የብር ኖቶችን በአግባቡ አለመያዝ ሊያስቀጣ ነው

የኢትዮጵያ የብር ኖቶች
የብር ኖቶች ላይ መጻፍም ኾነ ምልክት ማድረግ ተከለከለ
ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 18, 2020)፦ የብር ኖቶችን በአግባቡ አለመያዝ ሊያስጠይ የሚችልበት አዲስ መመሪያ ተግባራዊ ማድረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዛሬው ዕለት አስታወቀ።
የባንኩ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ዛሬ ማክሰኞ ነኀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. እንዳስታወቁት፤ በብር ኖቶች ላይ መጻፍ ወይም ምልክት ማድረግና ብርን በአግባቡ አለመያዝ ከዚህ በኋላ ያስቀጣል። (ኢዛ)