ኮሚሽነር አራርሳ መርደሳ

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር አራርሳ መርደሳ

በቡራዩ ግድያም የኦነግ ሸኔ አባሎች መኾናቸው ተጠቁሟል

ኢዛ (እሁድ የካቲት ፲፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 23, 2020)፦ በአምቦ የተፈጸመውን የቦምብ ጥቃት በኦነግ ሸኔ የተፈጸመ ስለመኾኑ ተጠቆመ። ይህንን የገለጹት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር ጥቃቱን ካደረሱት ተጥርጣሪዎች መካከል ይህንን የሚያረጋግጥ መረጃ በመገኘቱ ነው ብለዋል። በቡራዩ ግድያም የኦነግ ሸኔ አባሎች መኾናቸው ተጠቁሟል።

ማምሻውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳስታወቁት፤ በተወረወረው ቦምብ ጥቃት የደረሰባቸው 29 ሲሆኑ፣ 28ቱ የሕክምና እርዳታ ተደርጎላቸው ወደቤታቸው ተመልሰዋል። አንደኛው ግለሰብ በአምቦ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ መኾኑን ኮምሽነር አራርሳ መርደሳ ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ ጨምረው እንደገለጹት ጥቃቱን በመፈጸም የተጠረጠሩ ስድስት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ተይዘዋል።

ኮሚሽነሩ ከትናንት በስቲያ በተፈጸምው ጥቃት በቡራዩ ከተማ የአስተዳደርና የጸጥታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ሰለሞን ታደስ ግድያና በሌሎች ሦስት ግለሰቦች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል የተባሉ 17 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውንም አረጋግጠዋል። በቡራዩ የቆሰሉት ሦስት ናቸው።

በኦሮሚያ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የሥራ ኃላፊዎች ላይ ያነጣጠሩ ግድያዎች መበራከታቸው ይታወቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ