በቤትና በመሥሪያ ቤት ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር መያዝ ተከለከለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ
ሕጉን የጣሰ ይቀጣል
ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 18, 2020)፦ ከአሁን በኋላ በግለስብም ኾነ ኩባንያዎች በቤታቸው ወይም በመሥሪያ ቤቶቻቸው ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ መያዝ የማይችሉ መኾኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ማክሰኞ ነኀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቀ።
ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ ይዞ የተገኘ በሕግ የሚጠየቅ መኾኑንም የባንኩ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል። (ኢዛ)