Ethiopia Zare (ዓርብ መስከረም  ፱ (9) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 19, 2008)፦ የአርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) ጠበቃ አቶ ሚሊዮን አሰፋ በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ በተደረገው 7ኛ የኢህአዲግ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ታውቋል። በቀጣዩ ቀጠሮ ተጨማሪ ጠበቃ ሊቆምለት ታስቧል።

 

በመኪና ገጭቶ የሰው ሕይወት አጥፍቶ አምልጧል በሚል፣ ክስ ተመሥርቶበትና ክሱን እንዲከላከል ተበይኖበት በክርክር ላይ የሚገኘው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሣሁን (ቴዲ አፍሮ) የሕግ ጠበቃ፣ ከብይኑ በኋላ ጉዳዩን እያዩ በሚገኙት ዳኛ ልዑል ገ/ማርያም በቀረበባቸው ክስ አራት ቀናትን በእስር ማሳለፋቸው ይታወሳል።

 

ፍርድ ቤቱ ጠበቃው 50 የእስር ቀናትን እንዲቀጡ ቢወስንም፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበው ይግባኝ ለመመልከት ቀጠሮ በመያዙ፣ የቅጣት ውሣኔው ለጊዜው መታገዱ ይታወሳል።

 

ከሦስት ሣምንት በኋላ ከሌላ አንድ ተጨማሪ ጠበቃ ጋር ችሎት በመቅረብ፣ የመከላከያ ማስረጃ ያቀርባሉ ተብለው የሚጠበቁት የቴዲ አፍሮ ጠበቃ አቶ ሚሊዮን አሰፋ፣ በኢህአዲግ 7ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ሃሳብ ሲሰጡ ታይተዋል።

 

በተጨማሪም ምንጮቻችን እንደገለጹት መስከረም 29 ቀን 2001 ዓ.ም. በሚኖረው ቀጣይ ቀጠሮ ተጨማሪ ጠበቃ ሊቆምለት መታሰቡ ታውቋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ