ሰዓሊው 700 ሺህ ብር ካሣ ጠይቆ ነበር

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 25 ቀን 2000 ዓ.ም. August 01, 2008)፦ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት "ቴዎድሮስ ካሳሁን ከኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤት ጋር፣ በጋራ በመሆን ጭንብል ለብሰው፣ መንገድ ዘግተው የሥዕል ሥራዎቼን ከመኖሪያ ቤቴ በመስረቅ ያለፈቃዴ ተጠቅመዋል። የሥዕሎቼን ክብር በሚነካ ሁኔታም ተጠቅመው የሞራል ጉዳት አድርሰውብኛል" በሚል የ700 ሺህ ብር ካሣ ክፍያ ጥያቄ አቅርቦ ክሱ ውድቅ የተደረገበት ሰዓሊ ይግባኝ ጠየቀ።

 

ሰዓሊው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩ በታየበት ወቅት፤ ክሱ ውድቅ ተደርጎበት፣ ቴዲንም ሆነ የኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤት አቶ ተሾመን ሊያስጠይቃቸው እንደማይገባ፣ ሥዕሎቹ በክሊፑ ላይ መታየታቸው እንኳን ሞራል ሊነኩ ይቅርና እንደውም ባማረ ሁኔታ በክሊፑ ውስጥ በመታየታቸው፣ የተለየ ውበት ማግኘታቸው ከችሎት ተገልፆ ክሱ ተዘግቶ ነበር።

 

ባለፈው ሰኞ ሰዓሊው "በዓቃቤ ሕግ በኩል የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተቃውሞ፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሏል። በይግባኙ ቴዲ አፍሮና የኤሌክትራ ሙዚቃ ቤት ባለቤት አቶ ተሾመ ጥፋተኛ ተብለው የሞራል ካሣው እንዲሰጠው ጠይቋል።

 

ለክሱ መነሻ የሆኑት የሰዓሊው ፎቶግራፎች ለኢትዮጵያ አየር መንገድ በነፃ የተሰጡ እንደሆነና የሙዚቃ ክሊኙ በተቀረፀበት ሆቴል ግርግዳ ላይ ተሰቅለው የሚታዩ ናቸው።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ