Teddy Afroጋዜጠኛው በገደብ ተለቋል

የቴዲ ጠበቃ እንቁጣጣሽን ቃሊቲ ያሳልፋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ሐምሌ 30 ቀን 2000 ዓ.ም. August 06, 2008)፦ የቴዎድሮስ ካሳሁንን ችሎት የሚመሩት ዳኛ ልዑል ገብረማርያም በችሎቱ ሂደት ላይ ፍትሃዊ ባለመሆናቸው የተነሳ ለዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ክስ እመሰርታለሁ በማለት ለአዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ቃለምልልስ የሰጠው የቴዲ አፍሮ ጠበቃና ቃለ ምልልሱን ያተመው ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ዛሬ የተፈረደባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ዘጋቢዎቻችን አረጋገጡ።

 

ተከሳሾቹ ለሁለት ቀናት በዳኛው ትዕዛዝ መሰረት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ታስረው የቆዩ ከመሆናቸውም በላይ፣ ለሁለት ቀን በችሎት ተገኝተው ጥፋተኛ ያለመሆናቸውን ያስረዱ ቢሆንም፤ ዛሬ በዋለው ችሎት የቴዲ አፍሮ ጠበቃ ሚሊዮን አሰፋ ለአንድ ወር ከሃያ ቀን በእስር እንዲቆይ የተፈረደበትና ወደ ቃሊቲ የወረደ ሲሆን፤ የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ደግሞ በሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ የአንድ ወር እስራት ተፈርዶበት በገደብ የተለቀቀ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

 

የገደብ እስራት የሚጸናው በሁለት ዓመት ውስጥ ጋዜጠኛው በሌላ ክስ ከተወነጀለ የአንድ ወር እስራቱ ተፈጻሚ ይሆናል።

 

የቴዲ አፍሮ ጠበቃ አቶ ሚሊዮን አሰፋ አንድ ወር ከሃያ ቀኑን የሚጨርሰው መስከረም 13 ቀን  2001 ዓ.ም. ሲሆን፣ ፍርድ ቤቶችም ከነገ ጀምሮ ለሁለት ወር ስለሚዘጉ እንቁጣጣሽን በእስር ሊያሳልፍ እንደሚችል ታውቋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ