“ድሃ ወገኖቻችን አንጀታቸውን ቋጥረው በሠሩት ግድብ አንደራደርም!”

“ድሃ ወገኖቻችን አንጀታቸውን ቋጥረው በሠሩት ግድብ አንደራደርም!”

“ዓባይ የእኛም ጭምር ነው” ኢትዮጵያውያን

ኢዛ (ሐሙስ የካቲት ፲፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 27, 2020)፦ በታላቁ ህዳሴ ግድብና በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ የአሜሪካ መንግሥት አድሎአዊ ጣልቃ ገብነት በመቃወም፤ ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ የሚካሔደው ሰልፍ ተጀምሯል። በዚህ ሰልፍ ላይ ኢትዮጵያውያን “ዓባይ የእኛም ጭምር ነው!” ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያውያኑ፤ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን አድሎአዊ ጫን እንድታቆም ብቻ ሳይሆን፤ ከአደራዳሪነትዋ እንድትወጣ የሚጠይቁበት ነው።

በሰልፉ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች ውስጥ፤

“ፕ/ት ትራምፕ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መብት አይግፈፉ!”፣

“አሜሪካ የግብጽን የቅኝ ግዛት ውል መደገፍዋን ማቆም አለባት! ”፣

“ሚስተር ሴክሬታሪ፣ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በዓባይ ላይ ፍትሐዊ ድርሻ ይገባቸዋል!”፣

“ሚስተር ሴክሬታሪ፣ ዓባይ የእኛም ጭምር ነው”፣

“ምንም ልዩነት ይኑረን፤ በዓባይ ጉዳይ አንድ ነን!”፣

“ዶ/ር ዐቢይ፣ 200 ሚሊዮኖች ዓይኖች እያዩህ ነው! ብሔራዊ ጥቅማችንን እንዳትሠጥ!”፣

“መንግሥት የሕዝብ ንብረት ስለኾነው የዓባይ ጉዳይ በግልጽ ለሕዝብ ማሳወቅ ይጠበቅበታል!”፣

“ዓባይ ግድብ ብቻ አይደለም፤ የኢትዮጵያውያን ሕልውና ነው!”፣

“ፕ/ት ትራምፕ፣ ኢትዮጵያን መጫን ያቁሙ!”፣

“ድሃ ወገኖቻችን አንጀታቸውን ቋጥረው በሠሩት ግድብ አንደራደርም!” … የሚሉ ይገኙበታል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ