Ethiopia Zare ( ቅዳሜ ጥቅምት 18 ቀን 2004 ዓ.ም. October 29፣ 2011)፦ በሶማሊያዋ ፑንትላንድ በጎሳ መሪዎች የሞት ወይንም የ700 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ለተወሰነበት አስመሮም ኃይለስላሴ እውቁ የሙዚቃ ሰው ቴዎድሮስ ካሳሁን የገንዘብ ቅጣቱን እንደከፈለለት ተዘገበ።

 

የ31 ዓመቱ አስመሮም በ2002 ዓ.ም በስደት ከሚኖርበት የሶማሊያዋ ፑንትላንድ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ዘራፊዎች ገብተው ባለቤቱን ለመድፈር በሚሞክሩበት ወቅት ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ባደረጉት መከላከል ከዘራፊዎቹ አንዱ ህይወቱ በማለፉ እስር ቤት ገብቶ በሀገሪቱ የጎሳ መሪዎች የሞት ቅጣት ተወስኖበት ቆይቷል።

ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በፖንትላንዷ ቦሳሶ ከተማ በእስር ላይ የነበረው ኢትዮጵያዊ የገንዘብ ቅጣቱን መክፈል ካልቻለ የሞት ውሳኔው እንደሚፈጸም በሰሙ ቤተሰቦቹና ወዳቹ ከፍተኛ የገንዘብ ማሰባሰብ እርዳታ ሲያካሂዱ ቢቆዩም ለአስመሮም እህት የሞት ውሳኔው ከመጽናቱ ሁለት ቀናት በፊት ከእውቁ ሙዚቀኛ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የ700 ሺህ ብር በቼክ እንደደረሳትና ወንድሟን ከእስር ቤት ለማስፈታት ከሚመለከተው ክፍል ጋር በመነጋገር ላይ መሆኗን ገልጻለች።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ