ገንዘቡን ከይሌና ኢሲንባዬቫ እና ከሳንያ ሪቻርድስ ጋር ይካፈላል

አትሌት ገለቴ ቡርቃ በ2000 ሜትር አንደኛ ወጣች

(ተጨማሪ ዘገባና ፎቶዎች የታከለበት)

Kenenisa Bekele crosses the finish line to win the men's 5000m race at the IAAF Golden League Memorial Van Damme athletics meeting in Brussels September 4, 2009.

Ethiopia Zare (ዓርብ ነሐሴ 29 ቀን 2001 ዓ.ም. September 4, 2009)፦ ከአስር ደቂቃ በፊት ዛሬ ዓርብ ነሐሴ 29 ቀን 2001 ዓ.ም. ማምሻውን በቤልጅየም ብራስልስ እየተደረገ ባለው የ2009ኙ የጎልደን ሊግ 6ኛና የመዝጊያው ውድድር ላይ ቀነኒሳ በቀለ በ5000 ሜትር በአንደኝነት በማጠናቀቅ የአንድ ሚሊዮን ዶላሩ ጃክ ፖት ተቋዳሽነቱን አረጋገጠ። ውድድሩን በ12 ደቂቃ ከ55፡31 ሰከንድ ነው የጨረሰው። አንድ ሚሊዮን ዶላሩን ከራሺያዊቷ የምርኩዝ ዘላይዋ ይሌና ኢሲንባዬቫ እና ከአሜሪካዊቷ የ400 ሯጭ ሳንያ ሪቻርድስ ጋር ይካፈላል።

 

Yelena Isinbayeva of Russia (L), Kenenisa Bekele of Ethiopia (C) and Sanya Richards of the U.S. (R) celebrate with fake gold bars at the end of the IAAF Golden League Memorial Van Damme athletics meeting in Brussels September 4, 2009. Bekele (5000m), Richards (400m) and Isinbayeva (pole vault) shared the $1 million jackpot for winning their events at all six Golden League meetings.

 

በዛሬው የ5000 ሜትር የወንዶች ውድድር በኢትዮጵያውያኖቹ መካከል ከፍተኛ ፉክክር የታየ ሲሆን፣ አትሌት የማነ መርጋ በ12 ደቂቃ ከ55፡66 ሰከንድ ቀነኒሳን ተከትሎ ነው የገባው። አትሌት ቀነኒሳ አንደኛ የወጣው አትሌት የማነህን ከአንድ ሰከንድ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ቀድሞት በመግባት ሲሆን፣ አትሌት አሊ አብዶሽ ደግሞ በ12 ደቂቃ ከ56፡53 ሰከንድ አራተኛ ወጥቷል።

 

Kenenisa Bekele (L) is congratulated by compatriot Imane Merga after winning the men's 5000m race at the IAAF Golden League Memorial Van Damme athletics meeting in Brussels September 4, 2009.

 

ሦስተኛ የወጣው ኬንያዊው አትሌት ቪንሰንት ኪፕሮፕ ቺፕኮክ ሲሆን፣ እርሱም በ12 ደቂቃ ከ55፡98 ሰከንድ ነው ውድድሩን የጨረሰው። በዚህ ውድድር ላይ በቀነኒሳ፣ በየማነ፣ በቪንሰንት እና በዓሊ መሃከል የነበረው ፉክክር ከፍተኛ ነበር። በተለይም በቀነኒሳ እና በየማነ መሃከል የተካሄደው ፉክክር ልብ አንጠልጣይና አስደሳች ነበር።

 

በዚሁ ውድድር ላይ የተሳተፈው አትሌት አበራ ኩማ በ13 ደቂቃ ከ29፡40 ሰከንድ 16ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቅቋል።

 

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ባለፈው ኦገስት በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10000 እና በ5000 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት በዓለም የመጀመሪያው አትሌት በመሆን ታሪክ መሥራቱን መዘገባችን አይዘነጋም። አትሌቱ በ10000 ማሸነፍ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ተሸንፎ እንደማያውቅ ይታወቃል።

 

በዚሁ ዛሬ ዓርብ ነሐሴ 29 ቀን 2001 ዓ.ም. በብራስልስ ቤልጅየም በተካሄደው የሴቶች የ2000 ሜትር የሩጫ ውድድር አትሌት ገለቴ ቡርቃ በ5 ደቂቃ ከ30፡19 ሰከንድ አንደኛ ወጥታለች። ኬንያውያኖቹ አትሌቶች ቪቪያን ቼሩዮት እና ሜርሲ ቼሮኖ በ5 ደቂቃ ከ35፡46 ሰከንድ እና በ5 ደቂቃ ከ35፡65 ሰከንድ ተከታትለው በመግባት ሁለተኛ እና ሦስተኛ ወጥተዋል። አትሌት ገለቴ በረዥም ርቀት ልዩነት (ከ5 ሰከንድ በላይ) ነበር ኬንያውያኖቹን ጥላቸው የገባችው፡፤

 

በዚህ የሴቶች የ2000 ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ የተሳተፈችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዓለምነሽ በለጠ በ5 ደቂቃ ከ35፡60 ሰከንድ ውድድሩን በ13ኝነት አጠናቃለች።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ