አምስት ሰዎች ብቻ እንዲጠይቁት ተፈቀደ

Ethiopia Zare (እሁድ ሚያዝያ 19 ቀን 2000 ዓ.ም. April 27, 2008)፦ ዝነኛው ድምጻዊ፣ የግጥምና ዜማ ደራሲ ቴዎድሮስ ካሳሁን ወደ ጨለማ ቤት መግባቱንና ውስን ሰዎች ብቻ እንዲጠይቁት መደረጉን ዛሬ የአዲስ አበባ ምንጮቻችን ገለጹ።

 

ቴዲ አፍሮ በተለምዶ ‘ማማ’ በመባል ወደሚታወቀው የጨለማ ቤት ውስጥ ከተላከ በኋላ ቅዳሜና እሁድን ሊጠይቁት የሄዱት ዘመዶቹና ደጋፊዎቹ ውስጥ አምስቱ ብቻ ተመርጠው ለአጭር ጊዜ እንዲጠይቁት የተደረገ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

 

‘ማማ’ በመባል የሚታወቀው የጨለማ ቤት ውስጥ ከአሁን በፊት ታስረው የነበሩ ግለሰብ አነጋግረን እንደገለጹት ማማ የሚባለው ቦታ የፖለቲካ እስረኞች ብቻ የሚገቡበትና ምንም አይነት መረማመጃም ሆነ መንቀሳቀሻ የሌለው ጠባብ ቦታ መሆኑን ጠቁመው በመኪና አደጋ ተጠርጥሮ የታሰረን ሰው በምን ምክንያት ጨለማ ቤት ሊያሳስረው እንደቻለ ግራ እንዳጋባቸው ገልጸውልናል።

 

በኢትዮጵያ ውስጥ የፍትህ ሥርዓቱ ከሌሎች ሀገራት በእጅጉ የተለየ ነው የሚሉትና በካናዳ ነዋሪነታቸውን ያደረጉ የሕግ ባለሙያ እንደሚሉት ደግሞ በሌሎች ሀገራት የፍትህ ሂደት አንድ እስረኛ በፍርድ እስካልተወሰነበት ድረስ ንጹኅ መሆኑንና የፍትህ ሲስተሙም ንጹህ ሰዎችን የሚከላከል ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ያለው የፍትህ ሂደት ግን ንጹኅ ሰዎችን እያሳደዱ በማጉላላት ላይ ያነጣጠረ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አክለውም በዚህ ወጣት ድምጻዊ ላይ አገዛዙ የሚያደርገው ወከባም በብዙ የሀገሪቱ ዜጎች ላይ የሚከሰት መሆኑን ጠቁመዋል።

 

በአሁኑ ሰዓት ህዝብ የሚወደውንና የሚመርጠውን ግለሰብም ሆነ ቡድን እያሳደዱ ማዋከብ ብቻ ሳይሆን በሕይወታቸውም ላይ በማናቸውም ሰዓት አደጋ ሊደርስ ይችላል የሚሉት ሌላ ግለሰብ እንደገለጹት፤ ይህ አገዛዝ ይህንን በህዝብ ልብ ውስጥ ሰርጾ የገባ ድምጻዊ መርዘው እንዳያጠፉት መስጋቱን ለኢትዮጵያ ዛሬ ገልጿል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ