የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በጎበኙበት ወቅት

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ የታላቁ ህዳሴ ግድብን በጎበኙበት ወቅት

ግድቡን ከማንኛውም ጥቃት ለመጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ መዘጋጀታቸውን ገለጹ

ኢዛ (ሐሙስ መጋቢት ፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. March 12, 2020)፦ በህዳሴ ግድብ ላይ ጥቃት እንዳይሰነዘር ለመከላከልና ለመመከት የጦር ኃይሉ ከምንግዜውም በላይ ዝግጁ መኾኑን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ይህንን ያስታወቁት የጦር ጄኔራሎችንና የመከላከያ ሠራዊትን ከፍተኛ አመራሮች ይዘው የታላቁ ህዳሴ ግድብን ከጎበኙ በኋላ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጉብኝቱን አስመልክቶ ባሰፈረው መረጃ፤ የጦር ኃይሉ በግድቡ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውንም ጥቃት እመክታለሁ ማለቱንም ገልጿል።

ጉብኝቱ የጦር ኃይሉ የአገርን ሉአላዊነት ለማስከበር ያለውን ዝግጁነት የሚያረጋግጥበት መኾኑን ጄኔራል አደም መግለጻቸውንም አስታውቋል።

አያይዞም በጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ጄኔራል አደም መሐመድ የተመራው የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች፤ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ከኾኑት ከዶ/ር አብርሃም በላይና ከውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ከዶ/ር ስለሺ በቀለ ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ