Lemma Megersa

አቶ ለማ መገርሳ

ምክክሩ በኢትዮጵያና በአሜሪካን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር እንደኾነ ተደምጧል

ኢዛ (ሰኞ ኅዳር ፳፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. December 2, 2019)፦ ከሰሞኑ አነጋጋሪ የኾነ ቃለምልልስ ለአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የሠጡት የመከላከያ ሚኒስትርና የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ የመሩት የልዑካን ቡድን ዋሽንግተን ዲሲ መግባቱ ተገለጸ።

አቶ ለማ የመሩት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ወደ አሜሪካ የተጓዘው በኢትዮጵያና በአሜሪካን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር እንደኾነ፣ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገልጸዋል።

ከፍተኛ የልዑካን ቡድኑ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ የደረሰው ጠዋት እንደኾነም ጠቅሠዋል። አቶ ለማ በመሩት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ውስጥ እነማን እንደተካተቱ አልተገለጸም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ