Ethiopia Zare (ሰኞ ነሐሴ 25 ቀን 2001 ዓ.ም. August 31, 2009)፦ በየዓመቱ በሰሜን ምዕራብ የአሜሪካ እና የካናዳ ሀገራት የሚካሄደው የእግር ኳስ ስፖርት ውድድር በሜትሮ ቫንኩቨር ብሪቲሽ ኮሎምቢያ ይካሄዳል።

 

ይሄው በየዓመቱ በወርሃ መስከረም የመጀመሪያ ሣምንት የሚካሄደው ውድድር በሲያትል፣ ቫንኩቨር፣ ካልጋሪ፣ ኤድመንተን፣ ዌኒፔግ፣ ቪክቶሪያ እና ፖርትላንድ ነዋሪ የሆኑ ኢትየጵያዊያን የሚያካሂዱት የእግር ኳስ ውድድር ከ14 ዓመት በላይ ሲካሄድ የነበረ ሲሆን፤ የያዝነውን ዓመት ቫንኮቨር አስተናጋጅ መሆኗን ለማወቅ ችለናል።

 

ውድድሩ በፖርትላንድ ኦሬጋን ሊካሄድ ፕሮግራም ተይዞ የነበረ ቢሆንም፤ ሳይሳካ በመቅረቱ የዓለም አቀፉ 2010 ዊንተር ኦሎምፒክ አስተናጋጅ የሆነችው ውቧ ቫንኮቨር መስተንግዶውን በፀጋ ተቀብላ ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ እንደሆነች ታውቋል።

 

በዚሁ ለሁለት ቀናት በሚቆየው ውድድር ከስድስት ከተሞች የተውጣጡ 10 ቡድኖች ተጋብዘው፤ ዘጠኙ ቡድኖች የሚገኙ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ የሰሜን ምዕራብ ሀገራት ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ይገናኛሉ።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ