ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ምርጫ 2013)

በመራጮች ምዝገባ ሒደትና በሌሎች ክንውኖች ላይ በተፈጠረው መዘግየት ምክንያት መኾኑ ተገልጿል

ኢዛ (ቅዳሜ ግንቦት ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. May 15, 2021)፦ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደሚካሔድ የሚጠበቀው ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ 2013 በሦስት ሳምንታት ሊራዘም እንደሚችል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ይህንን ያስታወቀው በመራጮች ምዝገባ ሒደት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት እያደረገ ባለው መድረክ ላይ ነው።

በዚሁ ጉዳይ የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደገለጹትም፤ በመራጮች ምዝገባ፣ ሒደትና በሌሎች ክንውኖች ላይ የተፈጠረው መዘግየት የድምፅ መስጫ ቀኑን ሊገፋው እንደሚችል ነው።

በዚህ መሠረት የድምፅ መስጫው ጊዜ በሁለትና ሦስት ሳምንታት እንደሚራዘም ለማወቅ ተችሏል።

በቦርዱ መረጃ መሠረት እስከ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ለቦርዱ በደረሰው መረጃ መሠረት ለመምራት የተመዘገቡ ዜጎች ቁጥር ከ36 ሚሊዮን በላይ ደርሷል። የመራጮች ምዝገባ ትናንት መጠናቀቁ ይታወቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ