Teddy AfroEthiopia Zare (ዓርብ ነኀሴ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. August 29, 2008)፦ የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) አብሮ አደግ የሆኑትና የቤተልሔም ት/ቤት ተማሪዎች በየእምነታቸው በጾምና በፀሎት ሊያስቡት ማቀዳቸውን ገልጸው፣ በጾምና በፀሎቱ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ የቴዲ አፍሮ አድናቂዎች፣ ዘመድና ወዳጆች በያሉበት በመሆን ዘር፣ ፖለቲካ፣ ኃይማኖት ወደማይለየው ፈጣሪያቸው ይማፀኑ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

 

የጾም የፀሎቱ ዓላማ የቴዲ አፍሮ ”በአንድነት ከገባን የፍቅር ሱባዔ” የሚለው ሕልሙና አስተሳሰቡ ምኞቱ በእውን ተፈጽሞ እንዲያይ፣ በጭንቀቱ ጊዜ መረጋጋትን፣ በኀዘኑ ጊዜ መጽናናትን፣ በተከዘ ጊዜ ተስፋን፣ በፀለየ ጊዜ ምልሱን እንዲያገኝ መሆኑን አብሯ አደግ ጓደኞቹ ለኢትዮጵያ ዛሬ ከላኩት አንድ ገጽ ደብዳቤ ለመረዳት ችለናል።

 

በዚህ የጥሪ ደብዳቤያቸው ላይ ፀሎቱን አካትተዋል። ፀሎቱን ለማግኘትና ሙሉውን ደብዳቤ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! 

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ