Birtukan Mideksa

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ

- በደቡብ የምርጫ መገልገያ የያዘ ሳጥን በመሰረቁ፣ የምርጫ ጣቢያው አልተከፈተም
- ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 21, 2021)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ 2013 አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ሕገወጥ ተግባራት መታየታቸውን አመለከቱ። በደቡብ ክልል “ኡባ ደብረፀሐይ” በተሰኘ የምርጫ ጣቢያ፤ ለጣቢያው የሚያገለግል ሰማያዊ ሳጥን ተሰርቋል መሰረቁን ገልጸዋል።

ሰማያዊው ሳጥን ለአንድ የምርጫ ጣቢያ የሚያገለግሉ የምርጫ ቁሳቁሶችን ያሟላ ሳጥን ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት በኡባ ደብረፀሐይ የምርጫ ጣቢያው አለመከፈቱ ታውቋል።

ዛሬ ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ከንጋቱ 12 ሰዓት ምርጫው እየተካሔደ መኾኑን የገለጹት ወ/ት ብርቱካን፤ ነገር ግን በአንዳንድ ቦታዎች ሕገወጥ ተግባራት መኖራቸውን ጠቁመው፤ በአማራ እና በደቡብ ክልሎች የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የእጩ ተወዳዳሪ ወኪሎቻቸውን ማንቀሳቀስ እንዳልቻሉ የደረሳቸውን ሪፖርት መሠረት አድርገው አስታውቀዋል። በመኾኑም የትኛውም የአስተዳደር መዋቅር ችግሩን መፍታት እንደሚኖርበትም አስረድተዋል።

በምርጫ ቦርድ በኩልም አለ የሚባለውን ችግር ለመፍታት እየተሠራ ስለመኾኑ የገለጹት የቦርዱ ሰብሳቢ፤ በምርጫው ሒደት ሕገወጥ ተግባራትን የሚፈጽሙ አካላት አድራጎታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ