የደመራ በዓል በአዲስ አበባና በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል

የደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሲከበር (ቅዳሜ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም.)
በመስቀል አደባባይ ከ5-6 ሺህ ታዳሚዎች ተገኝተዋል
ኢዛ (ቅዳሜ መስከረም ፲፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 26, 2020)፦ የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው። ሐረርን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በዓሉ እየተከበረ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ከተማ በዓሉ ከዚህ ቀድም ሲከበር ከነበረው በተለየ ሁኔታ ከአምስት እስከ ስድስት ሺህ በሚገመቱ ምእመናንና የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ብቻ እንዲከበር በመወሰኑ፤ በዚሁ ውሳኔ መሠረት በዓሉ እየተከበረ ነው። (ኢዛ)