ምርጫ 2013

ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ 2013፣ ባሕር ዳር ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም.

ረዣዥም ሰልፎች በየቦታው እየታዩ ነው
የምርጫ ሒደቱ አለመፍጠን ቅሬታ እያስነሳ ነው

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 21, 2021)፦ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ 2013 ዛሬ ማለዳ ምርጫ በሚካሔድባቸው የአገሪቱ ክፍሎች ድምፅ መሰጠት ቢጀምርም በብዙ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ሒደቱ ፈጣን ካለመኾኑ ተያይዞ መራጮች ቅሬታ እያቀረቡ ነው።

በአንዳንድ አካባቢዎችም መራጮች ቀድመው የተገኙበትና አስመራጮች ግን በመዘግየታቸው ምርጫው እስከ አንድ ሰዓት አካባቢ የተጀመሩባቸው ጣቢያዎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

እንዲህ ዐይነቱ ችግር በአዲስ አበባ፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በአዳማን የመሳሰሉት ከተሞች የታዩ ናቸው። ከዚህ ውጭ እስካሁን ባለው ሒደት ምርጫው በሰላማዊ ሁኔታ እየተካሔደ ይገኛል።

ኾኖም አሁንም ድረስ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ረዣዥም ሰልፎች እየታዩ ነው። ይህም ፈጣን በኮነ ሁኔታ መራጮች እየመረጡ ያለመኾኑን ያሳያል።

ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ 2013፣ ባሕር ዳር ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም.
ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ 2013፣ ባሕር ዳር ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም.

ዘጠኝ ፓርቲዎች በሚሳተፉበት የባሕር ዳር ምርጫ ክልል ከፍተኛ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በዚህ የምርጫ ክልል ከ137 ሺህ በላይ መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ