል በርሄ ገ/መድኅን ደመወዝ፣
ኮሎኔል ናስር አባዲጋ አባዲኮ፣
ኮሎኔል ተመስገን አቦሴ ዳቴቦ፣
ኮሎኔል ወርቁ ከበደ ወልደየሱስ፣
ኮሎኔል እናሶ ኢጃጆ አናሾ፣
ኮሎኔል ደረጀ መገርሳ ኢሰታ፣
ኮሎኔል ነገራ ለሊሳ ሙለታ፣
ኮሎኔል ሰብስቤ ዱባ ኡንቲሶ፣
ኮሎኔል ዘላለም ፈተና ቀቀሞ፣
ኮሎኔል ዋለፃ ዋቻ ዋራ፣
ኮሎኔል የሺእመቤት አያሌው፣
ኮሎኔል እርጎ ሺበሺ ሲሳይ፣
ኮሎኔል ሸዋዬ ኃይሌ መኾናቸው ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ