አቶ አሸብር ባልቻ

አዲሱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ

ዶክተር አብርሃም በላይ ተሸኙ

ኢዛ (ዓርብ የካቲት ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 21, 2020)፦ በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሹመት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በመኾን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚነታቸው በለቀቁት በዶክተር አብርሃም በላይ ምትክ አዲስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተሾመ።

ዶክቶር አብርሃምን ተክተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ በመኾን የተሾሙት አቶ አሸብር ባልቻ ናቸው።

አቶ አሸብር ዋና ሥራ አስፈፃሚ እንዲኾኑ የተሰየሙት በዶክተር አብርሃም በሚመራው የድርጅቱ ሥራ አመራር ቦርድ ውሳኔ እንደኾነም ተመልክቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ድርጅቱ የሻረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይን በደማቅ ፕሮግራም እንደሸኛቸው የኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል። (ኢዛ)

ዶ/ር አብርሃም የኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች አሸኛኘት ሲያደርጉላቸው
ዶ/ር አብርሃም የኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞች አሸኛኘት ሲያደርጉላቸው

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ