Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 6 ቀን 2000 ዓ.ም. April 14, 2008)፦ ንብረትነቱ የሼክ መሐመድ ሁሴን አላሙዲንን (በዋናነት)፣ የአቶ አብነት ገ/መስቀል እና የአቶ ታደሰ ጥላሁን የተባሉ አንድ ሌላ ባለሀብት የሆነው ናሽናል ኦይል ኩባንያ (ኖክ) በተባለው ነዳጅ ማደያ ላይ በዛሬው ዕለት ፍንዳ መድረሱን ከስፍራ የደረሰን ዘገባ አስረዳ።

 

ኖክ የተባለው ነዳጅ ማደያ በኢትዮጵያ ያለውን የነዳጅ ማደያ ገበያ እየተቆጣጣረ የመጣ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት በአገሪቱ ውስጥ ካሉት 150 በላይ የነዳጅ ማደያዎች በአዲስ አበባ ውስጥ በሚገኙት በሁለቱ ላይ ፍንዳታ መድረሱ ታውቋል።

 

ፍንዳው የደረሰው በተለምዶ ገርጂ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ኢምፔሪያል ሆቴልን አለፍ ብሎ በሚገኘው የነዳጅ ማደያ እና በመገናኛ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የኖክ ነዳጅ ማደያ ላይ ነው።

 

በሁለቱም ማደያዎች ላይ በኬሮሲን (ለቤት ውስጥ መስሪያ የሚያገለግል ነጭ ጋዝ) መቅጃ ጋር የፈነዳ ሲሆን፣ ስፍራውን የፌደራል ፖሊስና ደህንነቶች ተቆጣትረውት ታይቷል።

 

በፍንዳታው የደረሰ ጉዳት መኖሩ ለጊዜው ያልታወቀ ሲሆን፣ ሁለቱም ማደያዎች አካባቢ ሰው እንዳይቆም ተከልክሎና ማደያዎቹ ተዘግተውና ታጥረው ፍተሻ እየተደረገባቸው ይገኛል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ